Get Mystery Box with random crypto!

'ችግር ፈቺ'፣ የሃሳብ ግብዓት ያስገኛል የተባለ ውይይት ለማካሄድ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን በቅርቡ | Ethio Fm 107.8

"ችግር ፈቺ"፣ የሃሳብ ግብዓት ያስገኛል የተባለ ውይይት ለማካሄድ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን በቅርቡ ከኢዜማ የለቀቁ አመራሮች እና አባላት አሳወቁ፡፡

ያልዳበረው የውስጠ -ፓርቲ የፖለቲካ ባህልና አሠራር ለተቃዋሚ ፖርቲዎች የትግል ጉዞ መዳከም ምክንያት ነው ብለዋል ስለውይይቱ ዝግጅት በተመከተ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላኩት መግለጫ፡፡

እነዚህን መሠረታዊ ከሀገራዊ ህልውና፣ ሰላምና እድገት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን ችግሮች ለመቅረፍ እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ፖለቲካ ድርጅታዊ ኃይል (ፓርቲ)፣ የፖለቲካ ባህላችንን በአፅንኦት መመልከት ፣ ጥሩውን ለመጠበቅና ለማሳደግ ኃላፊነት መውሰድ፣ መጥፎውን በመንቀስና ለችግሮቹ ሳይንሳዊ መፍትሔ በማፍለቅ የወደፊቱን መተለይም አማራጭ የሌለው ተቀዳሚ ተግባር ነው ብለዋል በመግለጫቸው።

ወቅቱ የሀገር ሰላምና ህልውናን ለማቅናት የሕዝቧን አብሮት (አንድነት) ለማስጥበቅ፤ ነባር ፖለቲካዊ ባህል በመገምገም፤ አዲስ ፖለቲካዊ ባህል ለመትከል በጋራ የምንቆምበት ወሳኝ ጊዜ ነው ሲሉም አንስተዋል።

በመሆኑም «በቅርቡ ከኢዜማ ድርጅታዊ መዋቅር የለቀቅን አመራሮች እና አባላት ፣ ከሌሎች ሀገር ወዳድ አካላት፣ ስብስብና ፣ግለሰቦች ጋር በመሆን፣ በመተባበር ለአዲስ ፖለቲካዊ ባህል ግንባታ ጠቀሜታ ባላቸው፣ ለቀጣዩ ፖለቲካዊ የትግል ጉዞ በሚያግዙ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ግምገማ፣ ውይይትና ምክክር መጀመራችንን ለማሳወቅ እንወዳለን» ብለዋል።

"ችግር ፈቺ"፣ የሃሳብ ግብዓት ያስገኛል ያሉትን ይህንን ውይይት እንዲሁም ለወቅቱ የሚመጥን፤ ተገቢውን ሰላማዊ የትግል አማራጭ ለመወሰን የሚያስችል አቅም ያጎናፅፋል የሚል እምነት እንዳላቸውም አንስተዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 13ቀን 2015 ዓ.ም