Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ከተማ 6ኛ ዙር የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራ ትላንት ተጀምሯል። በ6ኛ ዙር በተመረጡ | Ethio Fm 107.8

በአዲስ አበባ ከተማ 6ኛ ዙር የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራ ትላንት ተጀምሯል።

በ6ኛ ዙር በተመረጡ በሰባት ክፍለ ከተሞች ከግንቦት 03/09/2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ ተከታታይ አምስት ወራት 50 ሺህ የመሬት ይዞታዎችን የማረጋገጥ ስራ ይካሄዳል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታውቋል።

ኤጀንሲው ምዝገባው ፦

በኮልፌ ቀራኒዮ፣
በቂርቆስ፣
በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣
በቦሌ፣
በአዲስ ከተማ፣
በልደታና በአራዳ ክፍለ ከተሞች ባሉ 50 ቀጠናዎችና 211 ሰፈሮች እንደሚከናወን ገልጿል።

ይህ የይዞታ ማረጋገጥ እወጃ ከተላለፈ ከ15 ቀናት በኃላ የይዞታ ይረጋገጥልኝ ጥያቄዎች በክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤቶች ቀርበው ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይቻላል ተብሏል።

ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ በተመረጡ ቀጠናዎችና ሰፈሮች ስራው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ባለቱ አምስት ወራት ውስጥ የመረጃ ልዩነት እንዳይፈጠር ሲባል ምንም ዓይነት የስመ- ንብረት ዝውውር አገልግሎት እንደማይሰጥ ኤጀንሲው ማስታወቅን ከአ/አ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም


ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።