Get Mystery Box with random crypto!

ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ክልል ስለነበሩ ከ6ሺህ በላይ ኢንዱስትሪዎች አሁን ላይ መረጃ እንደሌለዉ | Ethio Fm 107.8

ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ክልል ስለነበሩ ከ6ሺህ በላይ ኢንዱስትሪዎች አሁን ላይ መረጃ እንደሌለዉ የክልሉ ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ

በትግራይ ክልል የነበሩ 6ሺህ 4መቶ 39 ኢንዱስትሪዎች መካከል አሁን ላይ ሁሉም በአጠቃላይ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንደማይዉቅ የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቋል፡፡

የቢሮዉ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ገ/ጻድቅ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት፤ በ 2012 ዓ.ም በክልሉ 61 ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች፣ 8 መቶ 72 መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች እና 5ሺህ 506 አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ነበሩ፡፡

አሁን ላይ እነዚህ ኢንዱስትሪዎች በአጠቃላይ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ምንም የምናዉቀዉ ነገር የለም ብለዋል፡፡

ለዚህም አቶ ዳዊት ጥናት አለመደረጉን እንደምክንያት አንስተዋል፡፡

ቢሮዉ በጉዳዩ ላይ ጥናት ባለማካሄዱ መቀሌ ላይ ካሉ የተወሰኑ ኢንዱስትሪዎች በስተቀር፤ ሌሎቹ የት ደረጃ ላይ እንዳሉ አስካሁን ያወቅነዉ ነገር የለም ነዉ ያሉት፡፡

በአጠቃላይ ግን ሙሉ ለሙሉ ከወደሙ እና ከተዘጉ ኢንዱስትሪዎችባሻገር የተወሰነ ጉዳት ደርሶባቸዉ ወደ ስራ መመለስ የሚችሉ ኢንዱስትሪዎች መኖራቸዉን ተናግረዋል፡፡

ይሁንና ለእነዚህ ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ ተደርጎ ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ አሁን ያለዉ የመንግስት አሰራር አመቺ አይደለም ብለዋል፡፡

የፌደራሉ መንግስት ኢንዱስትሪዎቹ የሚያስፈልጋቸዉን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ቢያሳይም ድጋፎቹ ግን ለኢንዱስትሪዎቹ በተግባር የደረሱ አይደሉም ነዉ ያሉት፡፡


በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም


ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos