Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 44

2022-09-05 17:29:26
490 views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 17:02:16 ከጥልቅ እንቅልፍ የማይነቃው ፥ ለህዝቡ ህልውናና ጥቅም መቆም ያቃተው የአማራ ልሂቅ ጉዳይ…..! 

መንግሥት << የአማራ ህዝብ ተስፋ ቆርጦብናል! >> የሚል ግምገማ አለው፡፡ አሸባሪው ትህነግ ደግሞ << ከአማራ ጋር በ83ቱ መንገድ ካልሆነ በስተቀር አይደለም ጦርነት ማሸነፍ ለህልውናችንም ያሰጋናል! >> የሚል ሰሞንኛ የግምገማ ነጥብ ላይ ደርሷል፡፡ 

ባለፈው በድርድሩ ሂደት ወቅት ደግሞ <<  አማራው በህወሓት ወረራም ሆነ በአገዛዝ ዘመኑ ከደረሰበት ውድመትና በደል ብሎም  በመንግሥት አስተዳደር ላይ ተስፋ እየቆረጠ በመምጣቱ በድርድሩ ስለማይስማማ  ፥ በህወሓት ዙሪያ የማይናወጥና ተመሳሳይ የባላንጣነት ስሜት ካላት ኤርትራ ጋር ሆኖ ሊሠለፍ ይችላል! ይህም ስልጣናችንን ወደሚያሳጣ የሀይል አሰላለፍ ሊያስገባው ይችላል፡፡>> የሚል ግምገማ ይዘው ሲንቀሳቀሱ ነበር፡፡

በነገራችን ላይ እቅዳቸው ባይሳካም ፥ በህዝብ ጥቅምና ፍላጎት እንዲሁም በትህነግ ባላንጣነት ዙሪያ ፅኑ አቋም ያላቸው ብሎም ህዝቡን የማደራጀት ተሰሚነት አላቸው የተባሉ በርካታ የአማራ ፖለቲከኞችንና የጦር መሪዎች ተመርጠው   " ከኤርትራ/ ከውጭ ሀይሎች ጋር በመሆን መፈንቅለ-መንግስት ለማድረግ በማሴር" የሚል ዲሪቶ ክስ በማዘጋጀት ወደወህኒ የማውረድ እንቅስቃሴ  ተጀምሮ የነበረው ብሎም ከአዲስአበባ ኤርትራውያንን እየታደኑ እንዲታሰሩ የማድረጉ ሂደት ፥ ...ወዘተ ከዚህ ግምገማ በኃላ የመጡ ናቸው፡፡ 

በጥራቃው ጠቅላይ ሚኒስቴር " ..ህወሓት ጋር ነገሮችን በድርድር ከፈታን ኤርትራን በጋራ ሆነን እንገጥማለን፡፡  .. አማራውን ነጥለን የአሰብን  ስም እየጠራን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ባንዲራ እያሳየን ከጎናችን  እናሰልፈዋለን! >> እስከማለት የደረሰ የአፍ ወለምታ ውስጥም ገብቶ ሲዳክር እንደነበር  ፥ ሾካኮቹ ሲያንሿክኩ ጭምጭምታዎችን ሰምተን "ጉድድድ..!" ብለን አልፈናል፡፡ ከሰሞኑ የአሸባሪው ትህነግ አፈቀላጤ ጌታቸው ረዳ ፥ ሰአት ጠብቆና "ከረንትሊ ይጠቅመናል!"  በሚል ስሌት ፥ ይህን ጉዳይ በአደባባይ ሲያነሳው  ፥ ብዙዎቹ "የኤርትራን ከመንግሥት ጋር የመተባበር ሂደት ለማዳከም የታለመ ፖለቲካዊ ቀደዳ ነው " ሲሉ  ፤ እኔ ግን ያረጋገጥኩበት ቀድሜ የነበረኝን መረጃ እውነተኛነትና ጉዳዩ ከሹክሹክታም አልፎ ወደጠረጴዛ የደረሰ አጀንዳ  መሆኑን  ነበር ፡፡ 

በነገሬ ላይ ኤርትራ እስከአለም ፍፃሜ ድረስ ብቻዋን እንኳ ብትቀር ህወሓት የተባለውን አሸባሪ ቡድን ከመፋለምና ከመታገል ወደኃላ የማያስብል ፅኑ አቋም አላት! ህወሓትን መታገል የዘላቂ ሰላምና ህልውና ጉዳይ መሆኑን አምነው የቆሙ ናቸው፡፡

ወደነጥቤ ስገባ በግራም ሆነ በቀኝ የአማራ ህዝብ በድርድሩም ሆነ በጦርነቱ አማራጭ ውስጥ ፥ የትኩረትና የስበት ማዕከል ሆኖ ከጀርባ እየተዶለተበት ያለ ህዝብ ነው፡፡ 

አሁንም ምስጢራዊ ድርድሮች በጓሮ በር እየተደረጉ እንደሆነ ሚስጥራዊ የመረጃ ምንጮች እያንሿከኩ ይገኛሉ፡፡ 

ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ የመንግሥት ባለሟሎች ዛሬ ድንገት ተነስተው ፥ "ህወሓት በአማራ ህዝብ ላይ ያደረሰውን በደል የሚያሳይ ጥናት ይፋ አደረግን " ብለው የሚደልቁትም ይቺን ስጋትና የቢሆን ግምገማ ያጣፉ መስሏቸው እንጂ ፥ የአማራ ህዝብ ስራአታዊና መዋቅራዊ መከራ የሚጀምረው "ህገ-መንግስት" ከተሰኘው የሀገር ማፍረሻ ውል መሆኑን አምነውና ደፍረው እንኳ የማይናገሩ መሆናቸው የአደባባይ ሀቅ መሆኑ ሳይታወቅ ቀርቶ አይደለም፡፡ በጥናቱ ከህወሓት ባሻገር ብልፅግና የፈፀመው ግፍስ ተካቶ ይሆንን?

ከዚህ አንፃር የአማራ የፖለቲካ ልሂቅ ፥ በሁለት ጠላቶች የጥቅምና የፍላጎት ማርኪያ የትኩረት ነጥብ ለሆነው ህዝባቸውና ቀጣይ ስለተዶነበት ፈርጀ ብዙ የሆነ አደጋ ፥ የቢሆን ትንተና ሰርተው ህዝባቸውን ከጠላት ከፋፋይ አጀንዳ በመጠበቅ በህብረት ለህልውናው እንዲታገል ያለእረፍት መትጋት አልነበረባቸውምን ?

ምን ይሻላል ግን ?
1.3K viewsedited  14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 16:29:40
3.1K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 16:29:34 ግራም ነፈሰ ቀኝ ችግሮቻችን የሚፈቱት በንቁ ህዝባዊ ተሳትፎ በሚገነቡ ጠንካራ ተቋማት ብቻ ነው!

" ወጣቶቻችን ይህን ለትልቅ አላማ ለመሠለፍ የቀረበን ትልቅ እድል ተጠቀሙበት! "

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለሀገርና ለህዝብ ህልውና በሚደረገው ጦርነት ምን ያህል ዋጋ እየከፈለ እንደሚገኝ የዳር ተመልካች ሆኖ መረዳት ሊከብድ ስለሚችል በአውደ ውጊያው አካባቢ ጠጋ ብሎ ያለውን እውነትና የገዘፈውን መስዋዕትነት መመልከት ይቻላል፡፡

ይህ ተቋም የሁላችንም ይሆን ዘንድ የሁላችንም ተሳትፎና እገዛ እንደሚያሻው አስረጂና ነጋሪ አያሻውም፡፡

በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሰራዊት መስፈርቱን ለሚያሟሉና የዚህ ትልቅ አላማ የመሠለፍን እድል ለሚሹ ሁሉ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ተከታዩን የአባልነት ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል!



የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከነሐሴ 26/ 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ መስፈርቱን የሚያሟሉ ወጣቶችን መልምሎ በመደበኛ ሰራዊትና በእጩ መኮነንነት በማሰልጠን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል ማድርግ ይፈልጋል ፤

የመመልመያ መስፈርቶች ፦

1) ከአሁን በፊት የፖሊስ ወይም የመከላከያ አባል ያልነበረ/ች

2) ከወንጀል ነፃ የሆነ የፍርድ ቤት ቀጠሮና ክርክር የሌለበት/ባት

3) ከማንኛውም ሱስና አጉል ልማድ የፀዳ/ች እና ሙሉ ጤንነት ያለው/ያላት

4) በመከላከያ ለ7 ዓመት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች በማንኛውም ቦታ ተመድቦ መስራት የሚችል/የምትችል

5) ፆታ፡- አይለይም

6) ኢትዮጵያዊ የሆነ/ች በሚኖርበት ቀበሌ 2 ዓመት የኖረ/ች

7) ዕድሜ፡- ከ18-25 አመት ፤ ቁመት ለወንድ 1.60 እና ከዚያ በላይ ፣ ለሴት ደግሞ 1.55 እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች

8)ክብደት፡-ለወንድ ከ50-75 ኪ.ግ የሆነ ለሴት ደግሞ 45-66 ኪሎግራም የሆነች፣

9) የትምህርት ማስረጃ፦ ለወንድ 6ኛ ክፍል ያጠናቀቀ እና ለሴት እወቅና ካለው የትምህርት ተቋም ዲፕሎማ ወይም በሌቭል ያጠናቀቁ እና ከዚያ በላይ የሆኑ የ 8ኛ ክፍል የሚኒስቲሪ ካርድ ማቅርብ የሚችሉ ፣

10) ያላገባ/ችና ያልወለደ/ች

11) ደመወዝ በመከላከያ ስኬል መሰረት ሆኖ ጥቅማጥቅም የመኖሪያ ቤትና ህክምና አገልግሎት በነፃ የሚያገኙ ሲሆን በመከላከያ ዕቅድና ፍላጎት መሰረት በትምህርት ተቋም ገብተው የመማር ዕድል አላቸው፣

12) የምዝገባ ቦታ ፦ በሁሉም የክልል ከተሞች የፀጥታ ተቋማት ቢሮ( ሚሊሻ ፤ ፖሊስ ፤ ሰላምና ደህንነት ቢሮዎች )

13) የምዝገባ ቀን፡- ከነሐሴ 26/2014 ዓ/ም ጀምሮ አስከ መስከረም 10/2015 ዓ/ም ዘወትር በሥራ ስዓት እንዲሁም ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ

ማሳሰቢያ፡- በምዝገባ ወቅት መቅረብ የሚገባቸው ማስረጃዎች የቀበሌና የፖሊስ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የትምህርት ማስረጃ ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የቀበሌ መታወቂያ በዘመኑ የታደሰ ያስፈልጋል።

ወጣቶቻችን ይህን ለትልቅ አላማ ለመሠለፍ የቀረበን ትልቅ እድል ተጠቀሙበት!
3.7K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 12:00:48 መረጃ ፋኖ!

ግንባር ላይ እየተፋለሙ ያሉት የምስራቅ አማራ ፋኖዎች የቁስለኛ ማሳረፊያና የሎጂስቲክ ካምፓቸውን በፀጥታ አካላት እንዲለቁ ተጠየቁ!

በሀይቅ ከተማ የሚገኘው የምስራቅ አማራ ፋኖ ከዚህ በፊት የአውራጎዳናና የቱርክ የባቡር ፕሮጀክት ካምፕ የነበረን ቦታ ለሎጂስቲክ ማከማቻ ፣ ለቁስለኛና አዲስ ምልምል ሰልጣኞች ማረፊያ ሲገለገልበት የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የትህነግ ወረራ ገና ሳይቆም የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎችና አመራሮች ካምፑን እንዲለቁ በተለያዩ ጊዜያት ጫና ሲፈጥሩ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሠአት ጦሩ ሙሉ በሙሉ ግንባር ተሰልፎ መሪር የሆነ ዋጋን እየከፈለ በሚገኝበት ወቅት ፥ የተለያዩ ተተኳሾች የተቀመጠበትንና በዚህ ሳምንት ብቻ በውጊያ ላይ ቆስለው እያገገሙ ያሉበትን ካምፕ ፥ በዛሬው እለት ከመንግሥት የበላይ አመራሮች ተላክን የሚሉ የታጠቁ አካላት "የስደተኞች ማረፊያ ልናረገው ነውና ለቃችሁ ውጡ! " በማለት አስነዋሪ ተግባር መፈፀማቸው ተገልፇል፡፡

እኚህን ለህዝባቸው ክብር ሲፋለሙ በዚህ ሳምንት እንኳ በርካታ ጀግኖችን የገበሩ ፥ የደሙና የቆሰሉ ፋኖዎችን ማክበር ፣ መደገፍና ማመስገኑ ቢቀር ከስር ከስር እየተከታተሉ ይህን አይነት አሳፋሪና የነቀዘ ተግባር መፈፀማቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው በዝምታ ሊታለፍ የማይገባው ጉዳይ ነው፡፡

ይህ ጉዳይ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጭምር የደረሰ ሲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ "ይሄን ያዘዘውን አካል እናጣራለን! ተገቢም አይደለም!" ሲሉ መግለፃቸው ታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለም በኮምቦልቻ ከተማ በሚገኘው ካምፕ የሚገኙት እጅግ በርካታ ፋኞዎች ወደግንባር ለመዝመት ሙሉ ዝግጅት አድርገው ከሳምንት በላይ የመንግሥት አካላትን ቢጠይቁም "ፈቃድ አንሰጣችሁም" ተብለው ጦራቸው እየተጉላላ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
1.6K views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:24:39 ትህነግ ወያኔ ከፍተኛ የሆነውን የሚካናይዝድ አቅሙን የሚጠቀመው ወልቃይት ላይ መሆኑን ቀደም ብሎ ከመገናኛ ሬዲዮናቸው የተገኘው መረጃ አረጋግጧል! ህዝባዊ ሰራዊቱም በቂ መረጃና ዝግጅት ስለነበረው በጉጉት የሚጠብቀው እስኪተነኩሱት ነበር! እየቀመሱ ነው!

በሰቆጣ አበርገሌ ቀድሞ አሸባሪው ይዟቸው የነበሩ ሁለት ወታደራዊ ቦታዎችን የወገን ጦር ከመቅፅበት ላፍ አርጓቸዋል! ወያኔ አሁን ከጀርባ ፣ ከፊት ፣ ከጎን ፣ ....እሳቱን ለኩሶ በሚገባ ሳንድዊሽ ሆኖ እየተጠበሰ ነው!

ይህ ሁሉ ግን በአንድ መቋጠሪያ ሊታሰር ይገባል!

መቋጠሪያውም "ድል!" ብቻ ነው! win the War rather than the little battle!

ታሪክ የሚፃፈው በአሸናፊ እጆች ብቻ ነው!

ለዚህ ደግሞ እያንዳንዳችን ሀላፊነትና ግዴታችንን መወጣት አለብን!
3.7K views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:34:18 ፋኖ የራሱን ወታደራዊ መረጃ ፥ በአደረጃጀቱ የመረጃና የፕሮፓጋንዳ ክፍል ብቻ እንዲተላለፍ የሚያደርግ ጥብቅ አሰራርን መከተል አለበት!

በተደጋጋሚ የፋኖ አመራሮችን ሳገኝ የማቀርበው ምክረ-ሀሳብ ይህንን መሠል ተቋማዊ አሰራር ማጎልበትን ቅድሚያ ሰጥተው እንዲሰሩበት ነው! ዛሬም ጥቂት ወንድሞችን በነበረን ቆይታ ሳሳስብ የነበረው ይህንኑ ነው!

በተግባር እሳት ላይ ተጥደው ከሰራዊቱ ጋር የሚፋለሙ ፋኖዎች ፥ ስለአውደ-ውጊያ ውሎዎቻቸውም ሆነ አጠቃላይ እንቅስቃሴአቸው ሳንሱር የተደረገ ብሎም ጥቅምና ጉዳቱ ተመጥኖ ይፋ የሚደረግ ተቋማዊ የመረጃና የፕሮፓጋንዳ ስርአት ማበጀት አለባቸው!

ጦርነት 80% የሚሆነው የመረጃና የፕሮፓጋንዳ ስራ ነው፡፡ በጥቂት የተሳሳተ መረጃ ትልቅ ዋጋ ይከፈላል፡፡ በትንሽ ወሬ ጦር ይፈርሳል፡፡ በተሳሳተ መረጃ ለጠላት ምቹ አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ አንድምታው ያልተገመገመ የመረጃ ፍሰት ጦርን ከጦር ፥ ጓድን ከጓድ ሁሉ እስከማጋጨት ሊጓዝ ይችላል፡፡

በመሆኑም የምስራቅ አማራም በሉት የወሎ ፋኖ ሁሉም የአንድ አላማ ዘማቾች ፥ የአንድ ህዝብ ልጆችና የአንድ አፈር አፈሮች ናቸውና በመረጃና በፕሮፓጋንዳ ረገድ የሚስተዋሉባቸውን ችግሮች ከላይ በገለፅኩት መሠረት በሀላፊነትና በጥንቃቄ ሊመሩት ይገባል፡፡

ከአደረጃጀቱ እውቅና ውጭ ፥ በድጋፍ ስምም ሆነ በተለያዩ መንገዶች ወደግንባር ዘልቀው ያዩትን የፎቶግራፍ ፣ የድምፅ ፣ የቪዲዮና መሠል መረጃዎችን ፥ ያለይሁንታ በማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በተለያዩ መንገዶች የሚያስተላልፉና የሚያሰራጩ አካላትን መከታተልና ቁጥጥር ማድረግ ይገባል! የድርጊቱ ፈፃሚዎችም አላማችን ከህዝብና ከትግሉ ጎን ሆነን በጎ አስተዋጽኦ ማድረግ ከሆነ ሀላፊነት ሊሰማን ይገባል!

የተለያዩ የዩቱብና መሠል ሚዲያዎችም ከፋኖ አደረጃጀት የዘርፉ ክፍል ወይም አመራር ውጪ ባገኛችሁት አጋጣሚ ማንኛውንም የፋኖ አባል ወይም አመራር ፥ ለፖለቲከኛ የሚቀርብን ጥያቄ ጭምር እየጠየቃችሁ በሚዲያ ሲሰራጩ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያስከትሉ ብሎም ለትርጉም የተጋለጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንድትቆጠቡና ሀላፊነት እንዲሰማችሁ ለማሳሰብ እወዳለሁ!

ድል ለሀገርና ለህዝብ ክብር በጀግንነት እየተፋለሙ ላሉት ህዝባዊ ሠራዊቶቻችን ይሁን!
4.4K views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:32:36
መሬት ያለው አሁናዊው እውነታ ይህ በጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ የቀረበው መረጃ ብቻ ነው!

<< ሕወሓት በራያ ግንባር ጦርነት ከጀመረበት ዕለት ጀምሮ ከፋኖዎች ጋር በምሽግ ውስጥ ነበረኩ ። ጦርነቱ በየደቂቃው ተለዋዋጭ በመሆኑ አንድ የጠራ ምስል እስካገኝ ድረስ ከመፃፍ ታቅቤ ቆይቻለሁ። >>

" ፋኖ ፣ መከላከያ ፣ የአማራ ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ ከራማ ኪዳነ ምህረት እስከ ጎብዬ ፣ በላጎ እና ቃሊም ድረስ የሞት ሽረት ውጊያ እያደረገ ነው። "

"ይሁን እንጅ አሁን በዚህ ሰአት የሕወሓት ታጣቂ ቡድን የተወሰነው ሾልኮ ከጎብዬ በእስከ ዱቡብ ምዕራብ በኩል ዱርለበስ በሚባለው አካባቢ የአላውሃን ወንዝ ለመሻገር እየተንደረደረ ነው። ይህ አቅጣጫ በማመጫ ድጎ እየሱስ አድርጎ ወደ ወልዲያ የሚያስገባውን ዋሻው ለመዝጋት ነው። "

" ጥምር ጦሩ ዋሻውን ቀድሞ ቢይዝ ወልዲያን ማዳን ይቻላል የሚል መልዕክት አለኝ። ባሳለፍነው አመትም የሕወሓት ቡድን ይህንኑ መስመር ተከትሎ ወልዲያ መግባቱ የሚታወስ ነው። "

"አማራ ብቻ ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕወሓት ሕዝባዊ ሆኖ እንደመጣው ሁሉ ሕዝባዊ ሆኖ ካልተነሳ በስተቀር አንድ ቀን ጧት በራችንን ስንከፍት ደጃፋችን ላይ እናገኛቸዋለን።"

ነቅተህ ፥ አንቃ! በትናትናው መንገድ ተጉዞ ድጋሜ መውደቁ ይብቃ!
5.3K views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:48:12 አንዳንድ ነገሮችን ለማስታወስ ያህል!

#በደም_ነጋዴነትን_እንታገለዋለን

ሁሉ ነገር ገደብ አለው፡፡ ገደብ ያለፉና ለተለያዩ ችግሮች የሚዳርጉንን አካላት ግን ከእንግዲህ መታገስ አያሻም!

ማንም ሰው የሚታገለው በቅድሚያ ለራሱ ሲል ነው፡፡ ሲቀጥል እንደማህበረሰብ የተጋረጠብንን አደጋ ለመቀልበስ ፣ የምንጠይቀውን የፍትህና የእኩልነት ጥያቄ ለማስመለስ ነው፡፡ ለራሱ ዛሬ ፣ ለትውልዱ ነገ አስቦ ዛሬ ላይ የሚታገል በጊዜ የነቃ ሙሉ ሠው ነው!

በዚህም መሠረት ሁሉም በየመክሊቱና በተሰማራበት መስክ ሁሉ የህዝብን ትግል ማገዝና መደገፍ ይችላል ፤ አለበትም፡፡ ፡፡ ለዚህ ተግባሩ ክፍያው ነፃነት ፣ ሰላም ፣ ፍትህና እኩልነት እንጂ የተለየ ነገር ሊሆን አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ ሁላችንም በቻልነውና የመጨረሻ አቅማችን እስከሚችለው ድረስ የሚጠበቅብንን አበርክተናል እናበረክታለንም፡፡

ነገርግን የህዝብን ትግል መነገጃና ግላዊ ፍላጎትን ማሟያ ማድረግ ከእንግዲህ ሊገታ ይገባዋል፡፡ በሜካፕ አርቲስት ታጅበው የመሸቀያ ፎቶ ለመነሳትና በተግባር ያልተገለፀ ርካሽ ውዳሴ ለማጋበስ ግንባር ድረስ በመዝለቅ የሚተጉ "ፎር ስታር ፋኖዎችን" ከእንግዲህ በቃችሁ ማለት መልመድ አለብን! በብዙ ጉድ ችለን ፀጥ ያልነው "መጓተቱ አይበጅም” ብለን መሆኑንም ሊታወቅ ይገባል!

በተለያዩ ሀገራት ያላችሁ ወገኖቻችንም ፥ በቅንነትና ትግሉን የደገፋችሁ እየመሠላችሁ ፥ አደረጃጀትን ከመደገፍ ይልቅ ሬንጀርና ጦርሲ ለብሶ ከንፈሩ ላይ ኮቾሮ ጣል አርጎ ሰልፊ የለቀቀውን ሁሉ "ለመሳሪያ መግዣ ፥ ለስንቅና ትጥቅ ፣ ….ወዘተ" በሚል ማታለያቸው ረብጣ ገንዘብ እየላካችሁ ወንድሞቻችን እርስበርስ ሲጠራጠሩ ፣ ግጭቶች ሲፈጠሩ ፥ አደረጃጀቶች ለመከፋፈል ሲዳረጉ ብሎም በተግባር ውድ ዋጋን የከፈሉት አስበውት የማያውቁትን እንዲያስቡና ሞራላዊ ተፅዕኖ እንዲያርፍባቸው ሲሆኑ አይተናል!

በመሆኑም በዚህ ረገድ የሚስተዋሉ ትግሉን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚጎዱና ነጋዴዎችን ከሚያበዙ ተግባራት መታቀብ ያስፈልጋል!

ፋኖን መደገፍ ከፈለክ በአደረጃጀቱ ይፋዊ የድጋፍ ማእቀፍ በቀጥታ ደግፍ! ሌላውንም ሀይል በተመሳሳይ እንዲሁ በህጋዊና በይፋዊ የድጋፍ ማዕከላት ደግፍ! አደራ/አማና ሰጥተህ ከሆነም ፥ ድጋፍህ ለታለመለት አላማ መድረሱን አረጋግጥ! ከዚያ ውጭ በተዋኒያን እውናዊውን ትግል እንደምትጎዳው መረዳት ያስፈልጋል!

ይታሰብበት!
5.8K viewsedited  15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:51:33 አሸባሪው ትህነግ/ህወሓት አመሻሹን በራያ ግንባር በኩል ጦሩን አስጠግቶ ምሽጎችን ሲይዝ አምሽቷል! እየተካሄደ ያለው ከሰሞንኛው ትንሽ ለየት ያለ እንቅስቃሴ ነው!

ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት በኤርትራና በሌሎች አንዳንድ አካባቢዎች የማጥቃት ሙከራዎችን አድርጎ የከሸፈበት ትህነግ ፥ ትኩረት ለመሳብና ውጥረት ለመፍጠር ከሚያደርጋቸው መሰል ሙከራዎች ባሻገር "ወደሙሉ ጦርነት ይገባል ወይስ አይገባም" የሚለው ጥያቄም በቀጣይ ቀናት የሚመለስ ይመስለኛል!

እንደሚታወቀው ህወሓት በኤርትራ በኩል ያለውን ጨምሮ በ5 የተለያዩ ግንባሮች ጦርነት ለመክፈት እየተዘጋጀ ሠንብቷል!
5.6K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ