Get Mystery Box with random crypto!

በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተፈፀመው ነውር ፥ በእግር ኳስ ፌዴሬሽንም ተደገመ! ተከታዩ ፅሁፍ የጌታ | ዘሪሁን ገሠሠ

በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተፈፀመው ነውር ፥ በእግር ኳስ ፌዴሬሽንም ተደገመ!

ተከታዩ ፅሁፍ የጌታቸው ሽፈራው ነው!


የጎንደር ሆቴሎች ለጠቅላላ ጉባኤ ሲባል የሰርግ ፕሮግራም ሳይቀር እንዲራዘም አድርገዋል!

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ነሃሴ 21 እና ነሃሴ 22 በጎንደር ጠቅላላ ጉባኤውን ለማድረግ ወስኖ ነበር። በዚህ ውሳኔ መሰረት የጎንደር ሆቴሎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚመጡ እንግዶችን በደንብ ለማስተናገድ ሲባል የሰርግ ፕሮግራሞች እንኳን እንዲራዘም አድርገዋል። በኮሮና እና ሌሎች ምክንያቶች ችግር ላይ የከረመው የሆቴሉ ኢንዱስትሪ ከመላ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ብለው ላሰቧቸው እንግዶች ከፍተኛ ዝግጅት አድርገው፣ ፌደሬሽኑ ወኪሎችን ልኮ ዝግጅታቸውን አድንቆ ተመልሷል። ከሰርግ ባሻገር ያሏቸውን ፕሮግራሞች ሰርዘው ሙሉ ዝግጅታቸውን ለፌደሬሽኑ ስብሰባ አድርገው ነበር።

ይሁንና ፌደሬሽኑ በሰበብ ስብሰባውን ቀይሬዋለሁ ብሏል። ይህ የመጀመርያ አይደለም። ከአሁን በፊት የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ስብሰባም ከባሕርዳር ወደ ሌላ ቦታ እንዲታጠፍ ተደርጓል። ይህ ንቀት እንጅ ምንም ሊባል አይችልም። በርካታ ሆቴሎች ለዝግጅት ወጭ ካደረጉ በኋላ መሰል ተግባራት ሕዝብን ከመናቅ የመጡ ናቸው።

ሰበብ ብለው ያስቀመጡት የአማራ ክልል አመራሮች አስፈራርተውናል የሚል ነው። ይህ ተራ ምክንያት እንጅ አሳማኝ ሊሆን አይችልም። የመጀመርያ ነገር የክልል ተወካዮች የፌደራል ተቋማቱን እያስፈራሩ ውሳኔ የሚያስቀይሩበት አካሄድ የተለመደ አይደለም። ሁለተኛው የሚሰበሰቡት ሆቴል እንጅ ጫካ ውስጥ አይደለም። ይሁንና ፌደሬሽኑ አማራ ክልል ላይ መሰል ጋጠወጥነት ያለ በማስመሰል የስም ማጥፋት ጭምር ነው በደብዳቤው ያስተላለፈው።

ይህ ተቋማዊ የነውር ፣ የጥላቻና የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው!