Get Mystery Box with random crypto!

አሁን ይሄ ማስመስገኑ ቢቀር ምኑ ለትችት ይዳርጋል ? የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) በአፍሪካ | ዘሪሁን ገሠሠ

አሁን ይሄ ማስመስገኑ ቢቀር ምኑ ለትችት ይዳርጋል ?

የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) በአፍሪካ ህብረት ስር በሚደረገው ድርድር እንደአንድ የአማራ ተቋም በድርድሩ ለመሳተፍ ያለውን ምክንያታዊ ፍላጎት ገልፆ ፥ በድርድሩ እንዲሳተፉ የመረጣቸውን የአራት ሰዎች ስም ዝርዝር ለሚመለከታቸው አለምአቀፍ ተቋማት ሁሉ ማስገባቱን አስታውቋል!

AAA በአማራ ህዝብ ላይ ተከታታይ የዘር ፍጅትና ማሳደድ ሲፈፀም ተከታትሎ ለአለምአቀፍ ተቋማት በመረጃና በማስረጃ በማጋለጥ ፥ የአማራ ህዝብ በሀገረ-መንግስቱ ለዘመናት የስቃይና የመከራ ገፈት እንዲቀምስ ያደረገውን የተዛባ ትርክት በማረም ረገድና በሁለንተናዊ መልኩ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ያለ ተቋም ነው፡፡

የጦር አውድማ ሆኖ ለአመታት የዘለቀው የአማራ ህዝብ ትህነግ ሀገረ-መንግስቱን ከመቆጣጠሩ በፊት ገና በጫካ እያለ "ጠላት" ብሎ ፈርጆና ትርክት ፈጥሮ ዛሬ ለደረሰበት አስከፊ መከራና ስቃይ ሁሉ የተዳረገ ህዝብ ነው፡፡

ህወሓት በህዝብ ትግል ከሀገረ-መንግስቱ ስልጣን ቢገፋም ፥ ከህገ-መንግስት ጀምሮ የአማራ ህዝብ ስርአታዊና መዋቅራዊ ጭቆና እንዲደርስበት የተዘረጉ አስተሳሰቦችን ተረክቦ ያስቀጠለው ፥ የህወሓት የአብራክ ክፋዩ የብልጽግና መንግሥት ፥ የአማራን ህዝብ የዘር ፍጅትና በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግፍ ፈፃሚና አስፈፃሚ የሆነ በአለምአቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መጠየቅ ያለበት ድርጅት ሆኖ ሳለ ፥ የ1983ቱን ታሪክ ከመድገም ባለፈ ከአሸባሪው ትህነግ ጋር ተደራድሮ የአማራን ህዝብ ዘላቂ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስከብር ብሎም ወደ መፍትሔው የሚያመራ ድርድር ያደርጋል ተብሎ አይታመንም፡፡

በዚህ አውድ ውስጥ AAA ጥያቄው ተቀባይነት አገኘም አላገኘም "በድርድሩ ውስጥ ተሳታፊ መሆን አለብኝ!" ማለቱ ሊያስመሰግን ሲገባና አማራው አንድ እንኳ የሚሞግትለት ተቋም በማግኘቱ መደሰት ሲገባ ስለምን ለማጣጣል ፣ ለመሳለቅና ለመፈረጅ የሚጣደፉ ግለሰቦችን እንመለከታለን ? ተገቢስ ነውን ?

መረገም ነውኮ ጓዶች!