Get Mystery Box with random crypto!

ለማብራራት ያህል! አሸባሪው ትህነግ/ህወሓት በለስ ቀንቶት ፥ በታሪክ አጋጣሚ የማዕከላዊ መንግስቱ | ዘሪሁን ገሠሠ

ለማብራራት ያህል!

አሸባሪው ትህነግ/ህወሓት በለስ ቀንቶት ፥ በታሪክ አጋጣሚ የማዕከላዊ መንግስቱን ስልጣን ጨብጦ የኖረባቸውን ጨምሮ ላለፉት አርባ አመታት በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመውን ግፍና ሰቆቃ ፤ ሰማይን እንደወረቀት ፣ ውቅያኖሶችን እንደቀለም ብሎም ከዋክብትን እንደቃላት ተጠቅመን ብንፅፈው እንኳ የሚያልቅ አይመስለኝም !

ይህ የግፍና የሰቆቃ ታሪክም በደፋር የታሪክ  ፀሀፍቶች በየጊዜው እየተሠነደ ለትውልድ መተላለፍ እንዳለበትም አምናለሁ፡፡ እነሱ ልቦለዳዊ የጥላቻ ድርሰት ፅፈውና ትርክት ፈጥረው ዘመን ተሻጋሪ ግፍና ሰቆቃ ሲፈፅሙ የኖሩት እያሉ ፥ የተፈፀመን እውናዊ ድርጊት በታሪክ ሰንዶ ማስቀመጡ  ፥ እንደአንድ መሠረታዊ ተግባር መወሠድ ያለበት አምድም ነው፡፡

ዛሬ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ምሁራን ተጠንቶ በመፅሐፍ የተጠናከረ መሆኑን ወንድሞች ያብራራችሁልኝ ፥ የትህነግን ጭካኔና ግፍ የሚያሳይ መፅሀፍም  የምወስደው የዚሁ አንድ አካል አድርጌ ነው፡፡ ባይሆን አጥኚ ምሁራኖቻችን ወቅት እየጠበቁ ሳይሆን በአሁኑ ሠአትና ላለፉት አራት አመታት በህዝባችን ላይ ያለእረፍት የዘነበውን የዘመነ ብልፅግና የዘር ፍጅት ፤ ማሳደድና ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት ደፍረው መፃፍንና መጋፈጥን ይጀምራሉ ብዬ አስባለሁ፡፡

ከሰአታት በፊት በፃፍኩት ፅሁፍ ውስጥም የዚህን መፅሀፍ  መፃፍ እየተቃወምኩ ወይም እየተቸሁ አለመሆኑን ፅሁፉን በቀናት ረጋ ብሎ ያነበበ ሁሉ በቀላሉ ሊረዳው ይችላል፡፡

ነገርግን ዛሬም ድረስ ተጠናክሮ የቀጠለው የአማራ ህዝብ ግፍና ሰቆቃ ስርአት ሰራሽና መዋቅራዊ መሆኑንና "ህገ-መንግስት" የተባለው የሀገር ማፍረሻ ውል  ደግሞ ህዝባችንን ሀገር-አልባና ስደተኛ ጭምር  ያደረገ የመከራ ዶሴ መሆኑን የማያምን ፣ የማይከራከርና እንዲቀየር የማይታገል   አድርባይና መርህ አልባ የፖለቲካ ልሂቅም ሆነ የታሪክ ከታቢ   " ስለአማራ ህዝብ ግፍና ሰቆቃ ፃፍኩ"  ቢለኝ << ...ታሪኩን ለታሪክ ፀሀፊ ትተህ ፥ የአማራ ህዝብ አሁን ያለበትንና በቀጣይ የተደቀነበትን መከራና ግፍ እንዴት እንደሚሻገር መክረህና ዘክረህ ብሎም በአንድነት  አደራጅተህ አታግለው! >> ማለቴ አይቀርም !

ሠላም!!!