Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 40

2022-10-10 21:04:55
ችግሩ የመንግሥት አለመኖር ብቻ ሳይሆን የመንግሥት አለመኖርን ተረድቶ ለመፍትሔ የተነሳ ህዝብ መጥፋቱ ላይ ነው!

ደልቃቃው አሸባሪ ኃይል እዚሁ ምዕራብ ሸዋ - አዲስአበባ አፍንጫ ስር ፥ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገብቷል!
3.9K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 20:30:49
ቢመረንም እንዋጠው!

አብዛኛው የአማራ የፖለቲካ ኤሊት ፥ እርስበርሱ የሚራኮተውና የማይግባባው ፥ አጋጣሚውን ጠብቆ ራሱን ለማንገስ ፥ ዘውዱን በጃኬቱ ኪስ ይዞ ስለሚዞር ነው! ሁሉም የሚፈልጉት መሪ መሆን ብቻ ነው፡፡

በመድረክ ድስኩር ሁሉም " የአማራ ህዝብ ከተደቀነበት የህልውና አደጋ ለመሻገር አንድ ሆኖ ተደራጅቶ መታገል አለበት!" ይሉህና እነርሱ ግን አንድ አይሆኑም፡፡ ስሜትና ፍላጎታቸውን አምቀው ስለህዝብ ሲሉ በአንድነት ቆመው ለጋራ ህዝባዊ አላማ አይታገሉም! ይህን ማድረግ የሞት ሞት መስሎ ይታያቸዋል፡፡

ለዚያም ነው " ስልጣን ለሰጣቸው ሁሉ" እንደህዳር አህያ የሚጫኑት!

በመሆኑም መሠረታዊ አጀንዳቸውን ጥለው እርስበርስ ሲራኮቱና ጠልፎ ለመጣጣል ሴራ ሲሾራረቡ ፥ ሠፊው የአማራ ህዝብ በእነሱ ጦስ የመከራ ቀንበሩን ተሸክሞ የመጣ የሄደውን ግፍ እያስተናገደ የግፍ ዘመን ሄዶ ሌላኛው የግፍ ዘመን ይተካል!

መደማመጥ ፥ መተባበርና መከባበር ያልቻለ ኤሊት ፥ ህዝብን አስተባብሮና አከባብሮ በአንድነት ሊያታግልም ሆነ ሊመራ አይችልም !

ምክንያቱም ህዝብን የሚፈጥረው ፈጣሪ ቢሆንም ፤ የህዝብን ማህበረሰባዊ ስነልቦና ፥ ውስጣዊ አንድነትና የትግል አቅጣጫ ፈር የሚያስይዘው የፖለቲካ ኤሊቱ ስለሆነ ነው!

ይህ ነጭ እውነታ ነው፡፡ ቢመረንም እንዋጠው፡፡ ራሳችንን ፈትሸን መከራ ስለሚዘንብበት ህዝብ ስንል ወደራሳችን እንመለስበት!
3.9K viewsedited  17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 19:03:28
1.3K views16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 19:03:13 የውክልናው ጦርነትና የገባንበት አጣብቂኝ ሀገራዊ የሀይል አሰላለፍ!

"አሸባሪው ትህነግና መንግሥት በአንድ ላይ ሆነው ኤርትራን የሚወጉበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል ብሎ ማሰብ የዋህነት ሊመስለን ቢችልም…! "

ገዢው መንግሥት የሚከተለው የተደበላለቀ የዲፕሎማቲክ የሀይል አሰላለፍ እና መሀል ሰፋሪነት በቀጣይ ምስራቅ አፍሪካን ለሁለት ጎራ ከፍሎ ወደተራዘመ የትርምስ ቀጠናነት እንዳይቀይረው እሰጋለሁ፡፡

አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት በቀንድ አፍሪካ ላይ ያላቸውን የበላይነትና ጥቅም ለማስከበር በተለይም ሀያላኑ ሀገራት ብሎም የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በሁለት ጎራ ተከፍለው የቀይ ባህርን ፖለቲካ በብቸኝነት ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ሽኩቻ ፥ ምዕራባውያኑ ህወሓትን በማጠናከር በይፋ ከሩሲያ ጎን የተሰለፈችውን ኤርትራን እንዲወጋላቸው ያለእረፍት መስራታቸውን ይቀጥላሉ፡፡

በዚህ አሰላለፍ ውስጥ ምዕራባውያኑ የብልጽግና መንግሥት ከኤርትራ ጋር የጀመረውን ስትራቴጂክ አጋርነት በመተው ከህወሓት ጋር ተደራድሮ በመስማማት ኤርትራን እንዲወጉላቸው ያላቸውን ፍላጎት መረዳት እጅግ ቀላል ነገር ነው፡፡

በዚህ ሂደት የኢትዮጵያ መንግስት የጠራ አሰላለፍ የሌለው በመሆኑ አሜሪካ ከሰሞኑ እንኳ በኢትዮጵያና በአሸባሪው ትህነግ ዙሪያ የጎንዮሽ አደራዳሪነት ሚናን በመውሰድ በጅቡቲ እንዲደረጉ ያደረገቻቸው የከሸፉ ሚስጥራዊ ድርድሮች ለዚህ ማሳያዎች ናቸው፡፡

በመሆኑም መንግሥት አንዱን ጎራ በመምረጥ አጣብቂኝ ውስጥ የገባበት ሁኔታ ባለበትና ጦርነቱ በቀጠለበት ሁኔታ ፥ ምእራባውያኑ ህወሓትን በሁለንተናዊ መልኩ የማስታጠቅና የማጠንከር ተግባራቸውን አጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን ለዚህ የውክልና ጦርነት ደግሞ ሱዳንና ጅቡቲን እንደድልድይ መጠቀማቸው አይቀሬና እየተስተዋለም ያለ ጉዳይ ነው፡፡

ታዋቂው አሜሪካዊ የሞስኮ (ሩሲያ) የፖለቲካ ተንታኝ አንድሪው ኮሪብኮ ፥ << በኢትዮጵያ ላይ በተከፈተው ድብልቅልቅ ጦርነት ውስጥ የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ ሱዳንን እንደ ተኪዎቻቸው እየተጠቀሙባት ነው! >> በማለት ሱዳን ለህወሓት ትጥቅ ለማስታጠቅ ለሚደረጉ በረራዎች እንደመተላለፊያ ድልድይ ሆና በምዕራባውያን መመረጧን ያተተበት ሁኔታ ለዚህ በቂ ማሳያ ነው፡፡

በሌላ መልኩ ከጊዜ ወደጊዜ እየሻከረ የመጣው የጅቡቲና የኤርትራ የዲፕሎማቲክ ግንኙነትና ጅቡቲ ከሰሞኑ ወታደሮቿን ወደኤርትራ ድንበር ማስጠጋቷ ፥ የምእራባዊያን በአፍሪካ ቀንድ ላይ የሚከተሉት አሰላለፍና ቀጣይ የውክልና ጦርነቱ ድግስ አንድ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

በሌላ መልኩ ገዢው መንግስት ከገጠመው አለማቀፋዊ የዲፕሎማሲ መታጎልና ኪሳራ ባሻገር ውስጠ - ፖለቲካውን መቆጣጠርና መምራት አለመቻሉ ይዞት የሚመጣው መዘዝ ትንሽ ገዘፍ ያለ ሊሆን ይችላል፡፡

በተለይም ከጦርነቱ አጋማሽ በኃላ ህወሓት የኤርትራና የአማራ ህዝብ ብቻ ቋሚ ጠላት እንደሆነ በመገምገም ፥ " ሁለቱ ህዝቦች የሚኖራቸው ስትራቴጂክ አጋርነት ለስልጣኔ ያሰጋኛል" በሚል ስሁት ብያኔ ፥ ብሎም የጦርነቱ የመጀመሪያው ምእራፍ መጠናቀቅ በኃላ ከኤርትራ ጋር "የወጪ ኪሳራ ስሌት" ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ጉልህ ያልሆኑ መቃቃሮችና የሚያራምደው የመሀል ሰፋሪ አሰላለፍ እንዲሁም የኤርትራ መንግሥት የአማራን ወጣቶች ወታደራዊ ስልጠና ለመስጠትና ለመደገፍ በግልፅ አቋም መያዙ ፥ የሁለቱን ሀገራት መፃኢ ግንኙነት ወደውጥረት እየከተተው እንደሚገኝ ከሁኔታዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ በነገራችን ላይ በአማራ ክልል ከፋኖ ጋር በተያያዘ መንግሥት የሚያራምደው አቋም ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

በመሆኑም ገዢው መንግሥት አንድም ከምዕራባውያኑ ጎራ በይፋ መነጠልና በእነሱ በኩል የሚመጣን ማንኛውም አደሳዳሪነትም ሆነ ግንኙነት መዝጋት አለያም በእነሱ ምክረ-ሀሳብ መስማማት በሚሉ ሁለት አማራጮች ውስጥ እንደወደቀ ይሰማኛል፡፡

በዚህ ሁኔታ "አሸባሪው ትህነግና መንግሥት በአንድ ላይ ሆነው ኤርትራን የሚወጉበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል" ብሎ ማሰብ የዋህነት ሊመስለን ቢችልም ፥ መንግሥት አሰላለፉን በምዕራባውያን በኩል ካደረገ ደግሞ ከህወሓት ጋር በሚያቀርቡት ሀሳብ መሠረት ተስማምቶ ፥ በቀጣይ ኤርትራን በይፋ እንዲወጋ ፍላጎት እንደሚኖራቸው ፥ ዛሬ እብደትና የማይመስል ድስኩር ቢመስለንም ውለን እያደርን የምናረጋግጠው ያፈጠጠ እውነታ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

በዚህ መሀል የአማራ ህዝብና የሀገሪቱ መፃኢ እጣፋንታ ምን ያህል ፈታኝ ሁኔታዎች እንደተጋረጠባቸው በበቂ ሁኔታ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ሠላም!
1.5K viewsedited  16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 22:43:46 በጥራቃውን መንግሥት እንዳይሻሻልና እንዳይድን አድርገው ወደባሰ ቁልቁለት እያወረዱት የሚገኙት ፥ መንግስታዊ ውሸቱን ከስር ከስሩ በጅምላ እየተረከቡ ለሰፊው ህዝብ የሚቸረችሩት ቸርቻሪዎቹ ናቸው!

አዎ! ህመምን ሳይባባስ ፊት ለፊት ተናግሮ መታከም እየተቻለ ህመምተኛው "ደህና ነኝ!" ሲል ከስር ከስር እየተከተሉ "ደህና ነው ፥ ከበፊቱም በጣም ተሻሽሏል ፥ አያሰጋውም!" በማለት ፥ የመዳን ተስፋውን አሟጠው ወደመቃብር የሚገፉት ውታፍ ነቃዮቹ ናቸው!
282 views19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 20:54:21
ኦነግ ከአዲስአበባ በቅርብ ርቀት ጥቃት እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ!

አሸባሪውና ያለከልካይ የሚፈነጨው የኦነግ ጨፍጫፊ ሰራዊት ሙሉ ወለጋን አካሎ ወደሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የሚያደርገውን የሽብር እንቅስቃሴ በማስፋፋት  በዛሬው እለት ከአዲስአበባ በቅርብ ርቀት በምትገኘው  ፥ ምእራብ ሸዋ ዞን ጨሊሞ ከሚባል አካባቢ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃትና ዘረፋ  እየፈፀመ  እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

ከትናንት በስቲያ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ ዳሊ ዳክ ቀበሌ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአሸባሪው ቡድን ሀይል ጭፍጨፋ ለመፈፀም መስፈሩን ተከትሎ ከፍተኛ ስጋት ላይ የወደቁትን ነዋሪዎች የድረሱልን ጥሪ መዘገቤ የሚታወስ ነው፡፡
1.9K views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 18:35:02
የትግራይ ህዝብ " ለእናንተ እብሪትና የስልጣን ጥም ወደ እሳት አልማገድም!" ማለት እስካልጀመረ ድረስ ነፍሰበላው ትህነግ ፍፁም አርፎ አይቀመጥም!

ለዚህ ማሳያው በሰሜን ወሎ ለወረራ አሰልፎ ያስጨፈጨፋቸውን  የትግራይ ወጣቶች አስከሬን ለመቅበር እንኳ አልችል ብሎ  በየጫካው ከምሯቸው ፈርጥጦ ፥ አርሷደሩ ወደማሳው መሄጃ አጥቶ አቅሙ በቻለው ለመቅበር እየታገለ ባለበት ሁኔታ  ተጨማሪ የሚጨፈጨፍ የትግራይ ወጣቶችን ወደተለያዩ የሰሜን ወሎ አካባቢዎች (ጀመዶ) ማስጠጋት ጀምሯል!

ለማሳያ በቪዲዮው የቀረበው ፥ ቡድኑ ከመፈርጠጡ በፊት በነበሩ ውጊያዎች በየጥሻው ከምሮት የሄደው  ለቀባሪ ያስቸገረው የትህነግ ወራሪ ሀይሎች አስከሬን ነው!
2.8K viewsedited  15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 17:23:04 ፖለቲካዊ አላማ ፥ ግብና የሀሳብ መስመርህ  የጠራ ከሆነ ፥ ባልተራዘመና ባልተንዛዛ ትግል አሸናፊ ትሆናለህ! 

በረዥም ጊዜ ግላዊ ግምገማዬ ፥ በተለይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ አብዛኛዎቹ " የሚያስፈልገን ጥገናዊ ለውጥ እንጂ ስር ነቀል ለውጥ አይደለም!" ብለው የሚያምኑ reformist ሀይሎች አድርባይና በተቃውሞው ጎራም ሆነ በገዢው ሀይል እኩል መወደድ የሚሹ መሀል ሰፋሪዎች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ 

የኢትዮጵያን በጥላቻ ትርክት ላይ የተመሠረተ የፅንፈኞች ደም አፋሳሽና አውዳሚ ፖለቲካዊ ስርአት ፥ በዘመን ሂደት ውስጥ በሚገባ ለገመገመ ግን ፖለቲካችንም ሆነ ሀገረ-መንግስታዊ ስርአቱ የሚያስፈልገው  ስር-ነቀላዊ ለውጥ (revolution ) መሆኑን በውል ይረዳዋል፡፡

"ብአዴናዊነት እኩይ የአስተሳሰብ ደዌ ነው!" ብለህ ከተረዳህ ፥ ትግልህ ይሄን አስተሳሰብ ነቅሎ መጣል ላይ ብቻ ያተኩራል፡፡ ይህን አቋም ይዘህ ሳለ አንድ የሰፈርህ ወይም ጓደኛና ዘመድህ የሆነ የስርአቱ ካድሬ ሲነካ " ጎጤ ተነጥሎ ተጠቃ!" ብለህ "እሪታ"  የምታቀልጥ ከሆነ ትግልህ የሀሳብ ጥራት የለውም አንተም አቋምና አላማ የለህም ማለት ነው፡፡ ከዚያ ሹማምንት (ድርጅት) በምታገኘው ግለሰባዊ ጥቅምና በውስጥህ ካለው የለውጥ ፍላጎት መካከል ሆነህ እያንገላጀህ ነው ማለት ነው፡፡ 

የብአዴናዊነትን አስተሳሰብ ጠላህ ማለት በውስጡ ያሉትን ጠንካራም ሆኑ ደካማ ሰዎች ጠላህ ማለት አይደለም፡፡ ፖለቲካዊ ትግልህ ከአስተሳሰብና ከስርአት እንጂ በወንድሞችህ የመረረ ጥላቻ መለከፍና መታወር ሊሆንም አይገባም፡፡ የመረረ ግለሰባዊ ጥላቻ ማዳበር ወደ ደም አፋሳሽና ከፋፋይ የፖለቲካ ውጥንቅጥ የሚያስገባ መሆኑንም አስተውሎ መገንዘብ ያሻል፡፡

ትግልህ ከፖለቲካዊ ቡድንና ከአስተሳሰባቸው ጋር ብቻ መሆኑንም እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡ በእኛ ሀገር በግራ ቀኙ ጎራ ፦ የትግራይን የፖለቲካ ሀይሎች መታገልና መቃወም የትግራይን ህዝብ ከመጥላት ፤ የኦሮሞ የፖለቲካ ልሂቃንና አገዛዛቸውን መታገል ወይም መተቸት የኦሮሞን ህዝብ በጅምላ መቃወም አድርጎ የመቁጠር ከንቱ አባዜ ይስተዋላል፡፡ 

ሌላው ቀርቶ ከአንድ ህዝብ መካከል በሚደረግ ትግል የአንዱን አካባቢ የፖለቲካ ቡድን ወይም ፖለቲከኛ መተቸት ሙሉ አካባቢውን የመጥላት ወይም የመቃወም ሂደት እንደሆነ የሚቆጠርበት የነቀዘ ሁኔታን ጧት ማታ እናያለን፡፡ ይህ አይነቱ ከንቱ አስተሳሰብ ሴረኛና ሰነፍ አመራሮችን መደበቂያ ዋሻ እንዲያገኙ ከማድረግና በውስጥ ሽኩቻ ተጠምዶ ከዋና አላማ ከመናጠብ ብሎም የትግልን ሂደት የተንዛዛና አሰልቺ ከማድረግ  በስተቀር አንዳች ለህዝብ የሚጠቅም አወንታዊ ጎን የለውም፡፡

የጠራ የሀሳብና የአላማ መስመር ያለው የፖለቲካ ማህበረሰብ ፥  ከየት ተነስቶ የት መድረስና ብሎም የትኛውን ለይቶ መታገል እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል! ባልተራዘመ ትግልም ከሚፈልግበት ግብ ላይ ይደርሳል!
2.9K viewsedited  14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 15:54:34
....ደርሶ ይሆን እንዴ?

ግዙፉ የክሬሚያ ድልድይ ተመትቷል ...! ፑቱን ያሰመሩት ቀይ መስመርም ታልፏል! ዩክሬንን "አይዞሽ በርቺ" እያሉ በማስታጠቅ ሲያበረታቱ የነበሩት አውሮፖውያንና አሜሪካ እምጥ ይግቡ እስምጥ ጨንቋቸው እየዋተቱ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ በፊት ሩሲያ "ይህን ድልድይ መምታት በቀጥታ የኒኩሌር ጦርነት ከማወጅ እኩል ነው!" ብላ አስጠንቅቃ ነበር፡፡ እነሆ! አሁን ምዕራባውያኑ ባስታጠቋት መሳሪያ ዩክሬን እንዳልነበረ አድርጋ ቀይ መስመሩን አልፋዋለች፡፡ "የሩሲያ አፀፋ ምን ይሆን ?" የሚለው ጥያቄ የመላው አለም ጭንቀት ሆኗል፡፡ አውሮፓውያኑ ዜጎች ከመሬት በታች ያሉ የዋሻ ቤቶችን ገበያ ከፍ አድርገውታል፡፡

ሩሲያ የምትወስደውን የአፀፋ እርምጃ ከትናንት ጀምሮ በእያንዳንዱ ሰከንድ በጭንቀት እየተጠበቀ ነው፡፡ እውነት የኒኩሌር መሳሪያዋን ትጠቀመው ይሆን ? ከዚያስ አለም ወደየት ልታመራ ነው? ይህን በሩሲያ እጅ ላይ የሚቆጥሩት እያንዳንዶቹ ሰከንዶች የሚወስኑት ይሆናል!

አንዳንድ የብልጽግና ካድሬዎች " ዩክሬን 6ተኛውን መርከብ ስንዴ ሳትልክልን መጥፋቷ ይሆን እንዴ? " ብለው ሊጨነቁ ይችላሉ፡፡ እኔ ግን አለም ወደባሰ አጣብቂኝ ውስጥ እየወደቀች መምጣቷ ያሳስበኛል!

ጎበዝ! ይሄ "የውመል ቂያማ/የምፅዓት ቀን" የሚባለው ጊዜ ደርሶ ይሆን እንዴ?
3.0K viewsedited  12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 20:25:53 ጥቁር ገበያ (black market) ምንድን ነው?

"መንግስት ጥቆማ ስጡኝ ከማለቱ በፊት ራሱን ይፈትሽ!"

በርካታ ደካማ ሀገረ-መንግስት ያለባቸውና በእርስበርስ ጦርነት የሚታመሱ ሀገራት ጥቁር ገበያ የተንሰራፋባቸውና ለእንቅስቃሴው አመቺ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

ጥቁር ገበያ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በህገ-ወጥ ፤ ቁጥጥር በማይደረግበት እና ቁጥጥር በሌለው መንገድ የመሸጥ ሂደት ነው፡፡ በንግዱ ህገወጥነት ባህሪ ምክንያትም "ጥቁር ገበያ" ተብሎ ይጠራል፡፡

የጥቁር ገበያ መንግሥት አንዳንድ ህገ-ወጥ ወይም ከተፈቀደላቸው አካላት ውጪ እንዳይገቡ ብሎ የከለከላቸውን ምርቶች ለማስገባትና በውድ ዋጋ ለመሸጥ ሲባል ሊጀመር ይችላል፡፡ የቁጥጥርና የህግ-ማስከበር ስርአቱ ደካማ የሆነ መንግሥት ከሆነ ሂደቱ ከቁጥጥር ውጫ ሆኖ የሀገርን ኢኮኖሚ በማሽመድመድ ፣ የዜጎችን ኑሮ በማበሰቋቆልና የአቅርቦት ችግርን በመፍጠር እጅግ አስከፊ ወደሆነ አዘቅት የማውረድ አቅም አለው፡፡

ጥቁር ገበያ በሰንሰለቱ ውስጥ ያሉትን ከባለሀብቶች ጀምሮ የመንግሥት ባለስልጣናትና ቸርቻሪዎችን በአጭር ጊዜ የናጠጡ ሀብታሞች የሚያደርግ ቢሆንም በሀገርና በህዝብ እንዲሁም በመንግሥት ላይ በርካታ ተፅዕኖዎችን ያሳድራል፡፡

ከነዚህ ተፅዕኖዎች መካከል ፦

ጥቁር ገበያ እንደ ዕፅ፣ የጦር መሣሪያ እና ሌሎች የተከለከሉ አደገኛ ሸቀጦችንና ሕገወጥ ምርቶች እንቅስቃሴን ያመቻቻል።

ሰዎች ለዝሙት አዳሪነት ተሽጠው በውጭ አገር በባርነት የሚሠሩበትን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ጨምሮ የሰው ልጅ የአካል ክፍሎች ሽያጭን ያበረታታል።

ጥቁር ገበያ አሸባሪዎችን ለማስታጠቅ እና ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለአሸባሪዎች ለመሸጥ እንደ መንገድ ሊያገለግል ይችላል።

በገበያው ውስጥ ደንብ ባለመኖሩ ገዢዎች በጥቁር ገበያ የመታለል ዕድላቸው ከፍተኛ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

በጦር መሳሪያ ንግድ እና ህገወጥ ድርጊቶችን በመፈፀም ብዙ ገንዘብ የማግኘት ፍላጎት እየጨመረ ስለሚመጣ የጥቁር ገበያ የወንጀል መጠን እንዲጨምር ዋና ምክንያት ሊሆን ይችላል።

ጥቁር ገበያው በታክስ ስወራ ስለሚታመስና በዘርፉ የተሰማሩት አካላት ለሚያቀርቡት ሸቀጥም ሆነ አገልግሎት ግብር ስለማይከፍሉ ፥ የሀገር ገቢና ኢኮኖሚ እንዲያሽቆለቁል ያደርጋል፡፡

በጥቁር ገበያ የሚሸጡት እቃዎች ዝቅተኛ ጥራት ያላቸው እና በዋስትና ያልተሸፈኑ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የጥቁር ገበያው ዋጋ አነስተኛ በሆኑ ምርቶች ላይ የሚሸጥ ሲሆን ይህም ስለ ኢኮኖሚው ሁኔታ የተሳሳተ ግንዛቤ ሊፈጥር ይችላል።

በጥቁር ገበያው የሚገቡ ሸቀጦች ፦ ለምሳሌ የጦር መሳሪያ ፣ ፣መድሀኒቶች ፣ ማሽነሪዎችና ኤሌክትሮኒክሶች ፥ ….ወዘተ የመሳሰሉት ከህጋዊ መሸጫ ዋጋቸው የቀነሱ ስለሚሆኑ ገዢዎች ታክስና ቀረጥ የሚወጣውን ወጪ ለመቀነስ ተመራጭ ስለሚያደርጓቸው ህብረተሰቡንም የድርጊቱ ተባባሪ የማድረግ እድል ይፈጥራሉ፡፡

በመደበኛው የፋይናንስ ስርአት ውስጥ የሚዘዋወረውን ምንዛሬ እንዲያሽቆለቁል በማድረግ ፥ ከፍተኛ የሆነው የውጭ ምንዛሬ ዝውውር ከመንግሥት ቁጥጥር ስርአት ውጭ ባለው በዚህ የጥቁር ገበያ ስርአት ውስጥ እንዲንቀሳቀስ ያደርገዋል፡፡ በግለሰብም ሆነ በተቋም ደረጃ የሚከወኑ ህገ-ወጥ የሀዋላና የገንዘብ ማዘዋወሪያ ስርአቶች ለዚህ አይነተኛ ሚና የሚጫወቱ ይሆናሉ፡፡

ከላይ የተጠቀሰውን ጨምሮ የጥቁር ገበያ ተፅዕኖ እጅግ በርካታና ፈታኝ አረንቋ ውስጥ የሚከት ሲሆን ፥ ይህንን እንቅስቃሴ ለማስቆም የሚችል ጠንካራ መንግስታዊ ስርአት በሌለበት ብሎም የመንግሥት አካላትና ባለስልጣናቱ ከእነዚህ የጥቁር ገበያ ሰንሰለቶች ጋር በጣምራ በሚሠሩበት እንዲሁም ማህበረሰቡ የንቃተ ደረጃ ዝቅተኛ በሆነበት እንደኛ ሀገር ወቅታዊ ሁኔታ ፥ በህዝብና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከሚፈጥረው ሁለንተናዊ ችግር ባሻገር ሀገርን እስከማፍረስ የደረሰ አስከፊ ውጤት ሊኖረው ወደሚችል ሀገራዊ ምስቅልቅል ሊያደርስ ይችላል፡፡
1.9K viewsedited  17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ