Get Mystery Box with random crypto!

ደምበል ኮሌጅ ተማሪዎቹን አስመረቀ። ኮሌጁ በቀን እና በማታ መርሃ ግብር  ያስተማራቸውን ተማሪዎ | Ethio Fm 107.8

ደምበል ኮሌጅ ተማሪዎቹን አስመረቀ።

ኮሌጁ በቀን እና በማታ መርሃ ግብር  ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል።

ደምበል ኮሌጅ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣በአውቶሞቲቨ በአካውንቲንግ ፣በነርሲንግ በፋርማሲ እና በሌሎችም መርሃ ግብር ነው ተማሪዎቹን ያስመረቀው።

በጠቅላላው 350 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል።

የኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢ እና የኮሌጁ ባለቤት የሆኑት አቶ ተሾመ በቀለ እንደተናገሩት የልፋታችሁ ውጤት ለማየት ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ኮሌጁ በቀጣይ አዳዲስ የትምህርት አይነቶችን ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል።



የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን ደመላሽ ከበደ አመታትን በድካም አሳልፋችሁ ለዛሬ ቀን ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ደምበል ኮሌጅ 2015 አመት የዲግሪ መርሃ ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል።

ደምበል ኮሌጅ የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ በየጊዜው ኮሌጁን እያስገመገመ እንደሚገኝ የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን ተናግረዋል።

ለቀጣይ የትምህርት ዘመን ምዝገባ እንደጀመረ አስታውቋል።


በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም