Get Mystery Box with random crypto!

ፌዴሬሽኑ ውሃ የማያነሳ ተራ ሰበብ መደረቱ ለምን አስፈለገው? ፌዴሬሽኑ ጎንደር ጉባኤውን ለማስተ | ዘሪሁን ገሠሠ

ፌዴሬሽኑ ውሃ የማያነሳ ተራ ሰበብ መደረቱ ለምን አስፈለገው?

ፌዴሬሽኑ ጎንደር ጉባኤውን ለማስተናገድ ሰፊ ዝግጅት አድርጋ ባጠናቀቀችበትና ይህንኑም ራሳቸው አይተው ባደነቁበት ማግስት ፥ ጉባኤውን ወደአዲስአበባ እንዲደረግ ከወሰነበት ምክንያት መካከል  ፦

<< ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጠቅላላ ጉባኤ ስራ ወደሚያከናውኑ ሰራተኞች ስልክ በመደወል ከክልሉ ክለቦች የተላኩ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ወኪሎችን ስሞች መቀየር አለባቸው ይህንን ካላደረጋችሁ  በማለት በማስፈራራት ጭምር ጉባኤውን እንዲስተጓጎል እንደሚያደርጉ ስሜታቸውን መግለፃቸው ኮሚቴው ባደረገው ማጣራት አጋግጧል! >> የሚል "የናቴ መቀነት አደናቀፈኝ!" አይነት ውሃ የማያነሳ ምክንያት ነው!

ግለሰቡ ይህንን ተግባር ፈፀሙ ቢባል እንኳ ፥ በመረጃና በማስረጃ በህግ ጭምር መጠየቅ ብሎም ከክልሉ አመራሮች ጋር በግልፅ ተነጋግሮ ማስተካከል እየተቻለ "እቃቃ ፈረሰ ፥ ...!" አይነት የልጆች ጨዋታ መጫወቱ ፥ ከአንድ ግዙፍና ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት የፀዳ ነው ተብሎ ከሚታሰብ ብሄራዊ ተቋም የማይጠበቅ አሳፋሪ ድርጊት ነው!

የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተፈሪ ካሳ የሚባሉ ግለሰብ ይመስሉኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ማብራሪያ እንደሚሠጡበት ይጠበቃል!

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በባህርዳር ሊያካሂደው የነበረውን ጠቅላላ ጉባኤ በተመሳሳይ መሰረዙ የሚታወስ ነው!