Get Mystery Box with random crypto!

....ደርሶ ይሆን እንዴ? ግዙፉ የክሬሚያ ድልድይ ተመትቷል ...! ፑቱን ያሰመሩት ቀይ መስመርም | ዘሪሁን ገሠሠ

....ደርሶ ይሆን እንዴ?

ግዙፉ የክሬሚያ ድልድይ ተመትቷል ...! ፑቱን ያሰመሩት ቀይ መስመርም ታልፏል! ዩክሬንን "አይዞሽ በርቺ" እያሉ በማስታጠቅ ሲያበረታቱ የነበሩት አውሮፖውያንና አሜሪካ እምጥ ይግቡ እስምጥ ጨንቋቸው እየዋተቱ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ በፊት ሩሲያ "ይህን ድልድይ መምታት በቀጥታ የኒኩሌር ጦርነት ከማወጅ እኩል ነው!" ብላ አስጠንቅቃ ነበር፡፡ እነሆ! አሁን ምዕራባውያኑ ባስታጠቋት መሳሪያ ዩክሬን እንዳልነበረ አድርጋ ቀይ መስመሩን አልፋዋለች፡፡ "የሩሲያ አፀፋ ምን ይሆን ?" የሚለው ጥያቄ የመላው አለም ጭንቀት ሆኗል፡፡ አውሮፓውያኑ ዜጎች ከመሬት በታች ያሉ የዋሻ ቤቶችን ገበያ ከፍ አድርገውታል፡፡

ሩሲያ የምትወስደውን የአፀፋ እርምጃ ከትናንት ጀምሮ በእያንዳንዱ ሰከንድ በጭንቀት እየተጠበቀ ነው፡፡ እውነት የኒኩሌር መሳሪያዋን ትጠቀመው ይሆን ? ከዚያስ አለም ወደየት ልታመራ ነው? ይህን በሩሲያ እጅ ላይ የሚቆጥሩት እያንዳንዶቹ ሰከንዶች የሚወስኑት ይሆናል!

አንዳንድ የብልጽግና ካድሬዎች " ዩክሬን 6ተኛውን መርከብ ስንዴ ሳትልክልን መጥፋቷ ይሆን እንዴ? " ብለው ሊጨነቁ ይችላሉ፡፡ እኔ ግን አለም ወደባሰ አጣብቂኝ ውስጥ እየወደቀች መምጣቷ ያሳስበኛል!

ጎበዝ! ይሄ "የውመል ቂያማ/የምፅዓት ቀን" የሚባለው ጊዜ ደርሶ ይሆን እንዴ?