Get Mystery Box with random crypto!

ምን አይነት መናናቅ ነው ግን? አንዳንድ በፍረጃ የተካኑ ሠዎች ሀሳብህን ከመሞገትና 'የራሱ ሀሳብ | ዘሪሁን ገሠሠ

ምን አይነት መናናቅ ነው ግን?

አንዳንድ በፍረጃ የተካኑ ሠዎች ሀሳብህን ከመሞገትና "የራሱ ሀሳብ ነው!" ብለው ከመቀበል ይልቅ አዕምሯቸው ውስጥ በደረቱት ቅዠት በሀሳብህ ቡድን ይሰጡሀል ፥ የሌሎች አጀንዳ ተሸካሚ መስለው ወይም የጎጥ ምድብ ደልድለው ተልካሻ ስም ሊሠጡህ ይላላጣሉ! ያሳዝናል! ያሳፍራልም!

ምን አይነት መናናቅ ነው ግን?

እኔ ስህተት እንኳ ብሆን ያመንኩበትን ፊትለፊት እሞግትሀለሁ ፥ ስህተቴን ካስረዳኸኝና ካመንኩበትም ፊትለፊት ይቅርታ ለመጠየቅ አላመነታም፡፡ ከውይይትና ንግግር ካለፈም ፊትለፊት እጋፈጥሀለሁ! አበቃ ይኸው ነው! አምኜበት እንጂ እንድትወደኝ ወይም እንድትጠላኝ አልሽለጠለጥም አላሽቋልጥም!

ለወንድማማችነት ፣ ለጓደኝነትና ለበጎ ተግባቦት ስንል በትእግስት የምናሳልፋቸው ፣ ፊትለፊት ያልተናገርናቸው ፣ የቻልናቸው በርካታ ነገሮች ቢኖሩም ፥ በጋራ ካሰባሰበን አላማና መርህ ውጪ ሲያፈነግጡ ግን ምን ጊዜም የምቆመው ከወሎ ፣ ከሸዋ ፣ ከጎንደር ወይም ከጎጃም ጋር ሳይሆን ከአማራ ህዝብ ትግል ጎን ነው! የምጓዘው በጓደኛ ፣ በጎጥ ሰው ወይም በቤተ-ዘመድ መንገድ ሳይሆን በገባኝ ልክ በተረዳሁት እውነተኛና ቀጥተኛው የጋራ መንገድ ነው!

እዚሁ ሳይበር ላይ ግን የሰውን ልክ የማያውቁ ወይም በእውቀት ድርቅ የተመቱ ሁሉ አልፎ አልፎ የፍረጃ ቀስቶቻቸውን ሲወረውሩብን ስቀን አልፈነዋል፡፡ "ስለእገሌ የሚባለው ትክክል አይደለም!" ባልን ጊዜ " ጓደኛው ስለሆነ ፥ የእገሌ አጀንዳ ተሸካሚ ….!" ተብለን አልፈናል፡፡ የሆነ ጊዜ " እነእከሌ ያደረጉት ነገር ተገቢ ነው! አትሳሳቱ! ነገሮች የሚታረሙትም በዚህ እንጂ በእዚህ አይነት ዘመቻ አደለም!" ስል " የእገሌ ፈረስ ፥ የእገሌ ጎጥ ሰው ስለሆንክ ፣ ….ወዘተ" ሲሉን አይተናል፡፡

በተለይ በየቀጠናው በሚኖረው በጀግናውና ደጉ አማራ ህዝባችን መሀል የበቀሉና ጫፍና ጫፍ በሚጓተቱት ጥቅመኛ የፍላጎት ቡድኖች ፥ ሀሳባችንን በነሱ የጥጥ ሚዛን እየመዘኑ ዛሬ ከአንዱ ሌላ ጊዜ ከሌላው እያቀያየሩ የፍረጃ ስም ሲለግሱን ከርመዋል፡፡ ይሄ የፍረጃ አባዜ በሀገሪቱ የብልሽት ፖለቲካ ውስጥ መርህ እስኪመስል የተለመደ ንቅዘት በመሆኑ ፥ ነገም ሆነ ከነገወዲያ በአማራ ህዝብ ውስጥ መነሻና መድረሻ ግቡን በቅጡ የተረዳ ጠንካራ የፖለቲካ ማህበረሰብ መፍጠር እስከምንችል ድረስ የሚቀጥል ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡ ሊቀንስ እንጂ ፈፅሞ ሊጠፋም አይችልም፡፡

የሚያውቁኝና የማውቃቸው እንዲሁም ከፍ ያለ ደረጃ የምሠጣቸው ሰዎች ሲፈርጁኝ ግን እጅግ ያመኛል ብቻ ሳይሆን እፀየፋቸዋለሁ!

"ፍረጃ" በተለይም በብሔር ፖለቲካ ውስጥ ፦ ህዝባዊ አንድነትን የሚሸረሽር ፣ መተማመንን የሚያጠፋ ፣ ወንድማማችነትን የሚያደበዝዝ ፣ ቅራኔ የሚፈጥርና በመርህና በአላማ ከሚዘወረው ሀዲድ አውጥቶ የሚፈጠፍጥ አስከፊ ደዌ ነው!

በመሆኑም በዚህ ደዌ የተጠቁ ሁሉ ፥ በፍረጃ ከገነቡት የቅዠት አድማስ ወጥተው ፥ በጠቃሚ የሀሳብ ሙግትና የመርህ ትግል እንዲፈወሱ አሳስባቸዋለሁ!