Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 38

2022-11-25 16:21:07
3.6K views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 16:20:43 የብርቱካን ሚደቅሳው ምርጫ ቦርድ ያስቀጠለው ፥ የትኛውን የመርጋ በቃና ሌጋሲ ነው?

በወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፥ በተስፋ አስቆራጩ የኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲና የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ውስጥ በአሰራር ረገድ እንኳ ጥቂትም ቢሆን የተስፋ ብርሀን ፍንጣቂን ሊያሳየን በመቻሉ ፥ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታው እጅግ አስፈላጊ የሆኑት ተቋማት "ተቋም" እንዲሆኑና እንዲጎለብቱ እንደሚሻ ዜጋ "በርቱ ፥ ተበራቱ …!" ብለን በይፋ አጋርነታችንን ሰጥተናል፡፡

ነገርግን ከዚህ ቀደም በነበሩበት እነመርጋ በቃናና አዲሱ ገ/እግዚያብሔርን መሠል የኢህአዴግ ሠዎች ይመራ እንደነበረውና "የኢህአዴግ ቁ.2 ፅ/ቤት" እስከመባል የደረሰው ምርጫ ቦርድ ፥ በመንግሥት እዝና ፖለቲካዊ ተፅእኖ ውስጥ ገብቶ ፥ የተሻለ ተገዳዳሪነትና ህዝባዊ ቅቡልነት ያላቸውን የፖለቲካ ድርጅቶችን "ድምፅ አልባ ሞት" እንዲሞቱና በሂደት ተዳክመው ህዝባዊ ቅቡልነት እንዲያጡ ፥ ሲያደርግ የነበረው ስትራቴጂካዊ ሌጋሲ ፥ ሂደቱ ፣ ስልቱና አፈፃፀሙ ቢለያይም ፥ በወ/ሪቷ በሚመራው ቦርድም ተጠናክሮ የቀጠለ ይመስለኛል፡፡

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክ "ቅንጅት" ኃላም "አንድነትን" የመሠሉ ሠፊ ህዝባዊ ቅቡልነትና አደረጃጀት የዘረጉ ፓርቲዎችን ፥ የቁም ሞት እንዲሞቱ አድርጎ ፥ ስያሜአቸውን " አየለ ጫሚሶና ትእግስቱ አወሉ" ለሚባሉ የሳምሶናይት ፓርቲ ተረካቢዎች በመስጠት የዴሞክራሲያዊ ትግሉን ተስፋ አስቆራጭና እምነት የማይጣልበት ካደረጉት ኃይሎች መካከል የምርጫ ቦርድ ሚና ከፍተኛው ነበር፡፡ ከዚያ በኃላም በሠማያዊ ፣ በመኢአድ ፣ ….ወዘተ ፓርቲዎች ውስጥ ፥ ሶኬቱ ከገዢው የኢህአዴግ/ህወሓት ስልጣን ስር የተሰካው የምርጫ ቦርድ እጅ እንደነበር የሚካድ አይደለም፡፡

በሌላ መልኩ ጠንካሮቹን ካኮሰመኑ ፥ ከፋፍለውና ለመንግሥት እጅ አስታጣቢ ሊሆን ለሚችለው አካል በገፀ-በረከትነት ከሰጡ በኃላ ፥ እርባና ቢስና በያኔው አገላለፅ "አጋር ፓርቲ" ተብለው ለምርጫ ጊዜ ብቻ የሰርተፍኬታቸውን አቧራ አራግፈው " ብቅ " የሚሉ "ኢሰዴፓን" መሠል የግለሰቦችና የቤተሰብ ድርጅቶች "ፓርቲ" ተብለው ፥ የመሮጫ ትራኩና የፌክ ትግል መድረኩ እንዲመቻችላቸው የማድረጉንም ሀላፊነት ምርጫ ቦርድ ከፊት ሆኖ ይመራው እንደነበርም የሚታወስ ነው፡፡

በቅርቡ የመነቃቃት ሂደትን አሳይቶ በነበረው የፓርቲዎች የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ውስጥ ፥ ሰፊ ህዝባዊ መሠረትና ቅቡልነት ማትረፍ ከቻሉት ፓርቲዎች መካከል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው፡፡

የእነዚህ ፓርቲዎች አብዛኛው ችግር ውስጣዊና የአመራር ችግር ሲሆን ፥ ይህን ችግር በመፍጠር ረገድ መንግስት ለምክንያት የሚጠቀስ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ነገርግን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን በሚመለከት በተለየ ሁኔታ የምርጫ ቦርድ "ፓርቲውን ድምፅ አልባ በሆነ መልኩ ቀስ በቀስ እንዲሞት ህግን ባለማስከበር ፥ ውሳኔን ባለማስተግበር ብሎም ሀላፊነትን ባለመወጣት በጉልህ ተባባሪ ሆኖ እየተመለከትነው እንገኛለን፡፡

በመሆኑም ፦ እነዚህ ፓርቲዎች ከምርጫ በኃላ ያሉበት ሁኔታ ምን ይመስላል ? የፓርቲዎቹ ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮትስ ከቅንጅትና ከአንድነት ፓርቲዎች በምን ይመሳሰላል? በምንስ ይለያያል ? በተለይ ከሁለቱ ፓርቲዎች በውስጣዊና በውጫዊ ፈተና ውስጥ የወደቀው አብንን በሚመለከት የምርጫ ቦርድ አስተዋፅኦ ምንድን ነው ? ህዝባዊ ቅቡልነት በማጣት ረገድ ሁለቱም ተመሳሳይ ቢሆኑም ፥ ጉባኤውን አካሂዶና በምርጫ ቦርድ ሂደት ካለፈው ኢዜማና ጉባኤውን በተደጋጋሚ ሞክሮ ማድረግ ካልተሳካለት አብን እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ያለው ማን ነው ? የአብን ጉዳይስ ለምን እጅግ ተጠባቂና ሰፊ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆነ ? ምንስ መደረግ አለበት ?

በቀጣይ የምመለስባቸው የሀሳብ መነሻ ጥያቄዎቼ ይሆናሉ!

ሠላም!
4.9K views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 18:51:01
እንደ ሃገርስ ቢሆን ይሄን ቋሚ ገመና ተሸክመን የት ልንደርስ ነው?

// አቶ የሱፍ ኢብራሒም//

ወለጋ ውስጥ በአማራዎች ላይ የሚፈፀመው የዘር ጭፍጨፋ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሚያሳዩ መረጃዎች ደርሰውናል።

በዚህ መሰረት በዛሬው እለት በኪረሙ ወረዳ በህፃናት እና እናቶች ላይ ሳይቀር መጠነ-ሰፊ፣ የተቀናጀ እና ዘግናኝ ጭፍጨፋ እየተካሄደ ነው። አስክሬኖችን ማንሳትና መቅበር እንኳን እንዳልተቻለ ታውቋል።

ይሄ ለእኛ አሳዛኝ ብቻ አይደለም፤ አሳፋሪና አዋራጅም ነው! እንደ ሃገርስ ቢሆን ይሄን ቋሚ ገመና ተሸክመን የት ልንደርስ ነው? ከእንግዲህ ሌላውን ሁሉ ተውት—ከምር የህሌና እዳ ያለብን ወገኖች ትኩረት ሰጥተን መፍትሄ ብንፈልግለት ጥሩ ነው!
1.9K views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 21:18:18 በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ 6 ቀበሌዎች በአሁኑ ሰአት በኦነግ ሸኔ ከበባ ውስጥ ሆነው የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ይገኛሉ!

" እልቂት ከመፈፀሙ በፊት በአስቸኳይ የሚደርስልን አካል ካለ ይታደገን! >> _ ነዋሪዎች

በየጊዜው የእልቂት አድማሱን እያሰፋ የዜጎችን ህልውና ስጋት ውስጥ ጥሎ የሚገኘው "ኦነግ-ሸኔ" በሚል የዳቦ ስም የሚጠራው የሽብር ሀይል ፥ በስፋት ከሚንቀሳቀስባቸውና በየጊዜው ዘረፋና ግድያ ከሚፈፅምባቸው የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች መካከል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ አንዷ ነች፡፡

ይህ ቡድን በወረዳው ካሉ ወደ40 የሚጠጉ ቀበሌዎች መካከል እስከአሁን በይፋ የማይንቀሳቀስባቸው 6ት ቀበሌዎች ብቻ ሲሆኑ ፥ በእነዚህ ቀበሌዎች በብዛት የሚኖሩት አማራዎች ላለፉት 16 ወራት የእርሻ ስራቸውን ትተው ቀን ከሌት ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል ከዚህ ቡድን ጋር እየተፋለሙ እንደሚገኙ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡

ቡድኑ ከሰሞኑ እነዚህን ቀበሌዎች አፀዳለሁ ብሎ በሁሉም አቅጣጫዎች በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ ጥቃት እየሰነዘረ እንደሚገኝ የተናገሩት የአይን እማኞች ፥ ቡድኑ በትናንትናው እለት ምሽት አጥናፉ በተሰኘች ቀበሌ ዘልቆ በመግባት በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት 3 የአንድ ቤተሰብ አባላትን ገድሎ ሁለት በከባድ ሁኔታ አቁስሎ ወደ15 የቀንድ ከብቶቻቸውን መውሰዱን ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ሠአት "አሮጂ" ከተሰኘችው ቀበሌ ላይ ሰፍሮ የሚገኘው የኦነግ ሰራዊት " ለሌቱን ጭፍጨፋ እንደሚፈፅም መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ከስድስቱ ቀበሌዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በእግር ተጉዘው ወደአጎራባቿ የደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ዳርጌ ከተማ እየተሰደዱ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

"ጥቂት ሆነን በኃላ ቀር መሳሪያ ፥ እስከአፍንጫው ዘመናዊ መሳሪያዎች ከታጠቀው ሀይል ጋር ለ16 ወራት ተናንቀን ቆየን፡፡ አሁን ግን ከአቅም በላይ ሆኖብናል ! " የሚለውና በዚህ ሰአት ከቡድኑ ጋር እየተፋለመ ያለው የመረጃ ምንጬ ፥ " ምናልባት እንደዜጋ የሚቆጥረን የመንግሥት አካል ካለ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከመፈፀሙ በፊት ይድረስልን !" ሲል ያሉበትን አሳሳቢ ሁኔታ ገልፇል፡፡

በስፍራው የተወሰነ የክልሉ ልዩ ሀይል ሰራዊት ቢኖርም " ትእዛዝ አልተሰጠንም !" በማለት አንዳችም እርምጃ ከመውሰድና ራሳቸውን ለማዳን እየተፋለሙ ያሉትን አርሶአደሮች ከማገዝ መቆጠቡን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

" ምናልባት ለሊቱን የሚፈጠረው አይታወቅምና መንግሥት በአፋጣኝ ይድረስልን" የሚሉት የመረጃ ምንጮቼ ፥ "የሽብር ቡድኑ ስናይፐር ፣ መትረየስና ዲሽቃ የመሳሰሉትን የርቀት መሳሪያዎች የታጠቀ በመሆኑ በቀላሉ ማጥቃት በሚችልበት ቦታ ሁኖ በከበባ ውስጥ ነን" ሲሉ አሳስበዋል ፡፡

መረጃውን #ሼር በማድረግ ለተጨነቁት ወገኖቻችን ድምፅ እንሁናቸው!
3.0K views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 20:58:37 አሁንም የሚያስፈልገው ….!

ሠላም አለርጂክ ከሆነበት አሸባሪ ቡድን ጋር የተደረገን የትንፋሽ መሠብሰቢያ ወሬ በማጣቀስ " የሰላም ስምምነቱ ….!" የሚል መድረክ እያዘጋጁ በጀት ከመጨረስና ደንቁሮ ከማደንቆር ፥ አቅምን አፈርጥሞ ትህነግን እስከወዲያኛው መቅበር ለዘላቂ ሠላም ዋስትና ነው!

በዚህ የድርድር ሂደት ውስጥ በሁለቱም ጎን የተሳለ ቢላ ይዞ እንደመቁረጥ ያለ አድቫንቴጅ ከተገኘ ለመጠቀም ካልሆነም ትንፋሽ ለመሠብሰብና ከዚህ ቀደም ጠቅላዩ እንዳሉት ጥቂት የሚሹለኮለኩ አውሮፕላኖች ትግራይ እየገቡ መሳሪያዎችን አራግፈው እስኪጨርሱ ካልሆነ በስተቀር ትህነግ ለሰላም የተፈጠረ ድርጅት አይደለም፡፡ ሠላም በራሱ የትህነግ ተቃራኒ ቃል ነው፡፡

ስለዚህ ሌላ ሌላ የውርክብ አጀንዳዎችን ገታ አድርጎ ፥ ምሽግ እየቆፈረና ለወረራ እየተሰናዳ ያለውን አሸባሪ ሀይል በአጭር ጊዝ በተቀላጠፈ ጦርነት ዳግም ስሙ እንዳይነሳ አድርጎ ለመቅበር ሳይዘናጉ ቆፍጠን ብሎ መሠናዳት ያስፈልጋል!

ሠላም በአንድ ወገን ፍላጎት ሊረጋገጥ አይችልም! ያለፍትህና ተጠያቂነትም ዘላቂ ሠላም የለም!
4.4K viewsedited  17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 16:02:05
2.9K views13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 16:01:51 መንግስታዊ ሽፋን የተሠጠው ረፍት-የለሽ ፍጅትና የኦሮሚያ ክልል!

ባለፈው በአርሲ ዞን በጀጁ ወረዳ መንበር ሂወት ከሚባል አካባቢ ጭፍጨፋ ከመፈፀሙ አስቀድሞ " ተከበናል ድረሱልን" ሲሉ ነዋሪዎቹ አስተጋቡ፡፡ የክልሉ ልዩ ሀይል ለይስሙላ ወደአካባቢው መጥቶ ማህበረሰቡ በሬ እያረደ ጭምር ሲንከባከበው ቆይቶ ፥ ልክ ጭፍጨፋው በተፈፀመበት እለት ነዋሪዎች "አትውጡብን" እያሉ "ሌላ ግዳጅ አለብን!" ብለው ሲወጡ ፥ ወዲያውኑ ጨካኙ ቡድን ያንን ግፍ ፈፀመ፡፡

በተመሳሳይ ትናንት በዚሁ አካባቢ አዲስ ህይወት ቀበሌ አንዲት እናትን ከነህፃን ልጇ ጨምሮ 9 ሰዎች አሰቃቂ ሁኔታ ማንነትን መሠረት ያደረገ ጭፍጨፋ ሲፈፀምባቸው የክልሉ ልዩ ሀይል በስፍራው አልነበረም፡፡ እርግጥ ነው ቢኖርም አንዳች ነገር እንደማያደርግ አለያም ተባባሪ ሊሆን እንደሚችል ጭምር ፥ ላለፉት አመታት ከደረሱት የጉሊሶን መሠል እልቂቶችና የዘር ፍጅቶች መገንዘብ እንችላለን፡፡

በኦሮሚያ ክልል ላለፉት ከአራት በላይ አመታት ያለእረፍት በየቀኑ ፍጅት እና እልቂት እየተፈፀመ ፥ ሚሊየኖች የሞት ስጋት አንዣቦባቸው ፣ ሚሊየኖች እየተሳደዱ ባለበት ሁኔታ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ተቀዳሚ ሀላፊነት ያለበት የፌደራሉም ሆነ የክልሉ መንግስት ማስቆም አለመቻላቸውም ሆነ አለመፈለጋቸው ጭፍጨፋውን በመንግስታዊ ሽፋን የሚፈፀም የዘር ማጥፋት ያደርገዋል፡፡

በዳቦ ስሙ "ኦነግ ሸኔ" እየተባለ የሚጠራው ጨፍጫፊ ሀይል ራቅ ካሉት የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች አልፎ ፥ ለማዕከላዊ መንግስት መቀመጫዋ አዲስአበባ አቅራቢያ ባሉ የምዕራብና የምስራቅ ሸዋ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች መሠል እልቂትና ሽብር እየፈፀመ እንዳሻው መንሰራፋቱ የክልሉን መንግሥት መፍረስ በግልፅ የሚያስረዳ ነው!

የኢትዮጵያ የሠብዓዊ መብት ኮሚሽን ፥ አለምአቀፍ ተቋማት ፥ የተለያዩ የሲቪል ማህበራት እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጭምር ፥ ይህን ለአመታት የተለመደ ዜና የሆነ ማንነት ተኮር የዘር ፍጅትና ጥቃት ለማስቆም ብሎም ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው የመንግሥት አመራሮችን ጨምሮ አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ካልቻሉ ይህ ሁኔታ በቀጣይ ሀገር ሊያፈርስ ብሎም የእያንዳንዳችንን ቤት ሊያንኳኳ የሚችል ብሔራዊ የደህንነት ስጋት መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡

ፈጣሪ የሟቾቹን ነፍስ ይማር!
2.9K views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 16:18:01 በግሌ ጦርነቱ ተጠናቆ ወይም ነፍሰበላው ትህነግ ስጋት በማይሆንበት ደረጃ ተደምስሶ ቢሆን ኖሮ ፥ ለመንግሥት  "ትህነግ ትጥቅ ይፍታ!" የሚለው ነጥብ መሠረታዊ  የመደራደሪያ ጭብጥ አይሆንም ነበር ብዬ አስባለሁ!

"ትህነግ ትጥቅ ለመፍታት ያስቀመጣቸው ናቸው!" ተብለው በመነገር ላይ ካሉት ፥ ቀላል የሚመስሉ ነገርግን አደገኛና ጨዋታ ቀያሪ ከሆኑ ቅድመ-ሁኔታዎች መካከል  ፦

" የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በይፋ ከሽብርተኝነት መዝገብ ሰርዞኝ ፥ ድጋሜ ምርጫ ተካሂዶ ወደዙፋኔ ልመለስ! >> የሚለው ቀይ መስመር የስምምነቱ አካል ከሆነ ፥ ጉዳዩ ከምናስበውም በላይ ውስብስብና ፥ መጥፋት ያለበት ቡድን ዳግም ከኢትዮጵያ አልፎ የምስራቅ አፍሪካ ስጋት እንዲሆን መፍቀድና እስካሁን በህዝብና በሀገር የተከፈለውን ህልቆ መሳፍርት ዋጋም መና ማስቀረት መሆኑ እሙን ነው!

We will see it!
3.2K viewsedited  13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 13:33:15 "ህወሓት ትጥቅ ይፍታ!" - መንግሥት
" መንግሥት ትጥቅ ማስፈታት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል!" - አጋር ፓርቲዎች

ቅድመ-ሁኔታዎች

" ከሽብርተኝነት መዝገብ ባስቸኳይ ሰርዙኝ!" - ትህነግ
" ድጋሜ ምርጫ ተካሂዶ ህወሓት በሚለው ብራንዴ ልወዳደር!" - ትህነግ
"የኤርትራ ጦር ......!" - ትህነግ
.
.
.
.
ይሄ ነገር እውነት ሊሆን ነው እንዴ?
3.8K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 16:00:33
2.8K views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ