Get Mystery Box with random crypto!

ሕብረት ለበጎ የበጎ አድራጎት ድርጅት በ4 ቢሊየን ብር በለገጣፎ ሪፈራል ሆስፒታል ሊገነባ ነው፡፡ | Ethio Fm 107.8

ሕብረት ለበጎ የበጎ አድራጎት ድርጅት በ4 ቢሊየን ብር በለገጣፎ ሪፈራል ሆስፒታል ሊገነባ ነው፡፡

ሕብረት ለበጎ የበጎ አድራጎት ድርጅት በለገጣፎ የ4 ሄክታር ወይንም የ40 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተረክቦ በዛሬው ዕለት ሰኔ 01/2015 ዓ/ም የግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር አካሂዷል።

የሚገነባው ሪፈራል ሆስፒታል 4 ቢሊየን ብር እንደሚተይቅ ኢትዮ ኤፍ ኤም ከሕብረት ለበጎ የፕሮጀክት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ደጀኔ ሰምቷል።
የግንባታ ወጭውም ከህብረተሰቡ የሚሰበሰብ ስለመሆኑም ሰምተናል፡፡

ሆስፒታሉ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ለአካባቢው እና ከአጎራባች ክልሎች ለሚመጡ አገልግሎት ፈላጊዎች አገልግሉት ይሰጠል ሲሉ አቶ ሐብታሙ ተናግረዋል፡፡

ግንባታውን ለማጠናቀቅም 3 ዓመት ሊፈጅ እንደሚችል የፕሮጀክት ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ሕብረት ለበጎ ከሁለት ዓመት በፊት በለገጣፎ ከተማ አስተዳደር ቃል የተገባለትን 6 ሄክታር ወይንም 6ዐ ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ በሙሉ እንዳላገኘም ተናግሯል፡፡

2ሺህ ካሬ ሜትሩን ለአካባቢው ተጨማሪ የልማት ሥራዎች እንዲውል በመደረጉ የ 4 ሄክታር ወይንም የ40 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተረክቦ በዛሬው ዕለት የግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር አካሂዷል።

በግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ላይም የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ አርቲስቶችና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡

ሪፈራል ሆስፒታሉን ለመገንባት በሚደረገው ጥረትም መላው ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተቻላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም