Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 45

2022-08-19 00:11:41 ፌዴሬሽኑ ውሃ የማያነሳ ተራ ሰበብ መደረቱ ለምን አስፈለገው?

ፌዴሬሽኑ ጎንደር ጉባኤውን ለማስተናገድ ሰፊ ዝግጅት አድርጋ ባጠናቀቀችበትና ይህንኑም ራሳቸው አይተው ባደነቁበት ማግስት ፥ ጉባኤውን ወደአዲስአበባ እንዲደረግ ከወሰነበት ምክንያት መካከል  ፦

<< ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጠቅላላ ጉባኤ ስራ ወደሚያከናውኑ ሰራተኞች ስልክ በመደወል ከክልሉ ክለቦች የተላኩ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ወኪሎችን ስሞች መቀየር አለባቸው ይህንን ካላደረጋችሁ  በማለት በማስፈራራት ጭምር ጉባኤውን እንዲስተጓጎል እንደሚያደርጉ ስሜታቸውን መግለፃቸው ኮሚቴው ባደረገው ማጣራት አጋግጧል! >> የሚል "የናቴ መቀነት አደናቀፈኝ!" አይነት ውሃ የማያነሳ ምክንያት ነው!

ግለሰቡ ይህንን ተግባር ፈፀሙ ቢባል እንኳ ፥ በመረጃና በማስረጃ በህግ ጭምር መጠየቅ ብሎም ከክልሉ አመራሮች ጋር በግልፅ ተነጋግሮ ማስተካከል እየተቻለ "እቃቃ ፈረሰ ፥ ...!" አይነት የልጆች ጨዋታ መጫወቱ ፥ ከአንድ ግዙፍና ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት የፀዳ ነው ተብሎ ከሚታሰብ ብሄራዊ ተቋም የማይጠበቅ አሳፋሪ ድርጊት ነው!

የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተፈሪ ካሳ የሚባሉ ግለሰብ ይመስሉኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ማብራሪያ እንደሚሠጡበት ይጠበቃል!

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በባህርዳር ሊያካሂደው የነበረውን ጠቅላላ ጉባኤ በተመሳሳይ መሰረዙ የሚታወስ ነው!
8.9K views21:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 22:36:38
7.1K views19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 22:36:23 በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተፈፀመው ነውር ፥ በእግር ኳስ ፌዴሬሽንም ተደገመ!

ተከታዩ ፅሁፍ የጌታቸው ሽፈራው ነው!


የጎንደር ሆቴሎች ለጠቅላላ ጉባኤ ሲባል የሰርግ ፕሮግራም ሳይቀር እንዲራዘም አድርገዋል!

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ነሃሴ 21 እና ነሃሴ 22 በጎንደር ጠቅላላ ጉባኤውን ለማድረግ ወስኖ ነበር። በዚህ ውሳኔ መሰረት የጎንደር ሆቴሎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚመጡ እንግዶችን በደንብ ለማስተናገድ ሲባል የሰርግ ፕሮግራሞች እንኳን እንዲራዘም አድርገዋል። በኮሮና እና ሌሎች ምክንያቶች ችግር ላይ የከረመው የሆቴሉ ኢንዱስትሪ ከመላ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ብለው ላሰቧቸው እንግዶች ከፍተኛ ዝግጅት አድርገው፣ ፌደሬሽኑ ወኪሎችን ልኮ ዝግጅታቸውን አድንቆ ተመልሷል። ከሰርግ ባሻገር ያሏቸውን ፕሮግራሞች ሰርዘው ሙሉ ዝግጅታቸውን ለፌደሬሽኑ ስብሰባ አድርገው ነበር።

ይሁንና ፌደሬሽኑ በሰበብ ስብሰባውን ቀይሬዋለሁ ብሏል። ይህ የመጀመርያ አይደለም። ከአሁን በፊት የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ስብሰባም ከባሕርዳር ወደ ሌላ ቦታ እንዲታጠፍ ተደርጓል። ይህ ንቀት እንጅ ምንም ሊባል አይችልም። በርካታ ሆቴሎች ለዝግጅት ወጭ ካደረጉ በኋላ መሰል ተግባራት ሕዝብን ከመናቅ የመጡ ናቸው።

ሰበብ ብለው ያስቀመጡት የአማራ ክልል አመራሮች አስፈራርተውናል የሚል ነው። ይህ ተራ ምክንያት እንጅ አሳማኝ ሊሆን አይችልም። የመጀመርያ ነገር የክልል ተወካዮች የፌደራል ተቋማቱን እያስፈራሩ ውሳኔ የሚያስቀይሩበት አካሄድ የተለመደ አይደለም። ሁለተኛው የሚሰበሰቡት ሆቴል እንጅ ጫካ ውስጥ አይደለም። ይሁንና ፌደሬሽኑ አማራ ክልል ላይ መሰል ጋጠወጥነት ያለ በማስመሰል የስም ማጥፋት ጭምር ነው በደብዳቤው ያስተላለፈው።

ይህ ተቋማዊ የነውር ፣ የጥላቻና የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው!
6.8K views19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 19:57:07
4.4K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 19:57:04 ፍትህ የተዛነፈባቸው ፋኖዎች የርሃብ አድማ ከጀመሩ 2ተኛ ቀናቸው ነው!

መቼም እየሆኑ ያሉት ነገሮች ለሞራልም ለህሊናም ተቃራኒ ናቸው፡፡ ህወሓት ወረራ ሲፈፅም አይደለም ለህዝብና ስለህዝብ የቆመውን ፋኖ ይቅርና ፥ ፍርድ ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት ከሚገኙት ጀምሮ "ሽፍታ" ተብለው በጫካ እስከሚታደኑት ድረስ " የነፍስ ድረሱልን!" ተብለው ወደጦር ግንባር ዘምተው ለሀገራቸውና ለህዝባቸው የደምና የአጥንት ዋጋን እንዲከፍሉ ተደርጓል፡፡

ጦርነቱ ቀዝቀዝ ሲል ግን የሆነውና እየሆነ ያለው ለህሊናም ለሞራልም ተቃራኒ የሆነ ክህደት የሚመስል ተግባር ነው፡፡

ከነዚህ የመንግስታዊ ነውር ሰለባዎች መካከል ደግሞ የአማራን ፋኖ በአንድ ህዝባዊ አደረጃጀት ስር በሀላፊነትና በተጠያቂነት መንፈስ እንዲመራ ሲጥሩ በነበረበት ለመንግስታዊ አፈና የተዳረጉት ወደ13 የሚሆኑ "የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አመራሮች" ተጠቃሽ ነው፡፡

እነዚህ ወንድሞቻችን ለረዥም ጊዜ በእስር ከቆዩ በኃላ የክልሉ ፍርድ ቤት ሀምሌ 22 በዋለው ችሎት ለእያንዳንዳቸው የ25 ሺህ ብር ዋስትና አስይዘው እንዲወጡ የወሰነ ቢሆንም ፥ ይህንኑ ተፈፃሚ አድርገው ከእስር ለመውጣት ሲሞክሩ ፥ የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶችን ስልጣንና ውሳኔ በተደጋጋሚ በሀይል እየሻረ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ "አሻፈረኝ” በማለት ከታሰሩበት ሳባታሚት ማረሚያ ቤት ድረስ በመምጣት እንዳይለቀቁ አድርጎ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

ፍትህ የተጓደለባቸው እኚህ ወንድሞቻችን ሌላው ቢቀር "የክልሉ ፍርድ ቤት ውሳኔ ይከበር! ፍትህ ይሰጠን!" ሲሉ ከትናንት ጀምረው የረሃብ አድማ በማድረግ ላይ ናቸው ።

የክልሉ የፍትህ ተቋማት ግን እንዴት ይሄን በተደጋጋሚ የሚፈፀም ነውርና ውሳኔአቸውን በሀይል የመሻር አንባገነናዊ ጣልቃገብነት በዝምታ አለፉት ?

የፍርድ ቤት ውሳኔ ይከበር! ለወንድሞቻችን ፍትህ ይሰጣቸው!
4.5K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 18:11:58 የኦሮሞ ፖለቲከኞች ስለሰብአዊነት ፣ ስለፍትህና እኩልነት የመናገር ፣ የመዳኘትና የማማከር የሞራል ልእልናው የላቸውም!

ቫቲካን 825 ዜጎች ያሏት በአለም በህዝብ ቁጥርም ሆነ በቆዳ ስፋቷ የመጨረሻ ትንሿ ሀገር ነች፡፡ አስረኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ዶሚኒካ ሪፐብሊክ እንኳ የህዝብ ቁጥሯ 71,890 ብቻ ነው፡፡

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ብቻ በትንሹ ወደ 10 ሚሊየን የሚገመቱ አማራዎች ይኖራሉ፡፡ በአንዳንድ ዞኖችና ወረዳዎች እንደውም አብላጫውን ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚኖሩት አማራዎች ናቸው፡፡

እነዚህ ለአስርት አመታት ጫካ መንጥረው ፣ መንደር መስርተው ፥ አርሰው አምርተው ፣ ወልደው ከብደውና ሀብት አፍርተው ለሀገር ግንባታ የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እያበረከቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፥ አይደለም ማንነታቸውን ጠብቀው ፣ ባህልና ወጋቸውን እያበለፀጉ ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብት ሊያገኙ ይቅርና የመምረጥና የመመረጥ መብት የሌላቸው ከቁጥር የዘለለ ትርጉም ያልተሰጣቸው ዜጎች ናቸው፡፡

ባለፉት አራት አመታት ያለእረፍት በተፈፀመባቸው የዘር ፍጅት በአስርት ሺዎች አልቀዋል ፣ ሚሊየኖች ሀብት ንብረታቸውን ጥለው በገዛ ሀገራቸው ስደተኛ ሆነዋል፡፡ ኢትዮጵያን በሀገር ውስጥ ፍልሰት አንደኛ ያስባላትም ይሄው የአማራዎች ፍልሰት (ስደት) ነው፡፡

"የኦሮሞ ልሂቃን ተኮትኩተው ያደጉበት የሀሰተኛ ጥላቻ ትርክት ፍፁም ጨካኝና ህሊና ቢስ አድርጓቸዋል" የምለውም ለዚህ ነው፡፡

ያ ሁሉ ህዝብ (አብዛኛዎቹ የወሎ አማራዎች) ከቁጥር የዘለለ ትርጉም አጥተው የግፍና የሰቆቃ ዶፍ እየዘነበባቸው የሚኖርበት ክልል ውስጥ ሆነው ፥ "ወሎ ኬኛ ፣ ወሎ ክልል ይሁን! …ወዘተ" የሚል ሼም አልባ ፖለቲካ ሲዘውሩ ሳይ አፍራለሁ፡፡ እሸማቀቃለሁ!

አማራ ክልል ከማንኛውም የሀገሪቱ ክልሎች ቀድሞ የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብት ያረጋገጠ "የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት" አክብሮ የልዩ ዞንና ወረዳን እውቅና የሠጠ ብቸኛው ክልል ነው! ነገርግን ይህ የክልሉ መልካም ተግባር የሚስተዋለው ሲያስመሰግነው ሳይሆን ፖለቲካዊ እሳት በየጊዜው እንዲቀጣጠል ሲያደርግበት ነው!

እስኪ! ኦሮሚያ ክልል ውስጥ አይደለም ልዩ ዞን አንድ እንኳ ለነዋሪዎቹ የዜግነት መብት የተፈቀደበት የልዩ ወረዳ ሊጠቅስልኝ የሚችል ሠው አለን ? በፍፁም! ጥያቄውን ማንሳት ራሱ የሚያስቀስፍበት ምድራዊ ገሀነም ነው!

አዎ! ኦሮሚያ ክልል ያን ሁሉ ሚሊየን ህዝብ የፖለቲካ መያዣ አደድርገው ፥ በገዛ ሀገሩ " እንፈጀዋለን ፣ እናባርረዋለን ፣ እናፈናቅለዋለን!" በማለት እኩይ ፖለቲካዊ ፍላጎታቸውን ለማስፈፀም የሚተጉ ህሊና ቢስና ጨካኝ ፖለቲከኞች የሚዘውሩት ክልል ነው!

" የፊንፊኔ ልዩ ዞን" የሚባል የነዋሪዎቹን ይሁንታ ሳያገኙና የራስን እድል በራስ የመወሰን መብታቸው ሳይከበር ፥ በቤተ-ዘመድ ተመካክረው ሲመሰርቱ ፥ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እንደሰው እንኳ የመከበር ሰብአዊ መብት ስለተነፈጉት አማራዎችና ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ማስታወስ አይፈልጉም፡፡ ስታነሳባቸውም ይነዝራቸዋል፡፡

እውነት እውነት እላችኃለሁ…….!

የኦሮሞ ፖለቲከኞች ስለሰብአዊነት ፣ ስለፍትህና እኩልነት የመናገር ፣ የመዳኘትና የማማከር የሞራል ልእልናው የላቸውም!
5.4K viewsedited  15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 16:44:37 ምን አይነት መናናቅ ነው ግን?

አንዳንድ በፍረጃ የተካኑ ሠዎች ሀሳብህን ከመሞገትና "የራሱ ሀሳብ ነው!" ብለው ከመቀበል ይልቅ አዕምሯቸው ውስጥ በደረቱት ቅዠት በሀሳብህ ቡድን ይሰጡሀል ፥ የሌሎች አጀንዳ ተሸካሚ መስለው ወይም የጎጥ ምድብ ደልድለው ተልካሻ ስም ሊሠጡህ ይላላጣሉ! ያሳዝናል! ያሳፍራልም!

ምን አይነት መናናቅ ነው ግን?

እኔ ስህተት እንኳ ብሆን ያመንኩበትን ፊትለፊት እሞግትሀለሁ ፥ ስህተቴን ካስረዳኸኝና ካመንኩበትም ፊትለፊት ይቅርታ ለመጠየቅ አላመነታም፡፡ ከውይይትና ንግግር ካለፈም ፊትለፊት እጋፈጥሀለሁ! አበቃ ይኸው ነው! አምኜበት እንጂ እንድትወደኝ ወይም እንድትጠላኝ አልሽለጠለጥም አላሽቋልጥም!

ለወንድማማችነት ፣ ለጓደኝነትና ለበጎ ተግባቦት ስንል በትእግስት የምናሳልፋቸው ፣ ፊትለፊት ያልተናገርናቸው ፣ የቻልናቸው በርካታ ነገሮች ቢኖሩም ፥ በጋራ ካሰባሰበን አላማና መርህ ውጪ ሲያፈነግጡ ግን ምን ጊዜም የምቆመው ከወሎ ፣ ከሸዋ ፣ ከጎንደር ወይም ከጎጃም ጋር ሳይሆን ከአማራ ህዝብ ትግል ጎን ነው! የምጓዘው በጓደኛ ፣ በጎጥ ሰው ወይም በቤተ-ዘመድ መንገድ ሳይሆን በገባኝ ልክ በተረዳሁት እውነተኛና ቀጥተኛው የጋራ መንገድ ነው!

እዚሁ ሳይበር ላይ ግን የሰውን ልክ የማያውቁ ወይም በእውቀት ድርቅ የተመቱ ሁሉ አልፎ አልፎ የፍረጃ ቀስቶቻቸውን ሲወረውሩብን ስቀን አልፈነዋል፡፡ "ስለእገሌ የሚባለው ትክክል አይደለም!" ባልን ጊዜ " ጓደኛው ስለሆነ ፥ የእገሌ አጀንዳ ተሸካሚ ….!" ተብለን አልፈናል፡፡ የሆነ ጊዜ " እነእከሌ ያደረጉት ነገር ተገቢ ነው! አትሳሳቱ! ነገሮች የሚታረሙትም በዚህ እንጂ በእዚህ አይነት ዘመቻ አደለም!" ስል " የእገሌ ፈረስ ፥ የእገሌ ጎጥ ሰው ስለሆንክ ፣ ….ወዘተ" ሲሉን አይተናል፡፡

በተለይ በየቀጠናው በሚኖረው በጀግናውና ደጉ አማራ ህዝባችን መሀል የበቀሉና ጫፍና ጫፍ በሚጓተቱት ጥቅመኛ የፍላጎት ቡድኖች ፥ ሀሳባችንን በነሱ የጥጥ ሚዛን እየመዘኑ ዛሬ ከአንዱ ሌላ ጊዜ ከሌላው እያቀያየሩ የፍረጃ ስም ሲለግሱን ከርመዋል፡፡ ይሄ የፍረጃ አባዜ በሀገሪቱ የብልሽት ፖለቲካ ውስጥ መርህ እስኪመስል የተለመደ ንቅዘት በመሆኑ ፥ ነገም ሆነ ከነገወዲያ በአማራ ህዝብ ውስጥ መነሻና መድረሻ ግቡን በቅጡ የተረዳ ጠንካራ የፖለቲካ ማህበረሰብ መፍጠር እስከምንችል ድረስ የሚቀጥል ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡ ሊቀንስ እንጂ ፈፅሞ ሊጠፋም አይችልም፡፡

የሚያውቁኝና የማውቃቸው እንዲሁም ከፍ ያለ ደረጃ የምሠጣቸው ሰዎች ሲፈርጁኝ ግን እጅግ ያመኛል ብቻ ሳይሆን እፀየፋቸዋለሁ!

"ፍረጃ" በተለይም በብሔር ፖለቲካ ውስጥ ፦ ህዝባዊ አንድነትን የሚሸረሽር ፣ መተማመንን የሚያጠፋ ፣ ወንድማማችነትን የሚያደበዝዝ ፣ ቅራኔ የሚፈጥርና በመርህና በአላማ ከሚዘወረው ሀዲድ አውጥቶ የሚፈጠፍጥ አስከፊ ደዌ ነው!

በመሆኑም በዚህ ደዌ የተጠቁ ሁሉ ፥ በፍረጃ ከገነቡት የቅዠት አድማስ ወጥተው ፥ በጠቃሚ የሀሳብ ሙግትና የመርህ ትግል እንዲፈወሱ አሳስባቸዋለሁ!
7.6K views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 17:01:12
ብርቱው ጓዳችን በፀና ተይዟል!

ከወራት በፊት በአጋጣሚ ሳገኘው ፤ "ዘርሽ የጤናዬ ሁኔታ ከጊዜ ወደጊዜ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል! በፀሎት አስቡኝ!" ነበር ያለኝ!

ወዳጆቼ እባካችሁን ይህን ቪዲዮ ተመልከቱት ፤ በቻላችሁት ሁሉ ትረዱትና ትጸልዩለት ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን !

ወንድማችን ይድነቃቸው አዲስ ባጋጠመው ድንገተኛ የጤና መታወክ የተነሳ ጤናው በእጅጉ ተጓድሏል። የደም መርጋት (subacute proximal Deep vain thrombosis) በሚባል የጤና መታወክ የተነሳ የህክምና ሂደት ላይ እያለ በድጋሚ ልቡ ላይ ደም ረግቶ ( Acute thrombotic occlusion ) አጋጥሞት በህክምና ላይ ይገኛል። ስለሆነም የተሻለ ህክምና ያገኝ ዘንድ ወዳጆቹ ይህንን ጎ ፈንድሚ አዘጋጅተናልና ። በቻላችሁት ሁሉ ትረዱትና በፀሎትና በዱአ ታስቡት ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን!

በየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000 271 784 938
ይድነቃቸው አዲስ መኮንን

ጎ ፈንድሚ https://gofund.me/13feebf7

#ሼር ማድረግም ትልቅ ድጋፍ ነውና መልእክቱን ያጋሩት ዘንድ እጠይቃለሁ!
7.4K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 22:59:57 አዲስአበቤ የተወሰነብህን ሰምተሀል ወይ ?

የኦሮሚያ ክልልና አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር (ሽመልስና አዳነች) << የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የፌንፌኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን ስምምነት >> በሚል ርዕስ ለብልፅግና አመራሮችና አባላት እያወያዩበት ባለው ሰነድ ፥ " የፌደራሉን ህገ መንግስት ፥ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ ህገ-መንግስትና የአድስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተርን መሰረት አድርገን የወሰን ማካለሉን ሰርተናል!" ሲሉ አትተዋል!

በሰነዱ ላይ በግልፅ የተቀመጡ ውሳኔዎችም ፦

☞ " በጉለሌ ፥ የካና ለሚኩራ ክፍለ ከተሞች አሁን ያለዉን የተፈጥሮ ወሰንና ኢፌክቲቭ አስተዳደር ይዘው እንዲቀጥሉ ተወስኗል፡፡ " ተብሏል!

☞ " ኮልፌ በአብዛኛዉ የተፈጥሮ ወሰንና ኢፌክቲቭ አስተዳደርን መሰረት በማድረግ አብዛኛዉ ወደ አዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ወደ ቡራ እና ሰበታ ከተማ አስተዳደሮች እንዲካለሉ ወስነናል!" ብለዋል!

☞ " ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አብዛኛዉ ወደ አዲስ አበባ ሆኖ አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ወደ ሰበታ ክ/ከተማ አስተዳደር እንዲካለል ወስነናል!" ተብሏል!

☞ "አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ኮየ ጨፌ እና ቱሉ ድምቱ በከፊል ወደ ገላን ከተማ አስተዳደር እንዲካለል ተወስኗል!" ተብሏል!

እንግዲህ የትህነግን የሴራ ድርሰት መሠረት በማድረግ ፥ አዲስአበቤው የራሱን እጣፋንታ በራሱ የመወሠን መብቱ ሳይከበርለት እጅግ አደገኛና ቀጣዩን ሁኔታ አመላካች የሆነ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተወስኗል!

አዲስአበባ የመላው ኢትዮጵያውያን ከተማ ነች፡፡ በዚህ ጉዳይ የራሱን እድል በራሱ የመወሠን መብት ያለው አዲስአበቤው ነው፡፡ ነገ ከዚህ ተከትለው የሚመጡ ችግሮችን ጭምር በቀዳሚነት የሚጋፈጠው ራሱ አዲስአበቤው ነው፡፡

በመሆኑም አዲስአበቤው የዜግነት መብቱን ታግሎ ያስከብራል ወይስ እንደወትሮው በዝምታ ያልፈው ይሆን ?

አብረን የምናየው ይሆናል!
9.7K viewsedited  19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ