Get Mystery Box with random crypto!

የወለኔ ህዝብ ተደጋጋሚ የማንነት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን የወለኔ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመ | Ethio Fm 107.8

የወለኔ ህዝብ ተደጋጋሚ የማንነት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን የወለኔ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ፈይሰል አብዱላዚዝ ተናገሩ፡፡

ለ30 ዓመታት የቆየው የወለኔ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን የወለኔ ህዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ፈይሰል አብዱላዚዝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ፓርቲያቸው ‘የወለኔ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ’ በሀገሪቱ ፖለቲካ ሰፊ ተሳትፎ ያደረገ እንዲሁም በሁሉም የሀገሪቱ ምርጫዎች ላይ የተሳተፈ ቢሆንም የህዝባቸው የማንነት ጥያቄ ግን ምላሽ ሊያገኝ አለመቻሉን አስታውቀዋል፡፡

በጉራጌ ዞን ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኘው ወለኔ የራሷ ቋንቋ፣ባህል እና ማንነት ያላት ናት የሚሉት ሊቀመንበሩ የሚቀርቡ የማንነት ጥያቄያች ሰሚ ሊያገኙ አለመቻላቸው እንቆቅልሽ ሆኖብኛል ብለዋል፡፡

በደቡብ ክልል ካሉ ስድስት የማንነት ጥያቄዎች አንዱ የሆነው የወለኔ ህዝብ የማንነት ጥያቄን በተመለከተ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ይዞት ውሳኔ እየተጠባበቁ እንደሆነም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

አቶ ፈይሰል ፓርቲያቸው እየታገለ የሚገኘው የወለኔ ህዝብ የራሱ የሆነ አስተዳደር እንዲኖረው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉዳዩን አጥንቶ በቅርቡ ውሳኔ ከሚሰጥባቸው የማንነት ጥያቄዎች አንዱ እንደሚሆንም ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ሐምሌ 13ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube

https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos