Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 42

2022-09-28 14:21:39
729 views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 14:21:00 ፋኖ እስራኤልን ምን አድርግ ነው የምትሉት ?

" የመንግሥት ደህንነቶች ስራዬን ተረጋግቼ መስራት እንዳልችል አርገውኛል!"

// ፋኖ እስራኤል እሸቴ - የቀድሞው የምስ/አማራ ፋኖ ም/አዛዥ //

ፋኖ እስራኤል እሸቴ አሸባሪውና ነፍሰበላው የትግራይ ወራሪ ሀይል በህዝባችን ላይ የጥፋት አዋጅ ካወጀበት ጊዜ አንስቶ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ፥ " ቤቴን ፣ ልጆቼን ፣ ስራዬን ፣ ...!" ሳይል ፥ በተለያዩ ግንባሮች ተሰልፎ ከፍተኛ ዋጋ ሲከፍል የኖረ ፥ በተግባር መገለፅን እንጂ እንዲወራለት የማይሻ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው፡፡

እስራኤል በቅርቡ በግንባር ረዥም ጊዜ ከመቆየቱ ጋር ተያይዞ መደበኛ ስራውን መጀመር ካልቻለ ስራውን ሊያጣ በመሆኑና ቤተሰቡን ማስተዳደር ሀላፊነት ስላለበት ፥ ከምስራቅ አማራ ፋኖ በይፋ በመልቀቅ ወደመደበኛ ስራው ተመልሷል፡፡

ይሁን እንጂ የኛ ነገር "ወርቅ ላበደረ ጠጠር..!" ሆነና እስራኤል ካለፉት ወራት ጀምሮ ህይወቱን አደጋ ውስጥ እክከመጣል የደረሰ ማሳደድ ሲፈፀምበት ቆይቶ ፥ አሁን ደግሞ ስራውን ከጀመረ በኃላ ተረጋግቶ ህይወቱን እንዳይኖር የመንግሥት የደህንነት አካላት እስከ መስሪያ ቤት ድረስ በመሄድ የማሳደድና ረፍት የመንሳት ተግባር እየፈፀሙበት እንደሚገኙ ገልፇል፡፡

የመንግሥት የፀጥታ አካላት በጭንቅ ሰአት ወንድ ሆነው የተገኙትንና ለሀገርና ለህዝባቸው ታሪክ የማይሽረው ገድል የፈፀሙ ጀግኖችን ፥ ማመስገንና መደገፉ ቢቀር ተረጋግተው መደበኛ ህይወታቸውን እንዳይመሩ ማድረግ ፈፅሞ ለሞራል ተቃራኒ የሆነ አሳፋሪ ተግባር ነው!

የመንግሥት ሰዎች በፋኖ እስራኤል ላይ የሚፈፀመውን ወከባና ማሳደድ በአስቸኳይ እንድታቆሙ እየጠየኩ ፥ መላው ህዝባችንም ይህን መሠሉን ነውረኛ ተግባር በአንክሮ እንዲከታተለው ለማሳሰብ እወዳለሁ!
784 views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 19:34:21
መንግስታዊ እውቅና የተሰጠው የዘር ማጥፋት!

ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ ያለከልካይ በቀጠለው የወለጋ ጃርደጋጃርቴ የዘር ፍጅት የሟቾች ቁጥር ከ200 በላይ መድረሱን ምንጮች አስታውቀዋል!

ከ4 በላይ አመታትን ያለእረፍት - እልቂት!
ወለጋ በንፁሐን ደም የጨቀየች ምድራዊ ሲኦል!
1.4K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 00:41:30
የአብን ፓርቲ አባላት በመንግስት የስልጣን መዋቅር መካተት ያመጣው ጣጣ… ክፍል 1


173 views21:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 00:30:29
ሪፖርተር - ከአቶ የሱፍ ኢብራሒም ጋር ያደረገውን ቆይታ ክፍል ፪ ይከታተሉት!
226 views21:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 21:56:39
"ለደፋር ሰው ቦታ የለኝም!" - አቶ የሱፍ ኢብራሒም

ለወንድማማችነት ፥ ለፍቅር ፥ ለውይይትና ለመተማመን ካልሆነ ለማደናገሪያና ለስም ጥሪ የሚገብር— ሃጂ ነስረላ የለም!

"ለደፋር ሰው ቦታ የለኝም!" ለማለት ነው። ደፋር ማለት ጀግና ለማለት አይደለም። ለማለት የፈለኩት ከወሎ፣ ከአማራና ከኢትዮጵያ አንዱን ምረጥ ወይም አንዱን ተው የሚሉኝን—ደፋሮች ፤ የሙስሊምና የክርስቲያን ፣ የቆላና የደጋ ፖለቲካ የሚያራግቡ—ደፋሮችን ፤ የአንዱን ጎጥ ህዝብ ነጥለው የሚያንቋሸሹ—ደፋሮችን ፤ በሌላ አካል እስትንፋስና የልብ ትርታ ላይ ተወስነው ውሳኔ ለመጫን የሚመኙ—ደፋሮችን ፤ በነጠላና መለመላ ሆነው "ህዝብ ነን" የሚሉ—ደፋሮችን እንዲሁም በሳንሱር ብርድ ልብስ ለማፈን የሚሹ—ደፋሮችን ነው!

ይኸው ነው!
1.5K views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 23:04:05
እንዲህ አይነቱን ለአንድነትህ የቆመ ጀግና ምልክትህ አድርገው!

<< ስልጣን ይዘው ፤ አማራን መርተው ፣ ከከፍታ ማድረስ ሲገባቸው ሲሽሎኮለኩ ኑረው ፥ አሁን አማራን ለመከፋፈል ጎጃም ፣ ጎንደር ፣ ወሎ ፣ ሸዋ የሚልን ፖለቲከኛ ውሸታም በሉት ፣ እሱን አንቀበልም! >>

// ኮረኔል ደመቀ ዘውዱ//
1.5K viewsedited  20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 22:30:50
ያማል!

ይህ አሰቃቂ ምስል "በወለጋ ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ ዛሬ የተፈፀመ እልቂት ነው!" ተብሎ ሲዘዋወር አየሁ!

ጭፍጨፋው ኦሮሚያ መሆኑ እርግጥ ቢሆንም "መቼና የቱን" ግን ፎቶግራፉን ካሰራጨው አካል ውጭ በርግጠኛነት መናገር ላልችል እችላለሁ፡፡

ሆኖም ይህን መሠሉ አሰቃቂና መፈጠርን የሚያስጠላ እልቂት በወለጋ የእለት ተእለት የተለመደ ዜና መሆኑ እርግጥ ነው!

ኦህ ወለጋ በንፁሀን ደም የጨቀየች የደም ምድር!
4.3K views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 17:02:09
4.4K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 17:01:56 የዘመነ ካሴ እስር የአጠቃላይ የአማራ ብሔርተኝነት ፈተና ነፀብራቅ ነው!

" …እኛም ለስንፍናችንና ለፍርሃታችን ማስተባበያ እየሰጠን የክህደቱ ተባባሪ ሆነናል! " ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማሪያም

1. ምንም ማደባበስና መልመጥመጥ አያስፈልግም። ዘመነ ካሴን አጀንዳ ለማድረግ የተመረጠው ወቅት እጅግ አደገኛ ነው። የአማራ ክልልና ህዝብ በያቅጣጫው በጦርነት ሰቆቃና በስጋት በተወጠረበት በዚህ ቀዉጢ ወቅት ዘመነ ካሴን አታልሎም ይሁን አድፍጦ ማሰር የተጠና እብደት ነው። ሌላ ለመሸፈን ፣ ለማስቀየስ የተፈለገ ጉድ ያለ እንዳለ ይናገራል።

2. የዘመነ እስር አማራን አንገት የማስደፋት ርብርቦሽ አካል ነው። በደጀን ግንባር (home front) የተከፈተብንና አይቶ እንዳላየ ብናልፈውም ያልተላቀቀን ፣ ባለጋራዎቻችን በታላቅ ጥድፊያ ሌት ተቀን የሚሰሩበት አከርካሪ የመስበር ዘመቻ ነው። የሚደረግብን መዋቅራዊ ጥቃት ታሪካችንን ፣ እሴቶቻችንን ፣ ተቋማቶቻችንን ፣ ጀግኖቻችንን ላይ ያነጣጠረ ነው።

3. በተለይ የነፃነታችን ዋስትና የሆነውን ፋኖን ለማንበርከክና ለማጥፋት በተከፈተው ዘመቻ ፣ ከሃዲው መንግሥት ጦርነቱ ሳይቋጭና ፋኖዎቻችን ከቁስላቸውና ከጣመናቸው ሳያገግሙ በአስር ሺዎች እያፈሰና እያሳደደ እረፍት ነስቷቸዋል። እኛም ለስንፍናችንና ለፍርሃታችን ማስተባበያ እየሰጠን የክህደቱ ተባባሪ ሆነናል። ዛሬም ለዘመነም ሆነ ለሌሎች ጀግኖች "ከመሞት መታሰር ይሻላል" እያልን ተንበርካኪነትን እየተቀበልን ነው።

4. አንድ አማራ ሲነካ ሁሉም ይነካል። ዘመነ የአማራ ልጅ የአማራ ታጋይ ነው። ጥፋቱም ልማቱም ሁላችንንም እንደ እናት ልጅ የሚመለከተን ወንድማችን ነው። ጠላቱ ጠላታችን ወዳጁ ወዳጃችን ነው። ያለፍትህ አንዲት የጠጉር ዘለላ እንድትነካበት አንፈቅድም። የዘመነን ጉዳይ የጎጃም ብቻ አድርገህ የምትንገበገብና የማይገናኝ ታሪክ እየቆነፀልክ የምታሳስት ሁሉ ማፈሪያ ነህ።

5. ዘመነን በግል ላትወድደው ፣ በሀሳቡ ላትስማማና ልትቃወመውም ትችላለህ። እንዳባትህ ደመኛ ጉስቁልናውንና ሞቱን የምትመኝና የምታሴር አማራ ከሆንክ ከጠላት ለይቼ አላይህም። በተለይ የአማራ ብሔርተኛ ነኝ ከምትል ከሃዲ ጋር ህብረት አይኖረኝም። ለነገሩ ፋኖን ፋኖ ሲጠላና ለጠላት አሳልፎ ሲሰጥ አላየንም። ፋኖን የሚከፋፍል ፣ በፋኖ ስም የሚነግድና ለጠላት የሚሸጠው በየመንደሩ የሚያውደለድለውና በአማራ ስም የሚነግደው የሚዲያ አርበኛ ፣ ተከፋይ አክቲቪስትና ምንደኛ ፖለቲከኛ ነው።

6. ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ነው። ጥርስ አልባ ትግል ሰላሳ ዓመት ሙሉ ለአልፎ ሂያጅ መዛበቻነትና ለውርደት ዳርጎናል። እንደ ህዝብ መናደድ ፣ መቆጨትና መቆጣት አለብን። በማንኛውም መንገድ መብታችንን ለማስከበር ፣ መሪዎቻችንን ፣ ጀግኖቻችንንና ተቋማቶቻችንን ከአደጋ ለመጠበቅ ቁርጠኛ መሆን አለብን።

በምድር አንቀጥቅጥ ተቃውሞ መንግሥት ለማስገደድ ፣ የጭቆናና የጥቃት መዋቅሮችን ለማፍረስ ፣ መካከላችን ተወሽቆ ጀግኖቻችንን የሚያስበላውን ባንዳ ፣ ምንደኛና ጎጠኛ ዋጋውን እየሰጠን አደብ ማስገዛት ካልጀመርን ለቅሷችን ይቀጥላል።

ምንደኛ ይውደም
4.3K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ