Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ ባሉ የነዳጅ ማደያዎች ላይ መጨናነቅ መፈጠሩ ተገለፀ፡፡ በመዲናዋ ባሉ የነዳጅ ማደያዎች | Ethio Fm 107.8

በመዲናዋ ባሉ የነዳጅ ማደያዎች ላይ መጨናነቅ መፈጠሩ ተገለፀ፡፡

በመዲናዋ ባሉ የነዳጅ ማደያዎች ላይ ከሰሞኑ መጨናነቅ መስተዋሉን የነዳጅ ማደያዎች ማህበር አስታውቋል።

የነዳጅ ማደያዎች ማህበር ቦርድ አባል የሆኑት አቶ ደሳለኝ አበባየሁ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ከግንቦት 1/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ በመላው ሀገሪቱ መጀመሩን ተከትሎ ወደ አዲስ አባባ ዙሪያ ሄደው ይቀዱ የነበሩ ተሸከርካሪዎች ወደ ከተማዋ ተመልሰው እየቀዱ በመሆኑ መጨናነቅ መፈጠሩን ገልፀዋል፡፡

ከሰሞኑ ተረጋገግቶ የነበረው ሰልፍ የተመልሰው በዚህ ምክንያት ነው የሚሉት የቦርድ አባሉ፣ ቀስ በቀስ ግን ወደ ነበረበት ይመለሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

የኤልክትሮኒክስ የነዳጅ ግብይቱ ተግባራዊ ሲደረግ በርካታ መጨናነቆች ተፈጥረው እንደነበር ያስታወሱት አቶ ደሳለኝ፣ አሁንም ቴክኖሎጂው ችግር ፈቺ እና ኑሮን ለማቅለል የመጣ መሆኑን ህብረተሰቡ ሊረዳን ይገባል ብለዋል፡፡

ነዳጅ በኤልክትሮኒክስ ግብይት በመላው ሀገሪቱ ከግንቦት አንድ ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡

በክልሎች አከባቢ ያለው የህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀርፈው የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬተር ወይዘሮ ሰሀርላ አብዱላሂ አስታውቀዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም