Get Mystery Box with random crypto!

ቢመረንም እንዋጠው! አብዛኛው የአማራ የፖለቲካ ኤሊት ፥ እርስበርሱ የሚራኮተውና የማይግባባው ፥ | ዘሪሁን ገሠሠ

ቢመረንም እንዋጠው!

አብዛኛው የአማራ የፖለቲካ ኤሊት ፥ እርስበርሱ የሚራኮተውና የማይግባባው ፥ አጋጣሚውን ጠብቆ ራሱን ለማንገስ ፥ ዘውዱን በጃኬቱ ኪስ ይዞ ስለሚዞር ነው! ሁሉም የሚፈልጉት መሪ መሆን ብቻ ነው፡፡

በመድረክ ድስኩር ሁሉም " የአማራ ህዝብ ከተደቀነበት የህልውና አደጋ ለመሻገር አንድ ሆኖ ተደራጅቶ መታገል አለበት!" ይሉህና እነርሱ ግን አንድ አይሆኑም፡፡ ስሜትና ፍላጎታቸውን አምቀው ስለህዝብ ሲሉ በአንድነት ቆመው ለጋራ ህዝባዊ አላማ አይታገሉም! ይህን ማድረግ የሞት ሞት መስሎ ይታያቸዋል፡፡

ለዚያም ነው " ስልጣን ለሰጣቸው ሁሉ" እንደህዳር አህያ የሚጫኑት!

በመሆኑም መሠረታዊ አጀንዳቸውን ጥለው እርስበርስ ሲራኮቱና ጠልፎ ለመጣጣል ሴራ ሲሾራረቡ ፥ ሠፊው የአማራ ህዝብ በእነሱ ጦስ የመከራ ቀንበሩን ተሸክሞ የመጣ የሄደውን ግፍ እያስተናገደ የግፍ ዘመን ሄዶ ሌላኛው የግፍ ዘመን ይተካል!

መደማመጥ ፥ መተባበርና መከባበር ያልቻለ ኤሊት ፥ ህዝብን አስተባብሮና አከባብሮ በአንድነት ሊያታግልም ሆነ ሊመራ አይችልም !

ምክንያቱም ህዝብን የሚፈጥረው ፈጣሪ ቢሆንም ፤ የህዝብን ማህበረሰባዊ ስነልቦና ፥ ውስጣዊ አንድነትና የትግል አቅጣጫ ፈር የሚያስይዘው የፖለቲካ ኤሊቱ ስለሆነ ነው!

ይህ ነጭ እውነታ ነው፡፡ ቢመረንም እንዋጠው፡፡ ራሳችንን ፈትሸን መከራ ስለሚዘንብበት ህዝብ ስንል ወደራሳችን እንመለስበት!