Get Mystery Box with random crypto!

ለታለፈው ቀይ መስመር የተሠጠ አፀፋ ይሆንን? የኬቭ ሰማይ እሳት እየተፉ በሚያስገመግሙት የሩሲያ | ዘሪሁን ገሠሠ

ለታለፈው ቀይ መስመር የተሠጠ አፀፋ ይሆንን?

የኬቭ ሰማይ እሳት እየተፉ በሚያስገመግሙት የሩሲያ ሚሳኤሎች ሲተረማመስ ፥ ምድሩም "እምሽክ ድቅቅ" በሚያደርጉ ከባባድ ፍንዳታዎች ሲታረስ ውሏል፡፡

ከትናንት በስቲያ ፑቲን "ቀይ መስመሬ ነው!" ያሉት ክሬሚያን ከሩሲያ የሚያገናኘው ግዙፉ ድልድይ በከባድ ፍንዳታ እንዳልነበር ሆነ፡፡ ሩሲያ "ይህን ድልድይ መምታት በቀጥታ የኒኩሌር ጦርነት ከማወጅ እኩል ነው!" ብላ ስትዝት የሰነበተችበት ይህ ቀይ መስመሯ ፥ በምዕራባውያን "አይዞሽ በርቺ" በምትባለው ዩክሬን በአደባባይ ታለፈ፡፡

መላው አለም በተለይም አውሮፓውያን በፍርሃት መራድ የጀመሩት ፥ " ሞስኮ ለዚህ የቀይ መስመር መታለፍ የምትሰጠው የአፀፋ ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል?" የሚለውን ጉዳይ ማሰብ ከጀመሩበት ደቂቃ በኃላ ነበር፡፡ " የኒኩሌር ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች!" ብለው መላምታቸውን ያስቀመጡ ሁሉ ፥ በ24 ሰአት ውስጥ ከመሬት በታች የተሰሩ የዋሻ መኖሪያ መንደሮችን የቤት መሸጫ ዋጋ ከፍ አደረጉት፡፡

በዚህ መካከል ሞስኮ ዛሬ ማለዳ ጀምራ ያለእረፍት የዩክሬንን ዋና ከተማ ኬቭ ፥ በተምዘግዛጊ ሚሳኤሎቿ ስታርሳት ውላለች፡፡ ከጥቃቱ በኃላ የጦር ጀነራሏን የቀየረችው ሩሲያ ዛሬ ለሰአታት በፈፀመችው ጥቃት በ8 ክልሎች ላይ 11 መሰረተ ልማቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው የዩክሬኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዴኒስ ሺምይጋል ሲገልፁ ፥ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በበኩላቸው " ሩሲያ የዩክሬንን ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት እየጣረች ነዉ!" ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ጥቃቱ በሰው ህይወትና በመሠረተ ልማቶች ላይ ከባድ ጉዳት አስከትሏል፡፡

ለማንኛውም ኬቭ የዛሬውን ቀን በእሳትና በጭስ ታፍና በምድር አንቀጥቅጥ ፍንዳታ እየታመሠች ውላለች፡፡ የአዳሯን ሁኔታ በተመለከተ ከፈጣሪና ከሩሲያ በስተቀር አንዳችንም ለመገመት አንችልም!

ጓዶች! ትናንት << ይሄ "የውመል ቂያማ/የምፅዓት ቀን" የሚባለው ጊዜ ደርሶ ይሆን እንዴ? >> ብዬ ጠይቄአችሁ ነበር፡፡ አዎ! አለም ወዴት ልታመራ ይሆን ?

ሠላም ለአለም!