Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fm 107.8

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofm107dot8
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.32K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-05-05 10:45:00
82ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል በዓል እየተከበረ ነው።

ኢትዮጵያውያን አርበኞች የጣልያንን ወራሪ ኃይል ድል ያደረጉበት 82ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል በዓል አራት ኪሎ በሚገኘው የአርበኞች ድል መታሰቢያ ኃውልት በመከበር ላይ እየተከበረ ይገኛል ።

"አብሮነት ለጽናትና ድል" በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ በሚገኘው የመታሰቢያ በዓል ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከድል ሃውልቱ ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

በበዓሉ ላይ አባት አርበኞች፣ እናት አርበኞች፣የአርበኛ ቤተሰቦች፣የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣የአገር መከላከያ ሰራዊት ተወካዮችና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።
3.7K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 06:35:40
50ሚሊዮን ዶላር የዉጪ ምንዛሬ ያስቀራል የተባለለት የጎማ ማቀነባበሪያ ተመረቀ።

በዓመት ከ25ሺ እስከ 50ሺ ጎማዎችን ማምረት የሚችል የከባድ መኪና ጎማ መልሶ ማቀነባበሪያ ተመረቋል።

በምርቃቱ ላይም በርካታ ባለክስዮኖች አንዲሁም የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባን ጨምሮ በርካታ አርቲስቶች በተገኙበት የምርቃት መርሀ ግብሩ ተካሂዷል።

በገላን ከተማ 5ሺ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈዉ ግዙፍ የጎማ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት በ150ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት አቶ የምወድሀ ታደለ የዜድ ኤም ትሬዲንግ አክስዮን ማህበር የዳይሬክተሮቾ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ  ገልፀዋል።

ዜድ ኤም አክስዮን ማህበር  ከአጠቃላይ ፕርጀክቶች ካፒታል 3.5 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ አራት ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ነድፎ እየሰራ ነዉም ብለዋል።

በዜድ ኤም  ትሬዲንግ የተገነባዉ ይህ የጎማ መልሶ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ስራ ሲጀምር እስከ 50ሚሊዮን ዶላር የዉጪ ምንዛሬ ያስቀራልም ተብሏል።

ማህበሩ ከጎማ ማቀነባበሪያ በተጨማሪ 300.000ሊትር ወተት ማቀናበሪያ፣በኢኮ ቱሪዝም ሆቴሎችና ሎጆች እንዲሁም በታዳሽ ሀይል በአሌትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን መገጣጠሚያ በቀጣይ ለመስራት ማቀዱን አቶ ሳሙኤል ተገኝ የዜድ ኤም ቴሬዲንግ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ገልፀዋል።

በአሁን ሰዓት 3.2 ቢሊዮን ብር ካፒታል የሚያወጡ የንግድ ፕሮጀክቶችን ነድፎ በመስራት ላይ ይገኛል ተብሏል።

አክስዮን ማህበሩ በቀጣይ ሰባት አመታት ውስጥ 400 ሚሊየነሮችን ለማፍራትና ለአንድ መቶ ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚሰራ ተገልፆል።

ዜድ ኤም ትሬዲንግ አክስዮን ማህበር ከአራት ዓመት በፊት በ154 ባለድርሻ አባላት የተመሠረተ አክስዮን ማህበር ነዉ።


በአቤል ደጀኔ

ሚያዝያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም
1.5K views03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 15:09:41

2.8K views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 13:07:00
የቢቢሲ ሊቀመንበር በቦሪስ ጆንሰን የሙስና ቅሌት ምክንያት ከስልጣናቸዉ ለቀቁ፡፡


የቢቢሲ ሊቀ መንበር ሪቻርድ ሻርፕ የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስተር በነበሩት ቦሪስ ጆንሰን የሙስና ቅሌት ጋር በተገናኘ በፍቀዳቸዉ ከኃላፊነታቸዉ ተነስተዋል፡፡

ግለሰቡ ከሰሞኑ የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሙስና ቅሌትን የሚገልጽ ዘገባ ከመውጣቱ በፊት ነው ስራቸውን መልቀቃቸው የታወቀው።

ሻርፕ በወቅቱ ከነበረው የቦሪስ አስተዳደር ካቢኔ ፀሐፊ ጋር በመሆን የሃገሪቱን አስተዳደራዊ መመሪያዎችን ጥሰዋል ተብሏል፡፡


በተጨማሪም "ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር ቦሪስ ጆንሰን ገንዘብ በመቀበል፣ ፋይሎችን ሆን ብለው በማፋለስ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል እንደተወነጀሉ አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡


በመሳይ ገብረ መድህን

ሚያዝያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
3.1K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 12:57:04
ዜጎችን ከሱዳን ሊያስወጣ የነበረ የተርክዬ አዉሮፕላን በፈጥኖ ደራሽ ሃይል መመታቱ ተነገረ፡፡


በሱዳን የሚገኙ ዜጎችን ለማስወጣት ወደ ካርቱም ያቀናዉ የተርክዬ አዉሮፕላን በፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ መመታቱ ተሰምቷል፡፡

አዉሮፕላኑ ጥቃት ያጋጠመዉ በነዳጅ ማስተላለፊያ አካሉ ላይ ስለመሆኑም አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

አዉሮፕላኑ ከተመታ በኋላ የከፋ አደጋ ሳይደርስበት በዋዲ ሴይዲና አዉሮፕላን ማረፊያ ማረፉንም አንካራ አስታዉቃለች፡፡

የተርክዬ የመካለከያ ሚኒስቴር በሰጠዉ መግለጫ በዜጎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰና አዉሮፓላኑን ጠግኖ ተልዕኮዉን እንደሚያሳካ አስታዉቋል፡፡


በአባቱ መረቀ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.6K views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 12:50:05
በገለልተኛ አካል ሳይጣራ ከቅድመ ትንተናና ፍረጃ መቆጠብ ይገባል---ኢዜማ!


የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ የሺጥላ ከቤተሰቦቻቸው እና ጠባቂዎቻቸው ጋር በጉዞ ላይ እያሉ በተፈጸመባቸው ጥቃት በመገደላቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡


የግድያው ምክንያት፣ ሂደት እና የገዳዮች ማንነት በተመለከተ በገልለተኛ አካል በሚደረግ ምርመራ በግልጽ ታውቆ ፍትሕ እስከሚሰጥ ድረስ፤ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጨምሮ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በግድያው ዙሪያ ትንተና፣ ፍረጃ እና የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር ከሚደረግ ሩጫ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

እንዲህ አይነት የማኅበረሰቡን እሴት የሚንዱ መሰል ግድያዎችን በአንድ ድምጽ ልናወግዝ ይገባል ብሏል ኢዜማ።


ለሟቾች ቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድ በሙሉ መጽናናትን እንዲሁም በጥቃቱ ጉዳት አጋጥሟቸው የሕክምና ክትትል እያደረጉ ላሉት ፈጣሪ ምህረቱን እንዲሰጣቸው ፓርቲው ምኞቱን ገልጿል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
2.2K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 11:36:08
ኢትዮ ኢንተርናሽናል ኤክስፖ ሊዘጋጅ ነው።

በአምስት ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረገው ኢትዮ - ኢንተርናሽናል ኤክስፖ ሊካሄድ ነው።

ኤክስፖውን ትሬድ ኢትዮጵያ ከአዲስ እይታ እና ከአቡቀለምሲስ የሪል ስቴት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን አዘጋጅቶታል ተብሏል።

ኤክስፖው በግብርና ፣ ሪል ስቴት ፣ በታዳሽ ሃይል እና ኤሌክትሪክ መኪና ፣ በጨርቃጨርቅ እና አልባሳት እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ትኩረት ማድረጉን የትሬድ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ አቶ በርናባስ ወ/ገብርኤል ተናግረዋል ።

ኤክስፖው በአመት ሁለት ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በአዲስ አበባ እና በአሜሪካ የሚካሄድ ነው ተብሏል።

ባለፈው አመት በኦንላይን ብቻ ይሄ ኤክስፖ ተካሂዶ ነበር ያሉት አቶ በርናባስ በዚህ አመት ለ3 ቀናት በአካል ከተካሄደ በኋላ ለቀጣይ 5 ወራት ደግሞ በኦንላይን ይቀጥላል ነው ያሉት ።

በኤክስፖው ላይ 25 ሺህ ቤት ፈላጊ ዲያስፖራዎች ይሳተፉበታል የተባለ ሲሆን ካሉበት ሆነው በኦንላይን ኤክስፖውን በመሳተፍ የሚፈልጉትን ቤት ማማረጥ እንደሚችሉ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ኢንተርሌግዥሪ ሆቴል ከግንቦት 9-11 የሚካሄድ ሲሆን በገዢ እና በሻጭ መካከል ያለውን የግብይት ክፍተት በመሙላት የማስተሳሰር ስራ ይሰራበታል ተብሏል።

እስከዳር ግርማ
ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም
2.3K views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 11:35:48 የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
2.5K views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 19:41:36 ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በተከበሩ ግርማ የሺጥላ፣ በግል ጥበቃዎቻቸው እና በቤተሰቦቻቸው ላይ የመንግሥትና የድርጅት ሥራዎችን በአካባቢው ላይ ሠርተው ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን እየመጡ በነበረበት ሰዓት መንዝ ጓሳ ላይ በታጠቁ ኢ-መደበኛ ኃይሎች ጥቃት ተፈጽሟል፡፡

በዚህም ግርማ የሺጥላን ጨምሮ እስካሁን በደረሰን መረጃ የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ በደረሰው ልብ ሰባሪ ጥቃት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰማውን መሪር ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልጻል፡፡

እንዲህ አይነት አጥፊዎች እያደረሱት ያለው መረን የለቀቀ የሽብር ድርጊት ክልሉን እየመራ ያለውን መንግሥትና መላውን ሕዝብ የበለጠ ሊያጠናክር እንጂ በጥፋት ሃይሎች ሴራና ፍላጎት የሚሳካ ምንም አይነት ተልዕኮ የለም፡፡

ስለሆነም ይህንን የሽብር ሥራ እየሠሩ ያሉ እንዲህ አይነት ኃይሎች ላይ የክልሉ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል፡፡ የጥቃቱን አድራሾችም ለሕግ ያቀርባል፡፡ ማንኛውም በእንደዚህ አይነት ድርጊት የተሳተፉ ኀይሎችንንና ተባባሪዎችን ሁሉ ከያሉበት ለሕግ በማቅረብ አስፈላጊው ፍትሕ እዲረጋገጥ ይደረጋል፡፡

በመሆኑም መላው የክልላችን ሕዝብ የተፈጠረውን የሽብር ድርጊት ከማውገዝ ጀምሮ ወንጀለኞች ለሕግ ቀርበው ፍትሕ እንዲረጋገጥ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና እንዲረጋጋ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የጥፋት ኃይሎች ከዚህ በላይ ዓላማ ያላቸው እና ክልሉን የማፍረስ ተልዕኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በኋላ የክልሉ መንግሥት እንደማይታገስ እና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ እናረጋግጣለን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም

ባሕር ዳር
3.4K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 18:30:35
የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ  መገደላቸው ተሰምቷል።

ጠ/ ሚ ዐብይ አህመድ በአቶ ግርማ የሺጥላ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

ጠ/ ሚስትሩ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ይሄን አስፍረዋል


"ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል። ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው።

ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው" ብለዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
3.5K viewsedited  15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ