Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና የኢትዮጵያ የባህል አልባሳት እንዲጠፉ ምክንያት እየሆነች ነው---- የፈትል እመቤት! የኢ | Ethio Fm 107.8

ቻይና የኢትዮጵያ የባህል አልባሳት እንዲጠፉ ምክንያት እየሆነች ነው---- የፈትል እመቤት!


የኢትዮጵያዊን መገለጫ የሆኑት የባህል አልባሳት በቻይና የባህል ወረራ ተፈጽሞባቸዋል በዚህም ምክንያት ዘርፉ አደጋ ተደቅኖበታል ተብሏል።

የሃገራችንን ባህላዊ ጥለት መስለው በማሽን የሚታተሙት ጨርቆች ግማሾቹ ከቻይና ተመርተው እንደሚመጡ፤ ኢትዮጵያ ውስጥም የሚመረቱ እንዳሉ የፈትል እመቤት የተሰኘው ድርጅት አስታውቋል።

የኢትዮጵያን ቱባ የባህል አልባሳት ከወረራ ለመከላከል በማሰብ የፈትል እመቤት ከዮድ አብስኒያ የባህል ድርጅት ጋር ስምምነት አድርገዋል።

የፈትል እመቤት ድርጅት መስራች ወ/ሮ ጸዱ ተስፋዬ በሽመና ባለሙያዎች ጥበብ አምረው የሚሰሩት ባሕላዊ የኢትዮጽያ አልባሰት በቻይናዊያን ታትመው ከሚመጡት ጋር ተወዳድሮ ገበያ ውስጥ መዝለቅ ከባድ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።

የቻይናዎቹ አቡጀዲ ጨርቅ ላይ እነሱ ያተሙት ጥለት መሰል ጨርቅ ይለጠፍበታል።
ለመሥራት በጣም ቀላል ነው። ለዚያ ነው በርካሽ ዋጋ የሚሸጠው ብለዋል።
በሸማኔ የሚሠሩ ባህላዊ ልብሶች ብዙ ውጣ ውረድ አልፈው ነው እዚህ የሚደርሱት።


ከጥጥ ማምረት ጀምሮ፤ መፍተል እንዲሁም ከሳባ ወይም ከመነን ጨርቅ ጋር አስማምቶ መሸመን ትልቅ ጥበብ ነው፤ አድካሚም ነው እናም የሚመለከተው አካል ባህላችንን ማስጠበቅ አለበት ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ቻይና ውስጥ ተሠርተው የሚመጡ ጨርቆች ገበያውን መቀላቀል ከጀመሩ በኋላ አምራቾች እና ነጋዴዎች ባዶ እጃቸው መቅረታቸው ተነግሯል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም