Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 43

2022-09-20 19:21:17
ይህ ግፍና ሰቆቃ የሚያስለቅሰን እኛን እንጂ ፈፃሚ አስፈፃሚውን መንግሥት ሊሆን አይችልም!

"አልቃሻ!" በሉን ግዴለም!
4.9K views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 15:55:48 የስቃይ ማስታገሻ (ማረሳሻ)  መርፌ ከሞት አያድንም!

ከአመታት በፊት "ቁጥር -2 ኢህአዴግ" ወደስልጣን ሳይመጣ አንድ በሆነ ዩኒቨርስቲ የሚያስተምር ፕሮፌሰር ጋር በነበረን ውይይት ፥ ከታች ክፍል ስንማር መፅሀፍት ላይ የነበሩ ምሳሌዎችን በመውሰድ   << ... አማራ እኮ ከበሶ አቅም ለአበበ በሶ አብልቶ ፥ ለጫላ ግን ያስጨበጠው ጩቤ ነው!! .... >> እያለ ሲከራከረኝ ፥ በወቅቱ ሁኔታው የመሠለኝ ቀልድ እንጂ በዚህ በሁሉም ስርአቶች የግፍ ዶፍ በሚያስተናግድና አመድ አፋሽ በሆነ ህዝብ ላይ ፥  ያውም አንድ ትውልድ በመቅረፅ ላይ ባለ ምሁር  ፥ በዚህ  ደረጃ እስከ አጥንት ድረስ የዘለቀ ጥላቻና የተጠቂነት አስተሳሰብ ያዳብራል ብዬ አላመንኩም ነበር!

ነገርግን አሁን በሁሉም መስክ በገሀድ የምናየው ፥ የታሪክ አጋጣሚ እየጠበቀ   ለዘመናት የጥላቻ መርዝ እንደኒኩሌር ሲያብላላ የኖረው ፥ በሀሰተኛ ትርክት የሰከረ ፅንፈኛ የፖለቲካ ቡድን ፥ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያውን በፍፁማዊ ጭካኔ እየተጠቀመው ይገኛል!

ከዚህ አኳያ የአማራ ህዝብ ሰለባ እየሆነ ያለበት ለአመታት የተረጨው ሀሰተኛ የጥላቻ ትርክት ሰንኮፉ እስካልተነቀለና "ህገ-መንግስት" በተሰኘው የሀገር ማፍረሻ ውል የተተከለበት ስርአታዊና መዋቅራዊ ግፍ  ስርአታዊ በሆነ ለውጥ ካልተተካ ካሳለፈውም በላይ የመጪው ጊዜ ከበድ ያለ እንደሚሆን ቅንጣት አልጠራጠርም!

ይህ የሚሆነው ደግሞ የአማራ ህዝብ ጠንካራ የፖለቲካ ማህበረሰብ ሆኖ ፥ አንድነትና ህብረቱን ጠብቆ ፥ በጠራ የፖለቲካ  ግብ ላይ በመመስረት  እንደህዝብ የሞት ሽረት ተጋድሎ ሲያደርግ ብቻ ነው!

አሁን ያለው የትግል አካሄድ "ከስቃይ ማስታገሻ መርፌነት" የዘለለ አንዳችም ጠብ የሚያደርገው ነገር የለም!
6.1K viewsedited  12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 14:11:07
4.7K views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 14:09:03 ዛሬም " ኧረ መንግስት ሆይ ወዴት አለህ?" ማለት ላይ ነን!

ይህና በየጊዜው የምናየው እስከ አፍንጫው የታጠቀና "አሸባሪ" ተብሎም የተፈረጀ ኃይል ፥ ላለፉት አመታት እንዲህ እንደልቡ በየከተሞቹ እየተንቀሳቀሰ ፣ አካባቢዎችንና ተቋማትን እየተቆጣጠረ ብሎም በየጊዜዉ በገፍ አሰልጥኖ እያስመረቀ ጭፍጨፋና ሽብር መፈፀሙን አጠናክሮ የቀጠለው ፥ ኬንያ ወይም ኤርትራ ወይ ደግሞ ኤርትራ በረሀ ላይ ሆኖ ሳይሆን "መንግስት አለሁ!" በሚልበት የኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት እምብርት ላይ ሆኖ ነው!

የአንድ መንግሥት ተቀዳሚና በምንም መልኩ የማይዘነጋ ተግባሩ ከዜጎች ግብር ሰብስቦ የፀጥታ ተቋማትን ገንብቶ የዜጎችንና የሀገርን ደህንነትና ሉአላዊነት ማስጠበቅ መቻል ነው፡፡

ይህን መፈፀም ያቃተው ስርአት ካለ አይቆጠርም፡፡ ከጅምሩ የወደቀ ስርአትም ነው፡፡ የዜጎችን በሰላም ወጥቶ የመግባት ፥ የመንቀሳቀስና የመኖርን ዋስትና ያላስከበረ ፥ የሀገርን ሉአላዊነት መጠበቅ ያልቻለ ስርአተ መንግሥት ስለሌሎች የልማትም ሆነ የተቋማት ስራ የማውራት የሞራል ልዕልናው የለውም፡፡

መንግሥት ይሄን ያፈጠጠ ገሀድ ተቀብሎ ስህተቶቹን በአጭር ጊዜ ማረም ባለመቻሉ ፥ በተለይም የኦሮሚያ ክልል (ምስራቅ ወለጋ) የሚገኙ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የእልቂት ማእከል ሆነው በንፁሐን የደም ዋበላ የሚታጠቡ የሰቆቃ ምድር ሆነዋል፡፡ ቤኒሻንጉል የነበረው እልቂት በጋምቤላ በዜጎች ላይ ከሚፈፀመው ጭፍጨፋ ባሻገር ከክልላዊ መንግስቱን ለመቆጣጠር ከጫፍ እስከመድረስ የደረሱት የአሸባሪው ኃይሎች በዚቹ "መንግስት አለ!" በሚባልባት ሀገር በነፃነት እየሰለጠኑና እየታጠቁ መሆኑም የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡

በነገራችን ላይ የኢትዮጵያውያን የመከራና የግፍ ፅንስን አርግዞ የወለደው ትህነግ ፥ በለስ ቀንቶት የሀገረ መንግስቱን ስልጣን ይዞ በቆየባቸው በእነዚያ የተረገሙ አስርት አመታት ውስጥ በጥሩነቱም ውሰዱት በመጥፎ ፥ ብቻ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ አይደለም በቀበሌ በጎጥ ውስጥ እንኳ አንድም የታጠቀ ሀይል የሚንቀሳቀስበት ሁኔታ ተፈጥሮ አያውቅም ነበር፡፡

ከኢህአዴግ አብራክ የተወለደው ገዢው የብልጽግና መራሹ መንግሥት ሀገረ-መንግስቱን ከተቆጣጠረበት ሰአት ጀምሮ አማፂያን ቡድኖች መሀል ሀገር ሆነው በትጥቅና በሰው ሀይል እየተንሰራፉና እየደረጁ ሀገሪቷን በደም የጨቀየች ምድር ሲያደርጓት ፤ በተለያዩ ጊዜያት " ተደመሰሱ ፥ ወደጎረቤት ሀገር ተሰደዱ ፤ አንድም ቀበሌ አልተቆጣጠሩም ፣ መሪዎቻቸው ተያዙ ፣ ተበተኑ ፣ ….ወዘተ" የሚል መሬት ላይ ካለው እውነታ በተቃራኒ የሆነ ፕሮፓጋንዳ ከመስራት ፥ "የገነባሁት በአፍሪካ ተገዳዳሪ የሌለው ሰራዊት ነው" ሲል ያሞካሸውን ሀይል ተጠቅሞ እንኳ የዜጎችን በህይወት የመኖር መብት እንኳ ሊያስከብር አልቻለም፡፡

እልቂቱን ማስቆም ፥ መንግስታዊ ሀላፊነቱን መወጣት ያልቻለው ይህ ስርአት ወርዶ ወርዶ በንፁሀን ላይ ፍጅት ሲፈፀም መረጃ እንዳይወጣ ኔትወርክ ወደማጥፋት ደረጃ ዝቅ ብሎ ይገኛል፡፡ ወለጋም በየደቂቃው ኤልፎች የሚፈጁባት ፣ አስርት ሺዎች የሚፈናቀሉባት የደምና የግፍ ምድር ሆና ቀጥላለች፡፡

እኛም አቤት የሚል በሌለበት " ኧረ መንግስት ሆይ ወዴት አለህ?" እያልን አምስት እረፍት አልባ የሰቆቃ አመታትን ልንደፍን ነው፡፡

ኦ ወለጋ በንፁሐን ደም የጨቀየች ምድራዊ ሲኦል….!
5.8K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 22:25:54
4.6K views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 22:25:49 በቆቦ ዙሪያ ወረዳ ወገኖቻችን ያሉበት ሁኔታ ይህ ነው!

በብዙ ጭንቀት ውስጥ ሆነው የሚደርስባቸውን ሰቆቃና ግፍ የሚነግሩንን የራያ ወገኖቻችን ድምፅ አለማስተጋባት ከቶውንም አይቻልም!

" ሲያወሩ ስንሰማቸው ‘ ተኩስ አቁም ላይ ነን’ ነው የሚሉን ፥ ላለፉት 15 ቀናት አልፎ አልፎ ተባራሪ ተኩስ ካልሆነ በስተቀር ምንም ውጊያ የለም!" የሚሉት በሰቆቃ ስር ያሉ የቆቦ ዙሪያ ወረዳ ወገኖቻችን ፥ ከሚደርስባቸው ድብደባና እንግልት ባሻገር የእርድ እንስሳቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ እያረዱ እንደሚበሉባቸው ፥ ዱቄትና የእህል ዘር የተባለን የአርሷደሮችን ስም ዝርዝር ይዘው ከየቤቱ በአህያ እየጫኑ እንደሚወስዱ ፥ በዱር የደረሱ ሰብሎች አተርና የእሸት እህሎችን ባሉበት እያወደሙ እንደማገኙ የገለፁ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ጨው እንኳ የተቸገሩበት ሁኔታ መኖሩን ይናገራሉ፡፡

" ከረሀቡ በላይ በየመንደሩ የታመሙና ከፍተኛ ህክምና የሚሹ ነዋሪዎች በቃሊም በኩል እንኳ አሳልፈን ለመውሰድ ብንሞክርም ሊፈቅዱልን ባለመቻሉ በሞትና በህይወት መካከል የሚገኙ ህሙማን ወደሞት አፋፍ እየተቃረቡ ነው!" ሲሉም ያሉበትን አስከፊ የጨለማ ህይወት ይገልፃሉ፡፡

የመከላከያ ሰራዊቱ በቃሊም በኩል አስገዳጅ ከሚባል አካባቢ ያለ ሲሆን በቅርብ ርቀት ደርባ ፣ አዋስ ፣ ደብረ ሰላም ፣ ቱሜ አስመላ ፣ ….ወዘተ የሚባሉ የቆቦ ወረዳ አካባቢዎችን ደግሞ ከ25-30 ሺህ የሚገመት የአሸባሪው ሀይል የነዋሪውን እህል እያወደመ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ላለፈው 15 ቀን ገደማም በዚያ በኩል ከተባራሪ ተኩስ ውጭ ምንም አይነት ውጊያ የለም፡፡

በዚህ መካከል ህዝቡ በረሀብ ፣ በህክምና እጦት እንዲሁም በሽብር ቡድኑ ጥቃት እያለቀ መሆኑን የሚናገሩት ወገኖቻችን ፥ " …ቢያንስ እነሱ ተኩስ አቁም እንደተስማሙት ሁሉ እኛም ታመው በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ልጆቻችንን ወደደሴ ወስደን እንድናሳክም ተስማምተው ሊፈቅዱልን ይገባ ነበር!" ሲሉ ሲቃ እየተናነቃቸው ይናገራሉ፡፡ ለማለፍ ያደረጉት በርካታ ጥረትም አልተሳካም፡፡

" መሳሪያ አላችሁ አምጡ እያሉ በየቤቱ በመዞር ከፍተኛ ድብደቢና እስር እየፈፀሙ እንደሚገኙ የሚገልፁት ታጋች ወገኖቻችን " መሳሪያ የለንም ስንል ደግሞ መሳሪያ ያለው ቤተሰባችሁ ሸሽቷልና ካለበት አስመጡ በማለት ደግሞ ዙረው ተመሳሳይ ግፍ ይፈፅሙብናል፡፡" ብለዋል፡፡

በቆቦ ዙሪያ ወረዳ 015 ቀበሌን ጨምሮ እስከሮቢት ድረስ ባሉ የወረዳው ቀበሌዎች በየአርሷደሩ በር ላይ የአሸባሪው ታጣቂዎች ጥብቅ ክትትል እያረጉ እንቅስቃሴአቸውን እየተቆጣጠሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

ትኩረት በእገታ ስር የመከራን ፅዋ ለሚጎነጩት የራያ ወገኖቻችን!
5.5K views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 16:59:51 ተቋማትን የሚያፈርሰው የሀሳብ ሳይሆን ርዕዮተ-አለማዊ ልዩነት ነው!

ርዕዮተ ዓለም (ideology) በአወንታዊም ሆነ በአሉታዊ መልኩ የአለምን የማህበራዊ እና የፖለቲካዊ ግንዛቤዎችን ወይም አመለካከቶችን ለማንፀባረቅ ፥ ለመቅረፅ ወይም ለመመልከት የሚያገለግል ፤ የሃሳቦች፣ የእምነቶች እና የአመለካከቶች ጥቅል ብያኔ ነው። የፖለቲካ አሠራሮችንና ተቋማትን ለመጠበቅ ወይም ለመለወጥ ፥ የጋራ እርምጃዎች ላይ ለመምከር፣ ለማጽደቅ ወይም ለመደገፍ የሚያገለግል ፅንሰ ሀሳባዊ የአመለካከትና የአስተሳሰብ መስመር ነው!


ርዕዮት አለም አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ አለምን የሚመለከትበት መነፅር ነው፡፡ ግለሰብ የየራሱ አስተሳሰብ ይኖረዋል፡፡ ግለሰቦች ሲሰባሰቡ ደግሞ አንድን የጋራ አላማና ግብ ለማሳካት የጋራ አስተሳሰብ ፥ አመለካከትና እምነቶችን ሊገነቡ ይችላሉ፡፡ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ (political community) ከገነባው የጋራ ርዕዮተ-አለማዊ አስተሳሰብ ተነስቶ ተቋም ይመሰረታል፡፡ በተመሳሳይ የአስተሳሰብ ፣ የአመለካከትና የአሰራር ስርአት ውስጥ ሆኖም ወደጋራ አላማና ግብ የህብረት ጉዞ ይጀመራል ፡፡


አስተሳሰብ ይገነባል የተገነባንም ያፈርሳል፡፡ የፖለቲካ ተቋማት ውስጥ በአጀንዳዎች ላይ የተለያዩ የሀሳብ ልዩነቶች ፣ ሙግቶች ፣ ፍጭቶች አደግ ሲልም እስከ ግጭት የደረሱ ፍትጊያዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ነገርግን በሁሉም ወገን ያለው ፍትጊያ ከጋራ ግብና አላማ አኳያ ከተገነባው ርዕዮት አለማዊ አቅጣጫ የወጣ ሊሆን አይችልም፡፡ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ልዩነቶችና ፍጭቶች ቢኖሩም በመጨረሻ በጋራ ርዕዮት አለማዊ ስርአት ውስጥ የሚታረቁ ይሆናሉ፡፡ ነገርግን የልዩነቱ ምንጭ ርዕዮተ-አለማዊ ከሆነ ተቋማትን በልዩነቱ ልክ የመሠንጠቅና የማፍረስ እድል ይኖረዋል፡፡

ተቋማቶቻችን ከግለሰቦች ክህደት ፣ ጥቅመኝነትና እልክ ባሻገር በሂደት ውስጥ ከነዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ርዕዮተ-አለማዊ ልዩነቶች እየተፈጠሩ ወደመፈረካከስ የሚሄዱበት አቅጣጫ እንደሚያመሩ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

ለምሳሌ - የአማራ ብሔርተኛ ሆኖ " የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል የሚሳካው ብሎም ጥቅምና ፍላጎቶቹ የሚከበሩት እንደአማራ አንድ አማራ ተደራጅቶ መታገልና ጠንካራ ተደራዳሪ መሆን ሲችል ነው! " ብሎ የተሰባሰበ ሀይል መካከል ፥ በሂደት " …የአማራ ህዝብ ጥያቄ የሚመለሰው በኢትዮጵያዊነት ማእቀፍና ከገዢ አንባገነኖች ጋር ተቀራርቦ በመስራት ነው፡፡ በመሆኑም የአማራ ብሔርተኝነት ሳይጠነክር ከወዲሁ መጨንገፍ አለበት!" የሚል ሀይል ከተፈጠረ ችግሩ የሀይል አሰላለፍና የጎራ መለያየት ይሆናል፡፡ ይህም ከጋራ መርህና ርዕዮተ-አለማዊ አቅጣጫ ማፈንገጥ ይሆናል!
6.9K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 19:24:31 አሁንም " ሳይቃጠል በቅጠል!" እላለሁ!

" ..የታሪክ ሽሚያ - የራሱን ታሪክ መፃፍ የማይችል የመከነ ትውልድ መገለጫ ነው!"

ታሪክ ጥሩም ሆነ መጥፎ በታሪክነቱ ተከትቦ ትውልድ ከመልካሙ ታሪክ እንዲማርበትና እንዲያስቀጥለው ፥ እኩይ የሆነውን ታሪክ ደግሞ ዳግም እንዳይከሰት ተግቶ የሚሰራበት ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ቀዲም አሻራ ነው፡፡

የአሁኑ ትውልድ የሚጠበቅበት ከትናንት ተምሮ ፥ በጎ ታሪኮችን አስቀጥሎ ነገን የመስራትና የራሱን ታሪክ ፅፎ ፥ ለተተኪው ትውልድ አውርሶ ማለፍ ነው፡፡

ያለፈ ታሪክ ዛሬውንም ሆነ ነገውን እንዲያበላሽ የሚፈቅድና የትናንቱን የቀድምት አባቶቹን አኩሪ ታሪክ ከመድገም ይልቅ ወደሽሚያ ውስጥ የሚገባ እርሱ ታሪክ መስራት የማይችል የመከነ ትውልድ ነው፡፡

አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚንስትር ሆኖ ከመጣ ጀምሮ የታሪክ ትምህርት በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ከሀምሳ በላይ ዩኒቨርስቲዎች መሠጠት አቁሟል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ከዚህ " ቀደምት የነበረው የኢትዮጵያ ታሪክ የእኛ ታሪክ አይደለም!" ብለው የሚያምኑና ለታሪክ ሽሚያ ያሰፈሰፉ ነውረኛ የፖለቲካ ሀይሎች ፥ የሀገረ መንግስቱን ስልጣን በመያዛቸው ነው፡፡ እነዚህ ሀይሎች የቀደምት አባቶቻችንን አኩሪ ታሪክ በብሄር ሚዛን ላይ አስቀምጠው ለቅርጫ የተቀመጡ ብሎም የተፈፀመውንም ሆነ በትርክት የወለዱትን በጎ ያልሆነ ታሪክ ፥ ህዝብን እርስበርሱ በማባላት በደም የጨቀየ አሁናዊው የፖለቲካ ስልጣን ረሀባቸውን ለማስታገስ የሚጠቀሙ ከንቱዎች መሆናቸው የሚታመን ነው፡፡

የዛሬ ሁለት አመት ገደማ የኦሮሞ የፖለቲካ ኤሊት ከሚባሉት አብዛኛዎቹ በተገኙበት መድረክ ላይ የመታደም እድሉን አግኝቼ በውይይታችን ካነሳሁት ጭብጥ መካከል ፦

<< ..ኢትዮጵያ ውስጥ ታሪክን አንሻፎ የሚተረጉም ፥ በክፉም ሆነ በበጎ የነበረውን ታሪክ ያለፈ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው ብሎ የማያምን ፥ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አባቶቻችን ስለሀገር ብለው ሰርተው ያለፉትን ታሪክ በብሔር ቅርጫ ላይ አስቀምጦ ለመከፋፈልና ለመነጣጠቅ የሚተጋ ብሎም "ኢትዮጵያ" በምትባለው ሀገር ላይ በጋራ የሚያግባባ ተመሳሳይ ሀገራዊ ብያኔ የሌለው እንዲሁም ስያሜዋን ሁሉ የማይቀበል በፅንፈኝነትና በጥላቻ የሠከረ የፖለቲካ ኤሊት ባለበት ሀገር ፥ ማንኛውን ዘላቂ ሰላምና አብሮት ለማምጣት ነው ለውይይት የተቀመጥነው? ስለየቱ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ነው የምናወራው? ግጭትና እልቂትን እየደገሰ ያሐ የፖለቲካ ኢሊት ስለሰላምና ህዝባዊ አንድነት ለመስበክ መነሳቱ አሽሙር አይሆንምን ? ….. >> የሚል ሀሳብ አንስቼ ተከራክረን ሳንግባባ መለያየታችንን አስታውሳለሁ፡፡

በነገራችን ላይ ከኢህአዴግ/ህወሓት በፊት በነገስታቶችና በህዝቦች መካከል የነበረው ጥሩም ሆነ መጥፎ ታሪክ የተሰራው በሀገራዊ (ኢትዮጵያዊነት) ስሜት እንጂ በብሔር አጥር ስር አልነበረም፡፡ የሀገርን ሉአላዊነት ኢትዮጵያውያን በጋራ ሆነው ከውጭ ወራሪዎች ጋር ካደረጓቸው ጦርነቶችና ካስመዘገቧቸው አኩሪ ድሎች ባሻገር ፥ እርስበርስ ተደረጉ የሚባሉት ግጭቶች ለስልጣን ሽኩቻ (ንግስና) ካልሆነ በስተቀርም ለብሔር የበላይነት የተደረጉ አለመሆናቸውን በቀና ልቦና የኢትዮጵያን ታሪክ ለሚገነዘብ ሁሉ ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡

እናም " ለምን?" ብሎ የማይጠይቅ አድርባይና አጎብዳጁ የፖለቲካ ሀይል ፥ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ከመጡ በኃላ በኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ እየተሰራ ያለውን ሀገር አፍራሽና ለማንም የማይጠቅም የታሪክ ሽሚያ ማስቆምና መታገል አለመቻሉ ፥ በጥላቻ የሠከረው ፣ ፅንፈኛውና ታሪክ ለመስራት ያልተፈጠረው ይህ የፖለቲካ ቡድን ፥ ከዩኒቨርስቲ የታሪክ ዲፓርትመንት መዝጋት አልፎ ፥ መጪው ትውልድ የሚታነፅበትን ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተዘረጋ የትምህርት ስርአት ውስጥ የተንሻፈፈ ፣ የተፋለሰ ብሎም ለራስ ፖለቲካዊ ፍጆታ ማሳኪያነት ብቻ የሚውል ትርክት ተቀርፆ በማስተማሪያነት ሊመጣ ችሏል፡፡

ከዚህ በመነሳት ነገ ሀገሪቱ አሁን ካለችበት ማጥ መውጣት ቀርቶ ወደከፋ የእልቂት ጎዳና እየተንደረደረች እንደምትገኝ ፥ የተሟላ ጤንነት ያለው ሙሉ ሠው ሁሉ በቀላሉ የሚረዳው ሀቅ ነው!

ሠላም!
6.6K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 20:25:26
3.9K views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 20:18:05 ለማብራራት ያህል!

አሸባሪው ትህነግ/ህወሓት በለስ ቀንቶት ፥ በታሪክ አጋጣሚ የማዕከላዊ መንግስቱን ስልጣን ጨብጦ የኖረባቸውን ጨምሮ ላለፉት አርባ አመታት በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመውን ግፍና ሰቆቃ ፤ ሰማይን እንደወረቀት ፣ ውቅያኖሶችን እንደቀለም ብሎም ከዋክብትን እንደቃላት ተጠቅመን ብንፅፈው እንኳ የሚያልቅ አይመስለኝም !

ይህ የግፍና የሰቆቃ ታሪክም በደፋር የታሪክ  ፀሀፍቶች በየጊዜው እየተሠነደ ለትውልድ መተላለፍ እንዳለበትም አምናለሁ፡፡ እነሱ ልቦለዳዊ የጥላቻ ድርሰት ፅፈውና ትርክት ፈጥረው ዘመን ተሻጋሪ ግፍና ሰቆቃ ሲፈፅሙ የኖሩት እያሉ ፥ የተፈፀመን እውናዊ ድርጊት በታሪክ ሰንዶ ማስቀመጡ  ፥ እንደአንድ መሠረታዊ ተግባር መወሠድ ያለበት አምድም ነው፡፡

ዛሬ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ምሁራን ተጠንቶ በመፅሐፍ የተጠናከረ መሆኑን ወንድሞች ያብራራችሁልኝ ፥ የትህነግን ጭካኔና ግፍ የሚያሳይ መፅሀፍም  የምወስደው የዚሁ አንድ አካል አድርጌ ነው፡፡ ባይሆን አጥኚ ምሁራኖቻችን ወቅት እየጠበቁ ሳይሆን በአሁኑ ሠአትና ላለፉት አራት አመታት በህዝባችን ላይ ያለእረፍት የዘነበውን የዘመነ ብልፅግና የዘር ፍጅት ፤ ማሳደድና ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት ደፍረው መፃፍንና መጋፈጥን ይጀምራሉ ብዬ አስባለሁ፡፡

ከሰአታት በፊት በፃፍኩት ፅሁፍ ውስጥም የዚህን መፅሀፍ  መፃፍ እየተቃወምኩ ወይም እየተቸሁ አለመሆኑን ፅሁፉን በቀናት ረጋ ብሎ ያነበበ ሁሉ በቀላሉ ሊረዳው ይችላል፡፡

ነገርግን ዛሬም ድረስ ተጠናክሮ የቀጠለው የአማራ ህዝብ ግፍና ሰቆቃ ስርአት ሰራሽና መዋቅራዊ መሆኑንና "ህገ-መንግስት" የተባለው የሀገር ማፍረሻ ውል  ደግሞ ህዝባችንን ሀገር-አልባና ስደተኛ ጭምር  ያደረገ የመከራ ዶሴ መሆኑን የማያምን ፣ የማይከራከርና እንዲቀየር የማይታገል   አድርባይና መርህ አልባ የፖለቲካ ልሂቅም ሆነ የታሪክ ከታቢ   " ስለአማራ ህዝብ ግፍና ሰቆቃ ፃፍኩ"  ቢለኝ << ...ታሪኩን ለታሪክ ፀሀፊ ትተህ ፥ የአማራ ህዝብ አሁን ያለበትንና በቀጣይ የተደቀነበትን መከራና ግፍ እንዴት እንደሚሻገር መክረህና ዘክረህ ብሎም በአንድነት  አደራጅተህ አታግለው! >> ማለቴ አይቀርም !

ሠላም!!!
4.9K viewsedited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ