Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fm 107.8

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofm107dot8 — Ethio Fm 107.8
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofm107dot8
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.32K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-04-24 15:14:57
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ66 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በ2015 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ንብረቶች ከ66.1 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የመንግስት ግዥ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጎጃም ታደለ ለኢትዮኤፍኤም ተናግረዋል።

በፌዴራል መ/ቤቶች እንዲወገዱ ውሳኔ የተሰጠባቸው ንብረቶች 22 ፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች 44 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በሽያጭ በማስወገድ እንዲሁም የ19 ፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች 198 ሎት ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን በሽያጭ በማስወገድ ገቢ ማስገኘት የተቻለ ሲሆን በድምሩ በዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎችና ንብረቶች ከ66 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።

በበጀት አመቱ 53.8 ሚሊየን ብር ገቢ የማግኘት እቅድ እንደነበራቸው የሚናገሩት ሃላፌዋ ከተገኘው ገቢ ጋር ሲነፃፀር የዘንድሮው ብልጫ ማሳየቱም ተመላክቷል።

እሌኒ ግዛቸው
ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
1.9K viewsedited  12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 14:12:38
የኢትዮጵያ አካልጉዳተኞች መብት ድንጋጌ ረቂቅ በዚህ ዓመት ለመንግስት ይቀርባል ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች መብት ድንጋጌ ሊወጣ ዝግጅት ላይ መሆኑን ከ 2 ዓመታት በፊት ተገልጾ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች መብት ድንጋጌ ረቂቅ ለመንግስት ከ5 ወራት በፊት ሊቀርብ ተዘጋጅቶ ነበር ያሉት በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አሳልፈዉ አህመዲን ናቸዉ፡፡

ከተለያዩ ማህበራት ረቂቁን በደንብ ማየት ያስፈልገናል በሚል በተነሳ ጥያቄ መሰረት ረቂቁ ለመንግስት ሳይቀርብ የተወሰኑ ወራትን ወስዷል ነዉ ያሉት ፡፡

ከፌዴሬሽኑ እና ይህን ጉዳይ ካዋቀረዉ ኮሚቴ ጋር በጋራ ስንሰራ ቆይተናል ያሉት አቶ አሳልፈዉ በአሁኑ ሰዓት የመጨረሻዉን ቅርጽ የማስያዝ ስራ እየሰራን ነዉ ብለዋል፡፡

ረቂቁ በጣም ሰፊ እና ለመንግስትም ሲቀርብ ብዙ ዉይይት የሚደረግበት በመሆኑ በደንብ መመልከቱ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ሊዘገይ ችሏል ነዉ ያሉት፡፡

ስራ አስፈጻሚዉ አክለዉም ረቂቁ የትምህርት ጉዳይ ፣ከስራ ቅጥር ጋር ተያይዞ ስላለ ኮታ እንዲሁም የግብር አከፋፈል ስርዓትን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮችን በዉስጡ የያዘ መሆኑን ገልጸዉ ይህን ጉዳይ ከሚመለከታቸዉ ተጠሪ ተቋማት ጋርም በትብብር የመስራት ስራ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

መብትን ከማስፋት እንዲሁም ተጠያቂነትን ከማስፈን ጋር ተያይዞ በርካታ ጉዳዮችን የያዘ የህግ ማዕቀፍ ስለሆነ ነዉ ሰፊ ጊዜን የወሰደዉ ነገርግን ይህ ዓመት ሳይጠናቀቅ ረቂቁ ለመንግስት ይቀርባል ብለዋል፡፡


እስከዳር ግርማ
ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም
1.8K views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 14:03:25
በተቋማት ላይ በተደረገ የአደጋ ስጋት ቁጥጥር ከ17 ሺህ ተቋማት 25ቱ ብቻ ፈቃድ እንዳላቸው ተገለፀ

በአስራ ሰባት ሺህ ተቋማት ላይ በተደረገ የአደጋ ስጋት ቁጥጥር 25 ተቋማት ብቻ አለም አቀፍ የአደጋ ስጋት ምዘና መስፈርት እንዳሟሉ የአዲጽስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ይክፈለው ወልደመስቀል ለኢትዮኤፍኤም ተናግረዋል።

ለአመታት በተደረገው የአደጋ ስጋት እና ቁጥጥር 180 ባለኮከብ ሆቴሎች 13ቱ መስፈርቱን ያሟሉ ሲሆን በከተማዋ ከሚገኙ 667 ፋብሪካዎች አምስቱ ብቻ አለም አቀፍ የአደጋ ምዘና መስፈት እንዳሟሉም ገልፀዋል።

እስካሁን ባለው ሁኔታ በተቋማት ላይ ፍተሻ ማድረግ እና የምክክር አገልግሎት የሚሰጥ የነበረ ሲሆን በተቋማት ላይ የንግድ ፈቃድ እስከ ማገድ እና ተቋሙ አገልግሎት አንዳይሰጥ የማድረግ ህጋዊ እርምጃ በቅርቡ መውሰድ እንደሚጀመር ነግረውናል።

በመዲናዋ በሶስት ወራት ውስጥ 300 አደጋዎች የደረሰ ሲሆን በቅርቡ በሾላ ገበያ በደረሰ የእሳት አደጋ 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ሊወድም መቻሉም በመድረኩ ተገልፆል።

አደጋን ለመከላከል እኛም ሚና አለን በሚል መሪ ቃል ለኪነጥበብ ባለሞያ እና ለሚዲያ ባለሞያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።

እሊኒ ግዛቸው
ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም
1.7K viewsedited  11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 13:49:14

1.6K views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 13:42:54
አንድንድ የትራፊክ ፖሊሶች የትራፊክ ህጉን የሚጥሱ የህግ አካላትን መቅጣት” ስራዬን አጣለው” የሚል ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል ተባሏል፡፡

የትራፊክ ህጉን እንዲያከብሩ ግዴታ የተጣለባቸው አንዳንድ የህግ አካላት ፤ህጉን ሲጥሱ እንደሚስተዋሉ የመንገድ ደንነት ባለሞያ የሆኑት ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

የትራፊክ ህጉን የሚጥሱ የህግ አካላትን መቅጣት ደግሞ የትራፊክ ፖሊሶችን “ስራዬን አጣላው” የሚል ስጋት ውስጥ እንደሚከታቸው ገልጸዋል፡፡

ይህም እርሳቸው በነበሩበት የትራፊክ ፖሊስነት የስራ ዘመናቸው የገጠማቸው ነገር እንደሆነ አንስተዋል፡፡
የመንገድ ደንነት ባለሞያው እንደሚሉት ከሆነ አንዳንድ በመንግስት የስራ ሃላፊነት ላይ የሚገኙ አካላት በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ያልተፈቀዱ መንገዶችን ሲጠቀሙ ይስተዋላል፡፡

ህግን በማክበር ግንባር ቀደም መሆን አለባቸው ተብለው ስለሚጠበቁ ህግን በሚጥሱበት ወቅት በማህበረሰቡ ዘንድ በቀላሉ ተጋላጭ እንዲሆኑ እንደሚያረጋቸው ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም በትራፊክ ፖሊስነት የሚሰሩ ባለሞያዎች ቆራጥ ሆነው የትራፊክ ህጉን ሊያስከብሩ እና በመንግስት ሆነ በደንነት አካላት ሽፋን የትራፊክ ህግን የሚጥሱ አሽከርካሪዎችን ሊቀጡ ይገባል ብለዋል፡፡

ካልሆነ ግን የነዚህ አካላት ለትራፊክ አደጋ የሚኖራቸው አስተዋፅኦ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ አንስተዋል፡፡

መሳይ ገ/መድህን
ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም
1.7K viewsedited  10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 12:59:25
ማደያዎች ላይ የሚደረገዉ ቁጥጥር ተጠናክሮ ይቀጥላል ተባለ።

በማደያዎች ላይ ይደረግ የነበረዉ ቁጥጥር ከሶስትዮሽ ርክክብ ከእጅ በነፃ መንገድ በዲጂታል መንገድ ይፈፀማል ተብሏል።

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰሀረላ አብዱላይ ለጣብያችን እንደገለፁት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመቀናጀት ነደጅ አመላላሽ ቦቴዎች ላይ ጂፒ ኤስ በመግጠም የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

የፈሳሽ አመላላሽ ቦቴዎች ላይ በተገጠመዉ ጂፒ ኤስ የት እንደደረሱ እንዲሁም በሰዓቱ ማደያ መደርሳቸዉንም ቁጥጥር ይደረጋል ብለዋል።

ነዳጅ ማደያዎችንም ቁጥጥር እንደሚደረግ የገለፁ ሲሆን ከሶስተኛ ወገን በነፃ መልኩ ሴንሰር ማደያዎች ላይ በመግጠም ከቢሮ በመሆን የመቋጣጠር ስራ እየሰራ ነዉ ተብሏል።

አሁን እየተተገበረዉ ያለዉ አሰራር ብክነቶችን ከመታደግ አንፃር ፋይዳዉ ከፍ ያለ ነዉ ብለዋል ዋና ዳይሬክተሯ።

ከዛሬ ሚያዝያ 16 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በደጂታል የክፍያ አማራጮች ብቻ ግብይቱ ይፈፀማል መባሉም ይታወሳል።

አቤል ደጀኔ

ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
1.9K viewsedited  09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 10:51:24 የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
2.3K views07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:14:43 1444ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቀ፡፡ የበዓሉ የኢድ ሶላት ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶች እንደሚኖሩም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በየዓመቱ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ የሆነው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል በመላው የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ በዓል ነው፡፡ በመሆኑም በአዲስ አበባ ስታዲዮም እና በዙሪያው የሚከናወነው የበዓሉ የኢድ ሶላት ላይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች የሚታደሙበት እንደመሆኑ የሶላት ስነ-ስርዓቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ እና የበአሉ ድባብ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ወቅታዊውን የፀጥታ ሁኔታ ያገናዘበ ዕቅድ አውጥቶ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይል አስታውቋል፡፡

የዕምነቱ ተከታዮች እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በተለይም ለኢድ ሶላት የሚመጣውን ህዝበ ሙስሊም በማስተባበር እና የበዓሉን ድባብ ሊያደፈርስ የሚችል ችግር እንዳያጋጥም ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው በመስራት የሚያደርጉት ተሳትፎ የጎላ እንደሆነ የጠቀሰው የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይል በዘንድሮው በዓልም ይህንኑ አጠናክሮ ለማስቀጠል ከዕምነቱ አባቶች እና ከወጣቶች ጋር ተገቢው ውይይት መደረጉን ገልጿል፡፡
የዕምነቱ ተከታዮች በየአካባቢያቸው በዓሉን ሲያከብሩም ሆነ ወደ ኢድ ሶላቱ ሲመጡ እንደወትሮው ሁሉ የፖሊስን መስተንግዶና ትዕዛዝ በማክበር ተባባሪ እንዲሆኑ እና የበዓሉ ስነ ስርዓት በሰላም እንዲጠናቀቅ መላው የከተማችን ነዋሪዎች የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይሉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡ በዚህ የፀጥታ ማስከበር ሂደት ውስጥ በአካባቢያችሁ ለሰላም እንቅፋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮችን ስትመለከቱ በ011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ ሲልም የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይሉ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ 1444ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል የኢድ ሶላት ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቅ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች እንደሚኖሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ከዚህ በታች የተገለፁት መንገዶች ዝግ መሆናቸውን ተገንዝበው ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙም አሳስቧል ፡፡

በዚህም መሰረት
- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ
- ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ
- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት
- ከፒያሣ አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ
- ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ
- ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ
- ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀኛ
- ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ
- ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደ ፍል ውሃ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት
- ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ
- ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ
- ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለቀላል መኪና የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ እንዲሁም ለከባድ መኪና አጎና ሲኒማ አካባቢ

ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ በመሆኑም ህብረተሰቡ ከፖሊስ የተሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን እያስተላለፈ ለእምነቱ ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የፍቅርና የሰላም እንዲሆን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይል መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡

ኢድ ሙባረክ
1.9K views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 18:45:05
1444ኛው የኢድ አለፈጥር በዓል ነገ እንደሚከበር ተገለጸ።

የሻዋል ወር ጨረቃ በዛሬው እለት አርብ በሳዑዲ በቱሚናር እና ሱዳይር በመታየቷ 1444ኛው የኢድ አለፈጥር በዓል በነገው እለት አርብ እንደሚከበር ታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 12ቀን 2015 ዓ.ም
2.5K viewsedited  15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 15:28:45 በአማሮ ወረዳ የሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ተበድያለው ሲል ቅሬታውን አሰማ፡፡

በደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞን ውስጥ የሚገኘው የአማሮ ወረዳ የበዳንሶ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ባስመዘግብም እወቅና አልተቸረኝም ሲል ከሷል፡፡

ትምህርት ቤቱ ቅሬታውን ያሰማው ከሚጠበቀው በታች ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ያፈሩ መሰል ትምህርት ቤቶች መሸለማቸው ተገቢ አይደለም ሲል ነው፡፡

አንድም ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ ያላስገባ ትምህርት ቤት የዕውቅናና ሽልማት አግኝቷል ሲሉም የትምህርት ቤቱ መምህራንና ርዕሰ መምህራኖች ለጣቢያችን ቅሬታ አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም ተደጋጋሚ የህግና ደንብ ጥሰቶች በትምህርት ቤቱ መምህራን ላይ እንደሚፈጸም የትምህርት ቤቱ መምህራን ገልፀዋል፡፡

የአማሮ ልዩ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት ም/ሀላፊ አቶ አያሌው አሳምነው በበኩላቸው ቅሬታው በሬ ወለድ ነው ሲሉ ለጣብያችን የገለፁ ሲሆን የክልሉ መንግስት በወላይታ ሶዶ በነበረ ጉባኤ ላይ ተወካዮች እንድንልክ የተጠየቀን ሲሆን እኛም አንድ ተማሪ እና አንድ መምህር በአጠቃላይ አምስት ተወካዮችን ከየትምህርት ቤቱ ወክለን ልከናል ብለዋል፡፡

አቶ አያሌው አክለው ዕውቅናና ሽልማቱ 550 እና ከዚያ በላይ ላመጡ ተማሪዎች እንጂ ለመምህራንም ሆነ ለሌላ አካል የተሰጠ ሽልማት የለም ብለዋል፡፡

የወረዳው የትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት በትምህርት አሰጣጥ ሂደታቸው ዝቅ ያለ አፈፃፀም ያላቸውን ትምህርት ቤቶች ተመርጠው ልምድ እንዲወስዱ ከማድረግ በዘለለ የተለየ ጥቅም እንዲያገኝ የተመረጠ አካል የለውም ሲሉ ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡

የፅ/ቤቱ ም/ል ሀላፊ ችግሩን በመወያየት እንፈታው በማለት በተደጋጋሚ ለማወያየት ብንሞክርም ቅሬታ አቅራቢዎች ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል ሲሉ ምላሻቸውን ሰተውናል፡፡

አቤል ደጀኔ
ሚያዝያ 12ቀን 2015 ዓ.ም
2.8K views12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ