Get Mystery Box with random crypto!

አሁንም የሚያስፈልገው ….! ሠላም አለርጂክ ከሆነበት አሸባሪ ቡድን ጋር የተደረገን የትንፋሽ መሠ | ዘሪሁን ገሠሠ

አሁንም የሚያስፈልገው ….!

ሠላም አለርጂክ ከሆነበት አሸባሪ ቡድን ጋር የተደረገን የትንፋሽ መሠብሰቢያ ወሬ በማጣቀስ " የሰላም ስምምነቱ ….!" የሚል መድረክ እያዘጋጁ በጀት ከመጨረስና ደንቁሮ ከማደንቆር ፥ አቅምን አፈርጥሞ ትህነግን እስከወዲያኛው መቅበር ለዘላቂ ሠላም ዋስትና ነው!

በዚህ የድርድር ሂደት ውስጥ በሁለቱም ጎን የተሳለ ቢላ ይዞ እንደመቁረጥ ያለ አድቫንቴጅ ከተገኘ ለመጠቀም ካልሆነም ትንፋሽ ለመሠብሰብና ከዚህ ቀደም ጠቅላዩ እንዳሉት ጥቂት የሚሹለኮለኩ አውሮፕላኖች ትግራይ እየገቡ መሳሪያዎችን አራግፈው እስኪጨርሱ ካልሆነ በስተቀር ትህነግ ለሰላም የተፈጠረ ድርጅት አይደለም፡፡ ሠላም በራሱ የትህነግ ተቃራኒ ቃል ነው፡፡

ስለዚህ ሌላ ሌላ የውርክብ አጀንዳዎችን ገታ አድርጎ ፥ ምሽግ እየቆፈረና ለወረራ እየተሰናዳ ያለውን አሸባሪ ሀይል በአጭር ጊዝ በተቀላጠፈ ጦርነት ዳግም ስሙ እንዳይነሳ አድርጎ ለመቅበር ሳይዘናጉ ቆፍጠን ብሎ መሠናዳት ያስፈልጋል!

ሠላም በአንድ ወገን ፍላጎት ሊረጋገጥ አይችልም! ያለፍትህና ተጠያቂነትም ዘላቂ ሠላም የለም!