Get Mystery Box with random crypto!

ፍትህ የተዛነፈባቸው ፋኖዎች የርሃብ አድማ ከጀመሩ 2ተኛ ቀናቸው ነው! መቼም እየሆኑ ያሉት ነ | ዘሪሁን ገሠሠ

ፍትህ የተዛነፈባቸው ፋኖዎች የርሃብ አድማ ከጀመሩ 2ተኛ ቀናቸው ነው!

መቼም እየሆኑ ያሉት ነገሮች ለሞራልም ለህሊናም ተቃራኒ ናቸው፡፡ ህወሓት ወረራ ሲፈፅም አይደለም ለህዝብና ስለህዝብ የቆመውን ፋኖ ይቅርና ፥ ፍርድ ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት ከሚገኙት ጀምሮ "ሽፍታ" ተብለው በጫካ እስከሚታደኑት ድረስ " የነፍስ ድረሱልን!" ተብለው ወደጦር ግንባር ዘምተው ለሀገራቸውና ለህዝባቸው የደምና የአጥንት ዋጋን እንዲከፍሉ ተደርጓል፡፡

ጦርነቱ ቀዝቀዝ ሲል ግን የሆነውና እየሆነ ያለው ለህሊናም ለሞራልም ተቃራኒ የሆነ ክህደት የሚመስል ተግባር ነው፡፡

ከነዚህ የመንግስታዊ ነውር ሰለባዎች መካከል ደግሞ የአማራን ፋኖ በአንድ ህዝባዊ አደረጃጀት ስር በሀላፊነትና በተጠያቂነት መንፈስ እንዲመራ ሲጥሩ በነበረበት ለመንግስታዊ አፈና የተዳረጉት ወደ13 የሚሆኑ "የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አመራሮች" ተጠቃሽ ነው፡፡

እነዚህ ወንድሞቻችን ለረዥም ጊዜ በእስር ከቆዩ በኃላ የክልሉ ፍርድ ቤት ሀምሌ 22 በዋለው ችሎት ለእያንዳንዳቸው የ25 ሺህ ብር ዋስትና አስይዘው እንዲወጡ የወሰነ ቢሆንም ፥ ይህንኑ ተፈፃሚ አድርገው ከእስር ለመውጣት ሲሞክሩ ፥ የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶችን ስልጣንና ውሳኔ በተደጋጋሚ በሀይል እየሻረ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ "አሻፈረኝ” በማለት ከታሰሩበት ሳባታሚት ማረሚያ ቤት ድረስ በመምጣት እንዳይለቀቁ አድርጎ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

ፍትህ የተጓደለባቸው እኚህ ወንድሞቻችን ሌላው ቢቀር "የክልሉ ፍርድ ቤት ውሳኔ ይከበር! ፍትህ ይሰጠን!" ሲሉ ከትናንት ጀምረው የረሃብ አድማ በማድረግ ላይ ናቸው ።

የክልሉ የፍትህ ተቋማት ግን እንዴት ይሄን በተደጋጋሚ የሚፈፀም ነውርና ውሳኔአቸውን በሀይል የመሻር አንባገነናዊ ጣልቃገብነት በዝምታ አለፉት ?

የፍርድ ቤት ውሳኔ ይከበር! ለወንድሞቻችን ፍትህ ይሰጣቸው!