Get Mystery Box with random crypto!

ኦነግ ከአዲስአበባ በቅርብ ርቀት ጥቃት እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ! አሸባሪውና ያለከልካይ የሚፈነጨው | ዘሪሁን ገሠሠ

ኦነግ ከአዲስአበባ በቅርብ ርቀት ጥቃት እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ!

አሸባሪውና ያለከልካይ የሚፈነጨው የኦነግ ጨፍጫፊ ሰራዊት ሙሉ ወለጋን አካሎ ወደሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የሚያደርገውን የሽብር እንቅስቃሴ በማስፋፋት  በዛሬው እለት ከአዲስአበባ በቅርብ ርቀት በምትገኘው  ፥ ምእራብ ሸዋ ዞን ጨሊሞ ከሚባል አካባቢ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃትና ዘረፋ  እየፈፀመ  እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

ከትናንት በስቲያ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ ዳሊ ዳክ ቀበሌ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአሸባሪው ቡድን ሀይል ጭፍጨፋ ለመፈፀም መስፈሩን ተከትሎ ከፍተኛ ስጋት ላይ የወደቁትን ነዋሪዎች የድረሱልን ጥሪ መዘገቤ የሚታወስ ነው፡፡