2023-04-27 11:15:27
በአዲስ አበባ ከ2ሺ 600 በላይ ግለሰቦች ያለመንጃ ፍቃድ ሲያሽከረክሩ መገኘታቸው ተገለፀ፡፡
በአዲስ አበባ ያለመንጃ ፍቃድ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እየተበራከቱ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዘጠኝ ወራት ውስጥ በዚህ ላይ የተገኙ ከ2ሺህ 638 በላይ ግለሰቦች ያለመንጃ ፍቃድ ሲያሽከርክሩ በመገኘታቸው ቅጣት ተላልፎባቸዋል ተብሏል፡፡
በአዲስ አበባ ፖሊስ ትራፊክ ቁጥጥር መመሪያ የትራፊክ ሙያና ህዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ሀላፊ የሆኑት ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ ለጣብያች በሰጡት ቃል በዘጠኝ ወራት ውስጥ በርካታ የደንብ መተላለፎች ያጋጠሙ ሲሆን የአሽከርካሪ ማረጋገጫ ብቃት ሳይኖራቸው የሚያሽከረክሩ ግለሰቦች መበራከታቸውን ገልፀዋል፡፡
ኢኒስፔክተር አዳነ አክለውም በዚህ ዘጠኝ ወራት ውስጥ 320 በሀሰተኛ መንጃ ፍቃድ ሲያሽከርክሩ የተያዙ ግለሰቦች ላይ ክስ እንደተመሰረተባቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ሁሉም የትራፊክ ደንብ መተላለፎች የትራፊክ አደጋ የሚያስከትሉ ቢሆንም ዋና የሚባሉት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በከተማዋ ስልክ እያወሩ የሚያሽረክሩ በርካቶች አሉ ያሉት ኢንስፔክተር ሰለሞን በዚህ ዘጠኝ ወር ውስጥ ብቻ 73ሺህ 490 አሽከርካሪዎች ስልክ እያወሩ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ሲሆን 81 ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ያለደህንነት ቀበቶ ሲነቀሳቀሱ በመገኘታቸው ቅጣት ተላልፎባቸዋል ተብሏል፡፡
አቤል ደጀኔ
ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
2.5K views08:15