Get Mystery Box with random crypto!

የኦሮሞ ፖለቲከኞች ስለሰብአዊነት ፣ ስለፍትህና እኩልነት የመናገር ፣ የመዳኘትና የማማከር የሞራል | ዘሪሁን ገሠሠ

የኦሮሞ ፖለቲከኞች ስለሰብአዊነት ፣ ስለፍትህና እኩልነት የመናገር ፣ የመዳኘትና የማማከር የሞራል ልእልናው የላቸውም!

ቫቲካን 825 ዜጎች ያሏት በአለም በህዝብ ቁጥርም ሆነ በቆዳ ስፋቷ የመጨረሻ ትንሿ ሀገር ነች፡፡ አስረኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ዶሚኒካ ሪፐብሊክ እንኳ የህዝብ ቁጥሯ 71,890 ብቻ ነው፡፡

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ብቻ በትንሹ ወደ 10 ሚሊየን የሚገመቱ አማራዎች ይኖራሉ፡፡ በአንዳንድ ዞኖችና ወረዳዎች እንደውም አብላጫውን ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚኖሩት አማራዎች ናቸው፡፡

እነዚህ ለአስርት አመታት ጫካ መንጥረው ፣ መንደር መስርተው ፥ አርሰው አምርተው ፣ ወልደው ከብደውና ሀብት አፍርተው ለሀገር ግንባታ የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እያበረከቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፥ አይደለም ማንነታቸውን ጠብቀው ፣ ባህልና ወጋቸውን እያበለፀጉ ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብት ሊያገኙ ይቅርና የመምረጥና የመመረጥ መብት የሌላቸው ከቁጥር የዘለለ ትርጉም ያልተሰጣቸው ዜጎች ናቸው፡፡

ባለፉት አራት አመታት ያለእረፍት በተፈፀመባቸው የዘር ፍጅት በአስርት ሺዎች አልቀዋል ፣ ሚሊየኖች ሀብት ንብረታቸውን ጥለው በገዛ ሀገራቸው ስደተኛ ሆነዋል፡፡ ኢትዮጵያን በሀገር ውስጥ ፍልሰት አንደኛ ያስባላትም ይሄው የአማራዎች ፍልሰት (ስደት) ነው፡፡

"የኦሮሞ ልሂቃን ተኮትኩተው ያደጉበት የሀሰተኛ ጥላቻ ትርክት ፍፁም ጨካኝና ህሊና ቢስ አድርጓቸዋል" የምለውም ለዚህ ነው፡፡

ያ ሁሉ ህዝብ (አብዛኛዎቹ የወሎ አማራዎች) ከቁጥር የዘለለ ትርጉም አጥተው የግፍና የሰቆቃ ዶፍ እየዘነበባቸው የሚኖርበት ክልል ውስጥ ሆነው ፥ "ወሎ ኬኛ ፣ ወሎ ክልል ይሁን! …ወዘተ" የሚል ሼም አልባ ፖለቲካ ሲዘውሩ ሳይ አፍራለሁ፡፡ እሸማቀቃለሁ!

አማራ ክልል ከማንኛውም የሀገሪቱ ክልሎች ቀድሞ የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብት ያረጋገጠ "የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት" አክብሮ የልዩ ዞንና ወረዳን እውቅና የሠጠ ብቸኛው ክልል ነው! ነገርግን ይህ የክልሉ መልካም ተግባር የሚስተዋለው ሲያስመሰግነው ሳይሆን ፖለቲካዊ እሳት በየጊዜው እንዲቀጣጠል ሲያደርግበት ነው!

እስኪ! ኦሮሚያ ክልል ውስጥ አይደለም ልዩ ዞን አንድ እንኳ ለነዋሪዎቹ የዜግነት መብት የተፈቀደበት የልዩ ወረዳ ሊጠቅስልኝ የሚችል ሠው አለን ? በፍፁም! ጥያቄውን ማንሳት ራሱ የሚያስቀስፍበት ምድራዊ ገሀነም ነው!

አዎ! ኦሮሚያ ክልል ያን ሁሉ ሚሊየን ህዝብ የፖለቲካ መያዣ አደድርገው ፥ በገዛ ሀገሩ " እንፈጀዋለን ፣ እናባርረዋለን ፣ እናፈናቅለዋለን!" በማለት እኩይ ፖለቲካዊ ፍላጎታቸውን ለማስፈፀም የሚተጉ ህሊና ቢስና ጨካኝ ፖለቲከኞች የሚዘውሩት ክልል ነው!

" የፊንፊኔ ልዩ ዞን" የሚባል የነዋሪዎቹን ይሁንታ ሳያገኙና የራስን እድል በራስ የመወሰን መብታቸው ሳይከበር ፥ በቤተ-ዘመድ ተመካክረው ሲመሰርቱ ፥ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እንደሰው እንኳ የመከበር ሰብአዊ መብት ስለተነፈጉት አማራዎችና ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ማስታወስ አይፈልጉም፡፡ ስታነሳባቸውም ይነዝራቸዋል፡፡

እውነት እውነት እላችኃለሁ…….!

የኦሮሞ ፖለቲከኞች ስለሰብአዊነት ፣ ስለፍትህና እኩልነት የመናገር ፣ የመዳኘትና የማማከር የሞራል ልእልናው የላቸውም!