Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fm 107.8

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofm107dot8
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.12K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 101

2022-07-14 16:03:00
4.0K views13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 13:47:25 በመዲናዋ ሊተገበሩ የታሰቡ የከተማ ፈጣን አዉቶቢስ ትራንስፖርት ኮሪዶሮች ይፋ ተደረጉ

በአዲስ አበባ ከተማ ሊተገበሩ የታሰቡ የከተማ ፈጣን አዉቶቢስ ትራንስፖርት (Bus Rapid Transit) ኮሪዶሮችን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ይፋ አድርጓል።

የከተማ ፈጣን አዉቶቢስ ትራንስፖርት (BRT) በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች እየተተገበረ ያለ ዘመናዊ የትራንስፖርት ሲስተም ሲሆን፤ ራሱን የቻለ የተከለለ መንገድ፣ በቀላሉ የተሳፋሪን ፍሰት ማስተናገድ የሚያስችሉ መጠበቂያዎች፣ ከአዉቶቢስ ዉጭ የሆነ የክፍያ ሥርዓት፣ ለአዉቶቢስ ጥገናና ስምሪት የሚያገልግል ዴፓ ያለው፣ በመንገድ መጋጠሚያዎች ለአዉቶቡስ ቅድሚያ የሚሰጥ እና የኮሪዶር ልማትን የሚያበረታታ የብዙሃን ትራንስፖርት ዓይነት ነዉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የብዙሃን የትራንስፖርት ችግር በመፍታት ፈጣን፣ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ተደራሽ፣ ወጪ ቆጣቢ እና አካባቢያዊ ተስማሚነቱ የተረጋገጠ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎትና ሥርዓት እንዲኖር ታስቦ 15 የBRT ኮሪደሮች ተለይተዉ በመሪ እቅዱ ላይ መቀመጡን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት ፈጣን የአውቶቢስ ትራንስፖርት አገልግሎት መሥመሮች እንደሚከተከለው ተለይተዋል፦

መሥመር-1፡- ከዊንጌት ተነስቶ በሆላንድ ኤምባሲ 3 ቁጥር ማዞሪያ አድርጎ አለርት አየር ጤና

መሥመር-2፡- ከዊንጌት በመርካቶ አድርጎ ሜክሲኮ- ጎፋ ወደ ጀሞ የሚደርስ

መሥመር-3፡- ከጉለሌ በለገሃር ጎፋ ገብርኤል አድርጎ ላፍቶ ሃና ማርያም የሚሄድ

መሥመር-4፡- ሽሮሜዳ በአራት ኪሎ በመገናኛ አድርጎ ኮተቤ ካራሎ የሚወስድ

መሥመር-5፡- ከመገናኛ በቦሌ ድልድይ አድርጎ ለገሃር

መሥመር-6፡- ከጦር ኃይሎች በቄራ አድርጎ ቦሌ ድልድይ

መሥመር-7፡- ከአየር ጤና በቶታል አድርጎ ብስራተ ገብርኤል በፑሽኪን አደባባይ ሜክሲኮ

መሥመር-8፡- ከቦሌ በኡራኤል ካዛንቺስ በአራት ኪሎ አድርጎ ስድስት ኪሎ ፈረንሳይ የሚያደርስ

መሥመር-9፡- ከአየር ጤና በመካኒሳ ቆጣሪ እስከ ቃሊቲ

መሥመር-10፡- ከቃሊቲ ቦሌ

መሥመር-11፡- ከካራሎ በሲኤምሲ ሰሚት አድርጎ በቦሌ ለሚ አይቲ ፓርክ የካ ቦሌ አራብሳ እስከ አያት

መሥመር-13፡- ከቡልቡላ በቂሊንጦ ኮዬ ፈጬ

መሥመር-14፡- ከለቡ በአቃቂ ኮዬ ፈጬ

መሥመር-15፡- ከኢምፔሪያል ሆቴል ጎሮ አድርጎ ቦሌ አራብሳ

መሆናቸዉን ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ አመላክቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 07 ቀን 2014 ዓ.ም
3.7K views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 09:19:36 የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 07-11-14
3.8K views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:49:44 “ኤልሻዳይ” ግብረ ሰናይ ድርጅት ከኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ጋር በመመሳጠር የተጠረጠሩበትን የሙስና ወንጀሎች ፖሊስ ይፋ አደረገ

ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን መንግስትዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት በተረጂዎች ስም ከብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለእርዳታ የተዘጋጀን ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶችን አላግባብ ወስዶ ለግል ጥቅም አውሏል በሚል ተጠርጥረው ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ፖሊስ ባደረገው የማጣራት ስራ የተሰበሰበውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በተለይ ለኢቲቪ አስታውቋል።

በምርመራ ሂደቱ የተገኙ ግኝቶችም፦

1ኛ- ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን በየጊዜው አሉ ተብሎ እርዳታ የሚጠየቅላቸው ዜጎች በትክክል ስለመኖራቸው እና አለመኖራቸው በተደረገ ምርመራ፡-

ድርጅቱ በክልል ካሉት ማዕከል ውስጥ በ3 ማዕከላት ማለትም በአማራ ክልል ቁጭት ለልማት ማዕከል ከ 2010 እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ የተረጂዎችን ቁጥር በመጨመር፤ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ2019 ማእከሉ 14 ተረጂዎች ብቻ እያለው ዓመቱን ሙሉ በ2 ሺህ 631 ተረጂዎች ስም የእርዳታ ስንዴ ጠይቆ ከኮሚሽኑ የተሰጠው መሆኑን በማስረጃ ተረጋግጧል።

ድርጅቱ በአፋር እና ደቡብ ክልል ማዕከል የተረጂዎችን ቁጥር በመጨመር የጠየቀ እና የወሰደ መሆኑን፣ በጋምቤላ ክልል ማዕከል ስም የጠየቀው ተፈቅዶለት ያልወሰደ እና በሙከራ ደረጃ የቀረ መሆኑን በማስረጃ ለማረጋገጥ ተችሏል።

2ኛ- ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን በተለይ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ አለአግባብ ከኮሚሽኑ ጠይቆ የተሰጠውን የእርዳታ ስንዴ ምን እንደሚያደረገው በተደረገ ምርመራ፡-

ድርጅቱ ከመንግስት የወሰደውን ስንዴ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ለሚገኝ ኪያ የዱቄት ፋብሪካ (ሶሮሮ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር) 66 ሺህ ኩንታል ስንዴ በ66 ሚሊዮን ብር ሸጦ ገንዘቡን የወሰደ መሆኑን፣ 6 ሺህ ኩንታል ስንዴ በብር 6 ሚሊዮን ግምት በ4 ተሸከርካሪ በአይነት ከሶሮሮ ትሬዲግ የተለዋወጠ መሆኑን፤

ኤልሻዳይ ድርጅት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አዋሽ መልካ የሚገኝ ነጃኼ ሬዲን የዱቄት ፋብሪካ ባለቤት እና ሰራተኛ ስም 27 ሚሊዮን ብር የገባለት በመሆኑ ነጃሄ ትሬዲን ተጠይቆ 15 ሚሊዮን ብር ያስገባው ከኤልሻዳይ ስንዴ ገዝቶ መሆኑን በሰነድ በማስደገፍ ቃሉን የሰጠ ሲሆን ቀሪው 12 ሚሊዮን ብር ቢሆን የሰነድ አያያዝ ችግር ነው እንጂ የስንዴ ግዥ ብር ነው በማለት የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል።

3ኛ- በኤልሻዳይ ድርጅት የበላይ አመራር አቶ የማነ ገ/ማሪያም እና በኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ መካከል መመሳጠር መኖር እና አለመኖሩን በተደረገ ምርመራ፡-

ኤልሻዳይ ኮሚሽኑን እርዳታ ለመጠየቅ ያዘጋጀው የአንድ ጊዜ በእጅ ጽሁፍ የረቀቀ መጠይቅ ሰነድ ተገኝቶ በፎረንሲክ ምርመራ ረቂቂ የእጅ ጽሁፍ ተመርምሮ የብሔራዊ አደጋ መከላከል ስራ አመራር ከሚሽን ኮሚሽነር በኤልሻዳይ ስም የተዘጋጀ መሆኑ ተረጋግጧል።

በተጨማሪም በኮሚሽነሩ ቤተሰቦች ላይ በተደረገ ማጣራት፦

1ኛ - የኮሚሽነሩ ወንድ ልጅ ኢያሱ ምትኩ ካሳ በኤልሻዳይ ድርጅት በተላለፈ ገንዘብ መኪና ተገዝቶለት ይህንኑ መኪና መልሶ ኤልሻዳይ የገዛው መሆኑን በማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን፤ እንዲሁም ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በኤልሻዳይ ድርጅት ፀሀፊ ስም በወር 15 ሺህ ብር በተከራየው ሙሉ ጊቢ ውስጥ የሚኖር መሆኑን መረጃ ደርሶ፤ በቤቱ ውስጥ የተባለው የኮሚሽነሩ ልጅ መኖሩን ወርሃዊ ክፍያውንም ኤልሳሻዳይ ድርጅት እንደሚከፍልለት በሰውና በሰነድ ተረጋግጧል፣

2ኛ- የኮሚሽነሩ ሴት ልጅ ወ/ሮ ሚኪያ ምትኩ ካሳ በኤልሻዳይ ድርጅት ውስጥ ተቀጣሪ ሳትሆን በኤልሻዳይ ድርጅት ፔሮል ውስጥ ስሟ ተካቶ ለ1 ዓመት ያክል በወር አምስት ሺህ ብር ደመወዝ በባንከ በኩል ሲከፈላት እንደነበር በማስረጃ ማረጋገጥ ተችሏል። እንዲሁም ከኤልሻዳይ ድርጅት የባንክ ሂሳብ ብር 800 ሺህ ብር ወደ ሚኪያ ምትኩ በተለያዩ ጊዚያት ገቢ መሆኑን በሰነድ ማረጋገጥ ተችሏል፤ እንዲሁም ተጨማሪ ማጣራም በማጣራት ላይ ይገኛል

3ኛ- የኮሚሽነሩ ባለቤት በወ/ሮ ሶፊያ ጀማል ስም ከእንይ ጀኔራል ቢዝነስ ሪል ስቴት (በወኪል የማነ ወ/ማሪያም በርሄ አማካኝነት (የኤልሻዳይ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ) ከኤልሻዳይ ድርጅት ሂሳብ ወጭ በተደረገ በብር 8,306,737.75 የቦታ ስፋት 388.75 ካሬ ሜትር የሆነ በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ የተገዛው መሆኑን እንዲሁም ተጨማሪ ጥቆማዎች ላይም ማጣራት እየተካሄደ ስለመሆኑ

4ኛ- የኮሚሽነሩ ወላጅ እናት ወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ከኤልሻዳይ ድርጅት 5,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን) ብር በሲፒኦ ገቢ በሆነላት ብር በቦሌ ክፍለ ከተማ ብቻ በተደረገ ማጣራት በኤልሻዳይ ድርጅት እና የኮሚሽነሩ የቅርብ ጉዳይ አስፈፃሚ በሆኑ ግለሰቦችና የወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ህጋዊ ወኪሎች አማካኝነት 7 ቤቶች የገዛች መሆኑ በተጨማሪም ከወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ስም የተገዙ ቤቶችን በተመለከተ ሙሉ ውክልና ለኤልሻዳይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ለሆኑት አቶ የማነ ገ/ማሪያም ውክልና ሰጥተው የተገኙ መሆኑን ይህ ቀሪ የማጥራት ስራ የሚቀረው ቢሆንም መመሳጠር መኖሩን ያስረዳል።

እንዲሁም ከእነዚህ ሰባት ቤቶች መካከል አንዱን አቶ የማነ ገ/ማሪያም በተሰጠው ውክልና መሰረት ከወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ለአቶ ምትኩ ካሳ መሸጡን ይህ ሽያጭ ሲፈፀም አቶ የማነ ገ/ማሪያም ሀሰተኛ መታወቂያ፣ ሀሰተኛ ፎቶ መጠቀሙ ተረጋግጧል።

5ኛ አቶ ምትኩ ካሳ ሚኖሩበት ቤት ቁጥር በማስመዝገብ እና የሌላን ሰው ፎቶግራፍ በመጠቀም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በስማቸው አሰርተው የተገኙ መሆኑን በማስረጃ ማረጋገጥ ተችሏል፣ ቤተሰባዊ ግንኙነቱ በመጣራት ላይ የሚገኝ 18 አመት ባልሞላው ልጅ መሀመድ አብዲልፈታህ አብዱላሂ በተበለ ስም ከእንይ ጀኔራል ቢዝነስ ሪል ስቴት ከኤልሻዳይ ድርጅት ሂሳብ ወጭ በተደረገ ገንዘብ በብር 8,306,737.75 የቦታ ስፋት 388.75 ካሬ ሜትር የሆነ በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ የተገዛው መሆኑን፣

በምርመራ መዝገቡ ላይ ተጠርጣሪ የሆኑት፡-

1. የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነሩ አቶ ምትኩ ካሳ እና ቤተሰቦቻቸው፤

2. የኤልሻዳይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ የማነ ወ/ማሪያም፤

3. የኤልሻዳይ ድርጅት ኦፕሬሽናል ዘርፍ ምክትል ስ/አስኪያጅ ዶ/ር ዮናስ ወ/ትንሳይ እና

4. የኤልሻዳይ ድርጅት የፋይናንስ ዘርፍ ምክትል ስ/አስኪያጅ አቶ ደመወዝ ኃይሉ መሆናቸውን
ኢቢሲ ፖሊስን ጠቅሶ ዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም
4.3K views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:20:42
የጋራ መኖሪያ ቤት ላይ የወጣው እጣ ውድቅ ተደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ውድቅ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ25 ሺሕ 491 ያወጣው የ20/80 እና 40/6 ላይ እጣ የወጣበት ሲስተም ላይ የተአማኒነት ጉድለት እንደነበር በመረጋገጡ ነው የወጣውን ዕጣ ውድቅ ያደረገው፡፡

ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ከዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ የጀመረው ከተማ አስተዳደሩ በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች መገኘታቸውን መግለጹ ይታወሳል::

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም
5.3K views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 15:46:36
ከፍተኛ ነዳጅ አምራች ከሆኑ ሀገራት አንዷ የሆነችዉ ናይጄርያ ነዳጅ አጥሮኛል እያለች ነው፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መናሩን ተከትሎ ናጄርያዊያን ባለሀብቶች ፊታቸውን ወደ ጸሕይ ብርሀን ማዞራቸውን አልጀዚራ ዘስነብቧል፡፡

ናይጄርያ ለ200ሚሊየን ዜጎቿ ከ12ሺህ ሜጋ ዋት የማይበልጥ የሀይል አቅርቦት እንዳላት ነው የሚነገረው፡፡
ይሕ በመሆኑ የተነሳም የሀገሪቱ ባለሀብቶች ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ ወደ ጸሀይ ሀይል እንዳዞሩ ተሰምቷል፡፡

የናይጄርያ የነዳጅት ኮሚሽን እንዳስታወቀው ሀገሪቷ በአመት ለነዳጅ 22 ቢሊዮን ዶላር ፈሰስ ታደርጋለች፡፡
አሁን ባለው መረጃ መሰረት በናይጄርያ አንድ ሊትር ናፍጣ 800 ናይራ ወይም 1.93 የአሜሪካ ዶላር እየተሸጠ ይገኛል፡፡
ይህም ከዩክሬን ጦርነት ጋር ቀጥተኛ ግኑኝነት እንዳለው መረጃዉ አመልክቷል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም
4.0K views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 12:29:49
አሁን ያለዉን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ከ3 ሽህ በላይ የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ያስፈልጉኛል ---የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሁን ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ በሶስት ዋና ዋና መንገዶች ለማሻሻል ማቀዱን አስታዉቋል፡፡

ችግሩን ለመፍታት በቀዳሚነት በዘመቻ መልክ ለመልስራት ማቀዱን የገለጸዉ ቢሮው ለዚህም በቢሮው አቅም ያሉ የስምሪት መስመሮች ላይ በጥብቅ እንዲሰራ መታቀዱን ተናግሯል፡፡

የታቀደ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለመስጠትም ከአንድ አመት ተኩል እስከ ሁለት አመት ይፈጃል ያለውን የተቀናጀ የትራንስፖርት ስርአት ለማዘጋጀት እየሰራሁ እገኛለሁም ብሏል ቢሮዉ፡፡

በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ ዘመናዊ የከተማ የትራንስፖርት ስርአትን ለመዘርጋት መታቀዱንም የቢሮው ሃላፊ አቶ አቶ ዳዊት የሺጥላ ተናግረዋል፡፡

በጥቂት አመታት ዉስጥ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች፣ የተሽከርካሪ ምርጫ፣ የክፍያ ሁኔታ፣ ጊዜን እና ሌሎች ፍላጎቶቻቸውን በአሟላ መልኩ እንደ ምርጫቸው እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋልም ነዉ ያሉት፡፡

አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ ትራንስፖርት ችግሩን ለመቅረፍ ከ3 ሽህ 184 ያላነሱ የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች እንደሚያስፈልገውም አስታዉቋል፡፡
አሁን ላይ ቢሮው ከ1 ሽህ 100 ያልበለጡ አዉቶብሶች ያሉት በመሆኑ ፍላጎት እና አቅርቦት እየተመጣጠነ አይደለም ተብሏል፡፡
ከዚህ ቀደም የታዘዙ 110 አዉቶቡሶች ከመስከረም በፊት እጄ ይገባሉ ያለው ቢሮው፣ ተጨማሪ 210 አዉቶብስ ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ማቀዱንም ገልጿል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም
4.0K viewsedited  09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 12:13:41
የካፍ ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገብተዋል::

የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ መትሴፔ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸውን ካፍ ኦንላይን ጽፏል፡፡

በቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ ከባህል እና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጄላ መርዳሳ ፣ ከእግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ጂራ እና ስፖርቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይገናኛሉ፡፡

ሞትሴፔ ከእግር ኳስ ክለቦች ፕሬዝደንቶች ጋር በመወያየት ጉብኝታቸውን እንደሚያጠናቅቁም ተገልጿል፡፡

በአቤል ጀቤሳ
ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም
3.7K views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 11:43:34
"ግሪን ቴክ አፍሪካ" በተሰኘ ኩባንያ የተመረቱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዛሬ ስራ ጀምረዋል፡፡


ተሸከርካሪዎችን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በዛሬዉ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ አስጀምረዋል።

የትራንስፓርት ዘርፉን ተደራሽና ፈጣን በማድረግ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የትራንስፖርት ስርዓት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በዚህ ወቅት ተናግረዋል፡፡


ስራ የጀመሩት ተሽከርካሪዎች ለመዲናዋ ነዋሪዎች ለአንድ ወር ያህል ነጻ የትራስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጡ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ተሽከርካሪዎቹ የተለያየ መጠን ያላቸውና የአየር ብክለትን በመቀነስ ለአካባቢ ጥበቃና ደህንነት ጉልህ ሚና አላቸው ነው የተባለው፡፡

በግሪን ቴክ አፍሪካ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች በአንድ ሙሉ ቻርጅ በአማካይ ከ200 እስከ 240 ኪሜ ሊጓዙ የሚችሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ ርቀት በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች 20 ብር ወጪ እንደሚጠይቅና በነዳጅ በሚሠሩ ተሽከርካሪዎች አሁናዊ ዋጋ እስከ 950 ብር የሚጠይቅ መሆኑን በንፅፅር ገልፀዋል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም
3.7K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 11:19:24
የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ኮሚሽነሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው ዛሬ በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት።

በፌዴራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ለኢቲቪ እንዳሉት፣ ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት "ኤልሻዳይ" ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው።

ይህ ኤልሻዳይ የተሰኘ ድርጅት በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሀዋሳ፣ በእንጅባራ እና በሌሎችም አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡን ነው ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ የተናገሩት።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ሰፊ ክትትል ሲያደርግ እንደነበረም ረዳት ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም
3.8K views08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ