Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 39

2022-11-01 16:00:24 ብስቁልናን እንደብልፅግና - መንግስታዊ የአስመሳይነት አዙሪት!

"...የምንቃወመውና የምንተቸው ሱስ ኖሮብን አይደለም! "

ኢትዮጵያውያንን ቃላት ድርደራ ፥ የመድረክ ድስኩርና የማይጨበጥ ተስፋ "የእለት ዳቦ" ሲሆናቸው ማየት ህልም እየሆነ መጥቷል፡፡ ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ በየደቂቃው የሚያሻቅበው የኑሮ ውድነት ፥ ለዜጎች በቀን አንድ ጊዜ መመገብን እንኳ አቀበት እያደረገባቸው ነው፡፡ የመንግሥት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ወርሀዊ ደመወዝ ለአንድ ወር ቀርቶ ለአንድ ሳምንት እንኳ በልተው ማደርን ፈታኝ አድርጎባቸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ የመንግሥት መሪዎች በየእለቱ በየሚዲያውና በየመድረኩ የሚገልፁት የህዝብን ከመጠን ያለፈ ብስቁልና እንደብልፅግና የሚቆጥር ድስኩር "ማንን ለማታለል ወይም ለመሸወድ እየተጣጣሩ ይሆን?" ያስብላል፡፡ ህሊናቸውን? በስቋላውን ህዝብ ወይስ ማንን ?

"ኢትዮጵያ በስንዴ አቢዎት እየተጥለቀለቀች ነው!" መባል ከጀመረ ሁለተኛ አመት ተቆጠረ፡፡ በሁለቱ አመት ውስጥ ደግሞ የዳቦ ዋጋ ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ ሁላችንም የምናውቀው የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጊዜ ወደጊዜ እየረከሰና ዋጋ እያጣ የመጣው ክቡር የሆነው የሠው ልጅ ብቻ እንጂ በሰው የሚሠሩ ወይም የሚመረቱ ነገሮች በዋጋ የማይቀመሱ ሆነዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ ችግኝ መትከላቸውን የተቃወመ የለም፡፡ ነገርግን መንግስታቸው ሀላፊነቱን ተወጥቶ " ሰላምና ደህንነቴን ያስጠብቅልኛል!" ያላቸው ህዝብ በየእለቱ እንደቅጠል እየረገፈ " ሰው እየሞተም ለአስከሬኑ ጥላ እንዲሆነው ችግኝ እንተክላለን!" ማለታቸው ከመሪ ሳይሆን ከሰይጣን የሚጠበቅ ምላሽ በመሆኑ ነበር፡፡

መናፈሻና አበባ መትከላቸውንም የነቀፈ የለም፡፡ ነገርግን ዜጎች ቁራሽ ዳቦ ርቋቸው "ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ" እያሉ ባለበት ሁኔታ ፥ በብድር የሚመጣን ቢሊየን ዶላር ለመናፈሻና መዝናኛ ቅድሚያ ሰጥተው ማፍሰሳቸው " ትለብሰው የላት ፥ ትከናነበው አማራት" እንዲሉት ብሂል ስለሚሆን ነው፡፡ ሲጀመር ለራሳቸውና ባለፀጎች እንዲዝናኑበት ካልሆነ በስተቀር ለራበው ህዝብ ዳቦ እንጂ መናፈሻ ምኑ ነው?

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይና መንግስታቸው በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከሁሉም መስክ በአንደኛው እንኳ ስኬታማ መሆን ቀርቶ የነበረውን ማስቀጠል የተሳናቸው መሆናቸውን ፥ የኖርንባቸው ያለፉት ወደአምስት የሚጠጉ የመከራ አመታት ከበቂ በላይ አስረጂ ናቸው፡፡

"ኢትዮጵያ ስንዴን ለኬኒያና ጅቡቲ ለመሸጥ ውለታ ፈፀመች" ሲባል ወይም ደግሞ " የድፍድፍ ነዳጅን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ጀመረች" በሚሉን ጊዜ እያረርን የምንስቀው ፥ እያመመን የምንተቸው የሀገራችንን እድገትና ብልፅግና ጠልተን ወይም ሳንፈልግ ቀርተን ሳይሆን የሀገሪቱን ህዝብ የማይጨበጥ ተስፋ እየመገቡ ፥ ከጊዜ ወደጊዜ በሚባባስ ብስቁልናና የኑሮ ጫና ውስጥ መኖሩን የምንረዳ የአይን ምስክሮች ስለሆንን ነው፡፡ በሚናገሩት ሁሉ የምናፌዘው በድስኩራቸው ልክ የምንተቸውም "ፍየል ወዲያ ቁዝምዝም ወዲህ" በሆነው ምግባርና ድስኩራቸው ስለመረረንና እምነት ስላጣንባቸው እንጂ የመቃወምና የመተቸት ሱስ ኖሮብን አይደለም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይና መንግስታቸው የተንደላቀቀ መናፈሻ አሰርተው ጥንዶችን እያጋቡ በዋሉበት እለት አለም የሚያወራው ደግሞ ከኑሮ ውድነቱና የዋጋ ግሽበቱ ባሻገር ፥ ኢትዬጲያ በ40 ዓመታት ውስጥ ያልታየ አስከፊ ድርቅ መመታቷንና ከ20 ሚሊየን የሚልቁት ዜጎቿ በከፋ የረሀብ ጠኔ ውስጥ ሆነው አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ የሚሹ መሆናቸውን ነው፡፡

ይህ የማስመሰልና የመሪዎች የታይታ የመሞላቀቅ አባዜ ክፉ ጭካኔ ከመሆኑ ባሻገር ፥ ነገ የሚያመጣው ዳፋ እጅግ የከፋና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡

ተረኛ ገዢ ሄዶ ተረኛ ገዢ እየተተካ ፥ በተመሳሳይ አዙሪትና የማስመሰል አባዜ ውስጥ ፥ ፍዳውን የሚበላው ህዝብ መከራና ግፉ የሚያቆምበት ጊዜ መቼ ይሆን ?

ቀና የህነ ልቦናና ፥ ለራሱ የሚያድር ያልተሸጠ ህሊና ይስጠን!
2.7K viewsedited  13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 19:43:13
7.4K views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 19:40:15 አሁን ይሄ ማስመስገኑ ቢቀር ምኑ ለትችት ይዳርጋል ?

የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) በአፍሪካ ህብረት ስር በሚደረገው ድርድር እንደአንድ የአማራ ተቋም በድርድሩ ለመሳተፍ ያለውን ምክንያታዊ ፍላጎት ገልፆ ፥ በድርድሩ እንዲሳተፉ የመረጣቸውን የአራት ሰዎች ስም ዝርዝር ለሚመለከታቸው አለምአቀፍ ተቋማት ሁሉ ማስገባቱን አስታውቋል!

AAA በአማራ ህዝብ ላይ ተከታታይ የዘር ፍጅትና ማሳደድ ሲፈፀም ተከታትሎ ለአለምአቀፍ ተቋማት በመረጃና በማስረጃ በማጋለጥ ፥ የአማራ ህዝብ በሀገረ-መንግስቱ ለዘመናት የስቃይና የመከራ ገፈት እንዲቀምስ ያደረገውን የተዛባ ትርክት በማረም ረገድና በሁለንተናዊ መልኩ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ያለ ተቋም ነው፡፡

የጦር አውድማ ሆኖ ለአመታት የዘለቀው የአማራ ህዝብ ትህነግ ሀገረ-መንግስቱን ከመቆጣጠሩ በፊት ገና በጫካ እያለ "ጠላት" ብሎ ፈርጆና ትርክት ፈጥሮ ዛሬ ለደረሰበት አስከፊ መከራና ስቃይ ሁሉ የተዳረገ ህዝብ ነው፡፡

ህወሓት በህዝብ ትግል ከሀገረ-መንግስቱ ስልጣን ቢገፋም ፥ ከህገ-መንግስት ጀምሮ የአማራ ህዝብ ስርአታዊና መዋቅራዊ ጭቆና እንዲደርስበት የተዘረጉ አስተሳሰቦችን ተረክቦ ያስቀጠለው ፥ የህወሓት የአብራክ ክፋዩ የብልጽግና መንግሥት ፥ የአማራን ህዝብ የዘር ፍጅትና በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግፍ ፈፃሚና አስፈፃሚ የሆነ በአለምአቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መጠየቅ ያለበት ድርጅት ሆኖ ሳለ ፥ የ1983ቱን ታሪክ ከመድገም ባለፈ ከአሸባሪው ትህነግ ጋር ተደራድሮ የአማራን ህዝብ ዘላቂ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስከብር ብሎም ወደ መፍትሔው የሚያመራ ድርድር ያደርጋል ተብሎ አይታመንም፡፡

በዚህ አውድ ውስጥ AAA ጥያቄው ተቀባይነት አገኘም አላገኘም "በድርድሩ ውስጥ ተሳታፊ መሆን አለብኝ!" ማለቱ ሊያስመሰግን ሲገባና አማራው አንድ እንኳ የሚሞግትለት ተቋም በማግኘቱ መደሰት ሲገባ ስለምን ለማጣጣል ፣ ለመሳለቅና ለመፈረጅ የሚጣደፉ ግለሰቦችን እንመለከታለን ? ተገቢስ ነውን ?

መረገም ነውኮ ጓዶች!
6.7K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 18:20:09
8.6K views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 18:19:54 የኢትዮጵያን ጀርባ ያጎበጠው ዕዳና የአበዳሪዎች እጅ ጥምዘዛ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል!

ኢትዮጵያ ላለፉት ሶስትና ከዚያ በላይ አስርት አመታት ከአለምአቀፍ ዋና ዋና አበዳሪዎች ከተበደረችው ብድርና ከነበረባት እዳ በእጥፍ የሚሆነውን የተበደረችው ባለፉት አራት አመታት ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ሀገሪቷ ከገጠማት የፖለቲካ አለመረጋጋትና ጦርነት ባሻገር በዲፕሎማሲው ዘርፍ የገጠማት ውድቀት ጋር ተዳምሮ ኢኮኖሚው እጅግ አሳሳቢ በሆነ ፈተና ውስጥ የወደቀ ሲሆን ፤ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነትም የህዝቡን ዳቦ አግኝቶ የመኖር እጣፋንታ አጣብቂኝ ውስጥ የከተተበት ሁኔታ በጉልህ እየተስተዋለ ነው፡፡

በተለይም ሀገሪቱ ከአመት በፊት ጀምሮ ፤ በምእራባውያን አበዳሪዎች በኩል በቅድመ ሁኔታዎች የተያዘባትን ብድር ለማስለቀቅና በአመት መክፈል የሚጠበቅባትን 5 ቢሊየን ዶላር መክፈል ባለመቻሏ የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላት በተደጋጋሚ ስትጠይቅ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የውጭ ብድር አከፋፈል ጫና እፎይታን ለማግኘትና የተያዘባትን ብድር ለማስለቀቅ ከአለም ባንክና የአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ጋር ውይይቶችንና ድርድሮችን እያደረገች ሲሆን ከሰሞኑ እንኳ የገንዘብና የኢኮኖሚ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ወደአሜሪካ ያቀኑበትን ሁኔታ መጥቀስ ይቻላል፡፡

አለምአቀፍ የገንዘብ ተቋማቱ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ብድር ለመስጠትና ያለባትን እዳ የመክፈያ ጊዜ ለማራዘም ከዚህ ቀደም ሲያስቀምጣቸው የነበሩት ቅድመ ሁኔታዎች አሁንም ተጠናክረው በመቀጠላቸው የሀገሪቱን ኢኮኖሚና መሰረታዊ እንቅስቃሴ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ እየከተተው ይገኛል፡፡

የዛሬ አመት በነበረው መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ በጥቅሉ ከ30 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚልቅ የውጭ ብድር የነበረባት ሲሆን ከዚያ ውስጥ 22 ቢሊየን ዶላሩ ከሀገራትና እና ከብዙሀን አበዳሪዎች (bilateral and multilateral) የተወሰደ ብድር ነበር። 3.3 ቢሊየን ዶላሩ ደግሞ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2014 በዩሮቦንድ ከግል አበዳሪዎች የወሰደችውን አንድ ቢሊየን ዶላርን ጨምሮ ከሌሎች የግል አበዳሪ ተቋማት የወሰደችው ሲሆን 2.3 ቢሊየን ዶላሩ ደግሞ በመንግስት ዋስትና ሰጭነት እንደኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አይነት ተቋማት የወሰዱት ብሎም ቀሪው 3.3 ቢሊየን ዶላሩ ደግሞ ያለመንግስት ዋስትና በኢትዮጵያ አየርመንገድና ኢትዮ-ቴሌኮም አይነት ኩባንያዎች ከውጭ አበዳሪዎች የተወሰደ ብድር ነበር።

መንግስት በወቅቱ ይህን ብድር ለመክፈል በማይችልበት ደረጃ መሆኑን ጠቅሶ በወቅቱም መክፈል የነበረበት 5 ቢሊየን እዳ የመክፈያው ጊዜ ሳምንት ብቻ ቀርቶት የነበረ በመሆኑ አበዳሪ ሀገራቱ የእዳ መክፈያ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጡትና የተያዘበት ብድርም እንዲለቀቅለት ለአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ቢማጸንም ያኔ በቀረቡትና ዛሬም በቀጠሉት የአበዳሪዎች ቅድመ ሁኔታ ምክንያት ለሀገር በቀል ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ በሚል የሶስት አመት ፕሮጀክት ሊለቀቅ የነበረውን ወደስድስት ቢሊየን ዶላር ጨምሮ በርካታ የብድር ጥያቄዎችን ሳይፈቅዱ በማጉላላት መቆየታቸው የሚታወቅ ነው፡፡

አለም ባንክ ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በአሁኑ ሰአት የሀገሪቱ ኢኮኖሚና የዋጋ ግሽበት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱንና ፤ የዜጎች የድህነት ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት ወደተባባሰ ድህነት ደረጃ ማደጉን ገልፆ በተለይም የብሄራዊ ባንክ ተቀማጭ የዶላር መጠን ከአንድ ወር በታች ለሆነ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል ብቻ መቅረቱ አሳሳቢ መሆኑን አጋርቷል፡፡

የመንግስት ከፍተኛ የብድር ፍላጎት መጨመር ፤ አለማቀፋዊው የኢኮኖሚ መታወክ በተለይ ደግሞ የሀገሪቱ ያልተረጋጋ ውስጣዊ ፖለቲካና የዲፕሎማቲክ አቅም መዳከም ፤ ከጦርነቱ ጋር ተዳምሮ ሀገሪቱን አጣብቂኝ ውስጥ የከተታት ሲሆን ፤ መንግስት ይህን ለማረምና ለማስተካከል የሚወስደው የተጠና የመፍትሄ አማራጭ አለመኖር ችግሩን ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ እንዲሄድ አድርጎታል፡፡ ለብሄራዊ ጥቅማቸው መከበር አሸባሪው ትህነግን በስውር የሚደግፉት ምእራባውያን ፤ ከመንግስት የተዳከመ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ጋር ተደምሮ ፤ አበዳሪ ሀገራቱንና የገንዘብ ተቋማቱን እንደእጅ መጠምዘዣና ማስገደጃ እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ፡፡

እንደሚታወሰው ጠ/ሚ አብይ ወደስልጣን ከመጡበትና ‹‹ለውጥ›› እየተባለ ከሚጠራው ጊዜ ወዲህ ሀገሪቱ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አለማቀፋዊ እዳዋ በእጥፍ አድጎ ይገኛል፡፡
8.3K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 22:42:52 አፍንጫህ አዲስአበባ ስር እየሆነ ያለውን ጥሬ ሀቅ ልንገርህ!

ኦነግ ወለጋን ጨምሮ ሌሎቹን ራቅ ያሉ የክልሉ አካባቢዎችን አልፎ ፥ ምስራቅ ሸዋን አብዛኛውን ቦታ ከቦና ተቆጣጥሮት ይገኛል፡፡ መሳሪያዎችን ከመንግሥት ተቋማትና ከማህበረሰቡ እየገፈፈ በገፍ እያስታጠቀ ነው፡፡ ማንኛውም ድጋፍ የማያደርግ ባለሀብትና አመራር ወዲያውኑ እንዲወገድ ይደረጋሉ!

ሁኔታው ከምንለውም በላይ አስጊ መሆኑን ፥ ምናልባት የሚገባን ከረፈደ በኃላ ሊሆን ይችላል!

መልካም ለሊት!
1.6K views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 22:42:50
1.5K views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 22:41:29 አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ የመንግሥት አመራሮችን ማፈኑ ተገለፀ!

በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እንዳሻው እየተንቀሳቀሰ ጭፍጨፋ የሚፈፅመው ኦነግ ፥ መጠነ ሰፊ እንቅክቃሴ ከሚያደርግባቸው አካባቢዎች መካከል የጉጂ ዞኖች ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው፡፡

በጉጂ ዞን ቡድኑ ከሠሞኑ እንኳ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታጣቂዎቹን ያስመረቀ ሲሆን አካባቢዎችን በመቆጣጠር ወደሞያሌና አዲስአበባ የሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችን በመግታት ብሎም ዘረፋና ግድያ በመፈፀም ላይ ይገኛል፡፡

ይህ ነፍሰበላ ቡድን በትናንትናው እለት ማለዳ በምእራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ ሁሩፋ ከተባለ አካባቢ በነዋሪዎች ላይ ጥቃት የፈፀመ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ነዋሪዎች ተገድለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ቡድኑ በፎቶግራፍ አስደግፎ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ፥ በዚሁ ወረዳ የወረዳው የካቢኔ አመራሮችን ፥ የፖሊስና የሚሊሻ አባላትን ማእከል አድርጎ በከፈተው ጥቃት ወደ13 የሚሆኑትን በመግደል 3ቱን አፍኖ መውሰዱ አስታውቋል፡፡

በአሸባሪ ቡድኑ ከታፈኑት መካከልም ፦

1ኛ. አቶ ደስታ ገለቶ - የወረዳው አመራርና ካቢኔ
2ኛ. አቶ አብረሀም ዋዱ - የፖሊስ አባልና ሌላ በስም ያልታወቀ የሚኒሻ አደራጅ እንደሚገኙበት ተገልፇል፡፡

ጉጂ ዞኖች ቡድኑ በከፍተኛ ሁኔታ አሸባሪዎቹን እየመለመለ የሚያሰለጥንባቸውና መጠነ ሰፊ የሽብር እንቅስቃሴ የሚያደርግባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡
1.5K views19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 22:07:13
3.6K views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 22:06:50 ለታለፈው ቀይ መስመር የተሠጠ አፀፋ ይሆንን?

የኬቭ ሰማይ እሳት እየተፉ በሚያስገመግሙት የሩሲያ ሚሳኤሎች ሲተረማመስ ፥ ምድሩም "እምሽክ ድቅቅ" በሚያደርጉ ከባባድ ፍንዳታዎች ሲታረስ ውሏል፡፡

ከትናንት በስቲያ ፑቲን "ቀይ መስመሬ ነው!" ያሉት ክሬሚያን ከሩሲያ የሚያገናኘው ግዙፉ ድልድይ በከባድ ፍንዳታ እንዳልነበር ሆነ፡፡ ሩሲያ "ይህን ድልድይ መምታት በቀጥታ የኒኩሌር ጦርነት ከማወጅ እኩል ነው!" ብላ ስትዝት የሰነበተችበት ይህ ቀይ መስመሯ ፥ በምዕራባውያን "አይዞሽ በርቺ" በምትባለው ዩክሬን በአደባባይ ታለፈ፡፡

መላው አለም በተለይም አውሮፓውያን በፍርሃት መራድ የጀመሩት ፥ " ሞስኮ ለዚህ የቀይ መስመር መታለፍ የምትሰጠው የአፀፋ ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል?" የሚለውን ጉዳይ ማሰብ ከጀመሩበት ደቂቃ በኃላ ነበር፡፡ " የኒኩሌር ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች!" ብለው መላምታቸውን ያስቀመጡ ሁሉ ፥ በ24 ሰአት ውስጥ ከመሬት በታች የተሰሩ የዋሻ መኖሪያ መንደሮችን የቤት መሸጫ ዋጋ ከፍ አደረጉት፡፡

በዚህ መካከል ሞስኮ ዛሬ ማለዳ ጀምራ ያለእረፍት የዩክሬንን ዋና ከተማ ኬቭ ፥ በተምዘግዛጊ ሚሳኤሎቿ ስታርሳት ውላለች፡፡ ከጥቃቱ በኃላ የጦር ጀነራሏን የቀየረችው ሩሲያ ዛሬ ለሰአታት በፈፀመችው ጥቃት በ8 ክልሎች ላይ 11 መሰረተ ልማቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው የዩክሬኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዴኒስ ሺምይጋል ሲገልፁ ፥ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በበኩላቸው " ሩሲያ የዩክሬንን ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት እየጣረች ነዉ!" ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ጥቃቱ በሰው ህይወትና በመሠረተ ልማቶች ላይ ከባድ ጉዳት አስከትሏል፡፡

ለማንኛውም ኬቭ የዛሬውን ቀን በእሳትና በጭስ ታፍና በምድር አንቀጥቅጥ ፍንዳታ እየታመሠች ውላለች፡፡ የአዳሯን ሁኔታ በተመለከተ ከፈጣሪና ከሩሲያ በስተቀር አንዳችንም ለመገመት አንችልም!

ጓዶች! ትናንት << ይሄ "የውመል ቂያማ/የምፅዓት ቀን" የሚባለው ጊዜ ደርሶ ይሆን እንዴ? >> ብዬ ጠይቄአችሁ ነበር፡፡ አዎ! አለም ወዴት ልታመራ ይሆን ?

ሠላም ለአለም!
3.5K viewsedited  19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ