Get Mystery Box with random crypto!

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚሰሩ ልማቶች ከወዲሁ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ ነው ተባለ፡፡ የታላቁ የኢት | Ethio Fm 107.8

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚሰሩ ልማቶች ከወዲሁ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ ነው ተባለ፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ከወዲሁ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በመገባደድ ላይ በሚገኘው የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ጥናት ማድረግ ተጀምሯል።

ግድቡ ሲጠናቀቅ ኃይል ከመስጠቱ ባለፈ የቱሪስት መዳረሻ ስለሚሆን፣ ባለሃብቶችን በልማት ስራ ላይ ለማሰማራት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስተባባሪነት ማስተር ፕለን እየዘጋጀለት መሆኑን ነግረውናል።

የህዳሴ ግድብ ውሃው በተኛበት ቦታ ላይ ደሴቶች መኖራቸው ይታወቃል፤ እነዚህም ለቱሪስት መስህብነት እንደሚሆኑ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ለባህር ትራንስፖርት ምቹ ስለሚሆን የቱሪዝም ዘረፉን ያነቃቃል ነው የተባለው።

ሌላው በአካባቢው ከፍተኛ የአሳ ርባታ ለማከናወን የሚያስችል ሁኔታ በመኖሩ፣ ግድቡ እንደተጠናቀቀ በእነዚህ ዘርፎች ላይ የሚሰሩ ስራዎች በጥናት ላይ የተመሠረቱ ለማደሰረግ ጥናቱ ተጀምሯል ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

ግድቡን ከዳር ለማድረስ አሁንም ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
አራተኛውን የግድቡን የውሃ ሙሌት ለማከናወን ዝግጅት መጀመሩንም ሰምተናል።

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos