Get Mystery Box with random crypto!

የትራፊክ ህግን በመተላለፍ ከ 90 በላይ አሽከርካሪዎች ተቀጡ። በትራፊክ መብራት ላይ ልመና እ | Ethio Fm 107.8

የትራፊክ ህግን በመተላለፍ ከ 90 በላይ አሽከርካሪዎች ተቀጡ።

በትራፊክ መብራት ላይ ልመና እና ግብይትን ለመከላከል የወጣውን ህግ የተላለፉ ከ90 በላይ አሽከርካሪዎች ተቀጥተዋል።

በአዲስ አበባ በሚያዝያ ወር ብቻ በተመረጡ 20 አካባቢዎች ላይ በተደረገ ቁጥጥር በልመና ለተሰማሩ ዜጎች ገንዘብ ሲሰጡ እና ግብይት የፈፀሙ 92 አሽከርካሪዎች በመንገድ ትራፊክ ደንብ መሠረት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ብርሃኑ ኩማ ለኢትዩ ኤፍ ኤም ገልፀዋል።

ኤጀንሲው ቁጥጥር ካደረገባቸው ዋና ዋና የከተማዎ የትራፊክ መብራቶች መካከልም ፣ በሾላ ገበያ ፖሊስ መምርያ፣ ልኳንዳ 18 ማዞሪያ፣ ሰሜን ሆቴል፣ኢሚግሬሽን መብራት፣ እስጢፋኖስ መብራት ፣ ለቡ መብራት፣ ጀሞ መብራት፣ አየር ጤና መብራት፣ ሜክስኮ፣ ጦር ሀይሎች መብራት፣ ቄራ እና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው።

በትራፊክ መብራቶች፣ አደባባዮች እና አካባቢዎች ላይ የሚከናወኑ የልማና እና የግብይት ክልከላዎች የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል፣ የትራፊክ ፍሰትን ለማሳለጥ እንዲሁም ህገወጥ የመብራት ላይ ንጥቅያና ሌብነትን ለመከላከል ጭምር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ኤጀንሲው ገልፆል።

እሌኒ ግዛቸው
ግንቦት 03 ቀን 2015