Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fm 107.8

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofm107dot8
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.32K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 100

2022-08-29 09:16:11 የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 23-12-14

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
3.6K views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:03:25
ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ

አሸባሪው ሕወሐት በአንድ በኩል የተለመደውን የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማ ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል።

የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚያስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል።

አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል።

ነሃሴ 21 ቀን 2014 ዓም
አዲስ አበባ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
4.5K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:59:33 ፈረስ ትራንስፖርት ከአገልግሎቱ ተጠቃሚ ከሆኑት ደንበኞቹ የሰበሰበውን ማይልስ ወደ ብር በመቀየር ለተለያዩ በጎ አድራገት ስራዎች  በስጦታ  አበረከተ፡፡


የፈረስ ትራንስፖርት ከደንበኞቹና ከአሽከርካሪዎቹ በበጎ ፈቃደኛነት የሰበሰበውን ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የፈረስ ማይልሶችን ለተለያዩ የልማትና የበጎ አድራጎት ስራዎች  ለመለገስ
ዛሬ  በራዲሰንብሉ ሆቴል ባዘጋጀው የስጦታ መርሃ ግብር  ለሚመለከታቸው አካላት  የገንዘብ ስጦታ አስረክቧል ።


በዚሁም መሰረት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ(1መቶ ሺ ብር) ለአርቲስት ዘነበች ገሰሰ ቤተሰቦች(1 መቶ ስድስት  ሺ  174  ብር) ለ ቢላሉል ሃበሺ የልማት እና መረዳጃ እድር(100 ሺ ብር) ፣ ለጌርጌሲዮን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል(145 ሺ 695 ብር)፣ ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ማዕከል(365 ሺ 914 ብር)  በእያዳንዳቸው በስማቸው በተሰበሰበ ማይልስ ስጦታው በብር ተቀይሮ  በፈረስ ትራንስፖርት  ከፍተኛ አመራሮች  በኩል  በዛሬው እለት ልገሳ ተደርጓል፡፡


እንዲሁም በስራ ላይ እያሉ ህይወታቸውን ላጡ  ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው ሃምሳ ሺ ብር የስጣታ ድጋፍ  አድርጓል ፡፡

ድርጅቱ ይህንን የልገሳ ፕሮግራም ሲያደርግ ይሄኛው ለሁለተኛ ዙር ሲሆን መሰል የልገሳ ፕሮግራም በሶስተኛው ዙር  ፤ ለኢትዮጵያ  ካንሰር  ህሙማን  አሶሴሽን ፣ለኢትዮጵያ  ዳያልሲስ ሴንተር፣  ለዘውዲቱ መሸሻ እና በቤተሰብ በጎ አድራጎት  ማህበር  እና ለሜቅዶኒያ የበጎ  አድራጎት  ማህበር  አጠናክሮ ማይልሶችን በመሰብሰብ በቀጣይ  እንደሚያስተላልፍ አስታውቋል፡፡


የፈረስ ትራንስፖርት አገልግሎቱ በዋናነት በአዲስ አበባ ብቻ ይሁን እንጂ በቀጣይ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ የአገሪቱ ከተሞች እንዲሁም በጎረቤት ሀገራት አገልግሎቱን እንደሚጀመር ያስታወቀ ሲሆን በመጪው አዲስ ዓመትም የዴሊቨሪ አገልግሎት ከሚጀመሩ ሌሎች አገልግሎቶች መሃል እንደሚሆን ተገልጿል፡፡


ፈረስ ትራንስፖርት የአገልግሎቱን አቅራቢዎችና ተጠቃሚዎች በቴክኖሎጂ አማካኝነት በማገናኘት ቀልጣፋና ዘመናዊ  ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎቱን ለሃያ አራት ሰዓት የሚያቀርብ ድርጅት ነው፡፡


በየውልሰው ገዝሙ

ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም
4.0K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 17:58:17
3.6K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:16:43
3.7K views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 21:23:22 የክልልነት ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኙ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ጉዳዩን የአመጽና የሁከት መነሻ ለማድረግ በሚሞክሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስጠነቀቀ።

የፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ መንግሥት በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በተለያዩ ጊዜያት የሚነሱ የክልልነት ጥያቄዎችን በሀገሪቱ ሕግና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየሠራ ይገኛል፡፡

ነገር ግን አንዳንድ አካላት ይህንን ሂደት በሚቃረን መንገድ ሕጋዊ ጥያቄዎችን ሽፋን በማድረግ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር በህቡዕ ዝግጅት ማድረጋቸውን የጋራ ግብረ ኃይሉ ባደረገው ክትትል ስለተደረሰበት ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል ነው ያለው፡፡

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በስሩ የሚገኙ ዞኖችን በአዲስ መልክ ለማዋቀር እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ የጋራ ግብረ ኃይሉ በመግለጫው አመላክቷል፡፡

ጌዲኦ ዞንም በአዲስ መልክ ከሚዋቀሩ ዞኖች አንዱ መሆኑን ገልጾ÷ የኅብረተሰቡን ተሳትፎ በተጨባጭ ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ሰሞኑን የማወያያ ሰነዶች ተዘጋጅተው የዞኑ ነዋሪ እየመከረበት መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ይሁንና የጌዲኦ ዞን የክልልነት ጥያቄ መፍትሔ የማይሰጠው ከሆን ጥያቄያችንን በኃይል እናስፈጽማለን የሚሉ አካላት በህቡዕ ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በተጨባጭ መረጃዎች ማረጋገጡን ነው የተገለጸው፡፡

በህቡዕ የተደራጁት አካላት የጥፋት እቅዶቻቸውን ለማሳካት ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች በመክፈት የተዛቡና የፈጠራ መረጃዎችን እያሰራጩ መሆኑን ያመለከተው የጋራ ግብረ ኃይሉ መግለጫ÷ ማኅበረሰቡንም በተሳሳቱ መረጃዎች ለማደናገር እየሞከሩ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

እነዚህ አካላት ያደራጇቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ቤት ለቤት ጭምር እየተንቀሳቀሱ ቅስቀሳ እያደረጉ እንደሚገኙ ይህም በደኅንነትና በጸጥታ አካላት እንደተደረሰበትም አመልክቷል፡፡

የጋራ ግብረ ኃይሉ ለዚህ እኩይ ዓላማ የተደራጁና የተሰለፉ ግለሰቦችንና ቡድኖችን በደኅንነትና በጸጥታ መዋቅሩ አማካይነት ለይቶ ክትትል እያደረገባቸው መሆኑን በማስገንዘብ÷ ከጥፋት ተልዕኳቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሰስቧል፡፡

ይህን ተላልፈው በሚገኙ ላይም ተገቢው ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 08 ቀን 2014 ዓ.ም
2.7K views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 16:57:19

3.1K views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 15:14:22
የስሪላንካዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጊዚያዊ ፕሬዝዳንት ሆነዉ ቃለ መኃላ ፈፀሙ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ራኒል ዊክሪሚስጊ ስሪላንካን በጊዚያዊ ፕሬዝዳንትነት ለመምራት ቃለ ማኃላቸዉን በዛሬዉ እለት ፈፅመዋል፡፡
የአገሪቱ ፕሬዝዳንት የነበሩት ጎታባያ ረጃፓክሳ አመፁን ሽሽት ከአገር መሰደዳቸዉ ይታወሳል፡፡

ጎታባያ በግዞት ላይ እያሉ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለአገሪቱ ፓርላማ አስገብተዋል፡፡
ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ ተረክበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ራኒል ዊክሪሚስጊ አገሪቱ የገጠማትን የኢኮኖሚ ዉድቀት ለመፍታት እንደሚሰሩ አስታዉቀዋል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 08 ቀን 2014 ዓ.ም
3.3K views12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 13:24:46
3.7K views10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 09:58:47 የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 08-11-14
3.4K views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ