Get Mystery Box with random crypto!

አንጋፋዋ ድምጻዊት ሂሩት በቀለ አረፈች፡፡ ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎ | Ethio Fm 107.8

አንጋፋዋ ድምጻዊት ሂሩት በቀለ አረፈች፡፡

ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን እንካችሁ ያለችው ድምጻዊት ሂሩት በቀለ፣ በአደረባት ህመም በሃገር ውስጥና በውጭ በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ህልፈተ-ሕይወቷ ተሰምቷል፡፡

ከ1950 መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን ያስደመጠችን ሂሩት በቀለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘማሪነት/አገልጋይነት ስራዎችን ስትስራ እንደነበር ይታወሳል፡፡
የቀድሞ ድምጻዊት ከዛም ዘማሪት ሂሩት በቀለ በተወለደች በ83 ዓመቷ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው፡፡

ሂሩት በቀለ የ7 ልጆች እናት፣የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች፡
(ታዲያስ አዲስ)
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ለቤተሰቦቿ፤ለወዳች ዘመዶቿና አድናቂዎቿ መጽናናትን ይመኛል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም