Get Mystery Box with random crypto!

አዲስአበቤ የተወሰነብህን ሰምተሀል ወይ ? የኦሮሚያ ክልልና አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር (ሽመ | ዘሪሁን ገሠሠ

አዲስአበቤ የተወሰነብህን ሰምተሀል ወይ ?

የኦሮሚያ ክልልና አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር (ሽመልስና አዳነች) << የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የፌንፌኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን ስምምነት >> በሚል ርዕስ ለብልፅግና አመራሮችና አባላት እያወያዩበት ባለው ሰነድ ፥ " የፌደራሉን ህገ መንግስት ፥ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ ህገ-መንግስትና የአድስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተርን መሰረት አድርገን የወሰን ማካለሉን ሰርተናል!" ሲሉ አትተዋል!

በሰነዱ ላይ በግልፅ የተቀመጡ ውሳኔዎችም ፦

☞ " በጉለሌ ፥ የካና ለሚኩራ ክፍለ ከተሞች አሁን ያለዉን የተፈጥሮ ወሰንና ኢፌክቲቭ አስተዳደር ይዘው እንዲቀጥሉ ተወስኗል፡፡ " ተብሏል!

☞ " ኮልፌ በአብዛኛዉ የተፈጥሮ ወሰንና ኢፌክቲቭ አስተዳደርን መሰረት በማድረግ አብዛኛዉ ወደ አዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ወደ ቡራ እና ሰበታ ከተማ አስተዳደሮች እንዲካለሉ ወስነናል!" ብለዋል!

☞ " ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አብዛኛዉ ወደ አዲስ አበባ ሆኖ አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ወደ ሰበታ ክ/ከተማ አስተዳደር እንዲካለል ወስነናል!" ተብሏል!

☞ "አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ኮየ ጨፌ እና ቱሉ ድምቱ በከፊል ወደ ገላን ከተማ አስተዳደር እንዲካለል ተወስኗል!" ተብሏል!

እንግዲህ የትህነግን የሴራ ድርሰት መሠረት በማድረግ ፥ አዲስአበቤው የራሱን እጣፋንታ በራሱ የመወሠን መብቱ ሳይከበርለት እጅግ አደገኛና ቀጣዩን ሁኔታ አመላካች የሆነ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተወስኗል!

አዲስአበባ የመላው ኢትዮጵያውያን ከተማ ነች፡፡ በዚህ ጉዳይ የራሱን እድል በራሱ የመወሠን መብት ያለው አዲስአበቤው ነው፡፡ ነገ ከዚህ ተከትለው የሚመጡ ችግሮችን ጭምር በቀዳሚነት የሚጋፈጠው ራሱ አዲስአበቤው ነው፡፡

በመሆኑም አዲስአበቤው የዜግነት መብቱን ታግሎ ያስከብራል ወይስ እንደወትሮው በዝምታ ያልፈው ይሆን ?

አብረን የምናየው ይሆናል!