Get Mystery Box with random crypto!

አሁን ያለዉን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ከ3 ሽህ በላይ የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ያስ | Ethio Fm 107.8

አሁን ያለዉን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ከ3 ሽህ በላይ የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ያስፈልጉኛል ---የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሁን ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ በሶስት ዋና ዋና መንገዶች ለማሻሻል ማቀዱን አስታዉቋል፡፡

ችግሩን ለመፍታት በቀዳሚነት በዘመቻ መልክ ለመልስራት ማቀዱን የገለጸዉ ቢሮው ለዚህም በቢሮው አቅም ያሉ የስምሪት መስመሮች ላይ በጥብቅ እንዲሰራ መታቀዱን ተናግሯል፡፡

የታቀደ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለመስጠትም ከአንድ አመት ተኩል እስከ ሁለት አመት ይፈጃል ያለውን የተቀናጀ የትራንስፖርት ስርአት ለማዘጋጀት እየሰራሁ እገኛለሁም ብሏል ቢሮዉ፡፡

በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ ዘመናዊ የከተማ የትራንስፖርት ስርአትን ለመዘርጋት መታቀዱንም የቢሮው ሃላፊ አቶ አቶ ዳዊት የሺጥላ ተናግረዋል፡፡

በጥቂት አመታት ዉስጥ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች፣ የተሽከርካሪ ምርጫ፣ የክፍያ ሁኔታ፣ ጊዜን እና ሌሎች ፍላጎቶቻቸውን በአሟላ መልኩ እንደ ምርጫቸው እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋልም ነዉ ያሉት፡፡

አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ ትራንስፖርት ችግሩን ለመቅረፍ ከ3 ሽህ 184 ያላነሱ የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች እንደሚያስፈልገውም አስታዉቋል፡፡
አሁን ላይ ቢሮው ከ1 ሽህ 100 ያልበለጡ አዉቶብሶች ያሉት በመሆኑ ፍላጎት እና አቅርቦት እየተመጣጠነ አይደለም ተብሏል፡፡
ከዚህ ቀደም የታዘዙ 110 አዉቶቡሶች ከመስከረም በፊት እጄ ይገባሉ ያለው ቢሮው፣ ተጨማሪ 210 አዉቶብስ ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ማቀዱንም ገልጿል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም