Get Mystery Box with random crypto!

የስቃይ ማስታገሻ (ማረሳሻ)  መርፌ ከሞት አያድንም! ከአመታት በፊት 'ቁጥር -2 ኢህአዴግ' ወደ | ዘሪሁን ገሠሠ

የስቃይ ማስታገሻ (ማረሳሻ)  መርፌ ከሞት አያድንም!

ከአመታት በፊት "ቁጥር -2 ኢህአዴግ" ወደስልጣን ሳይመጣ አንድ በሆነ ዩኒቨርስቲ የሚያስተምር ፕሮፌሰር ጋር በነበረን ውይይት ፥ ከታች ክፍል ስንማር መፅሀፍት ላይ የነበሩ ምሳሌዎችን በመውሰድ   << ... አማራ እኮ ከበሶ አቅም ለአበበ በሶ አብልቶ ፥ ለጫላ ግን ያስጨበጠው ጩቤ ነው!! .... >> እያለ ሲከራከረኝ ፥ በወቅቱ ሁኔታው የመሠለኝ ቀልድ እንጂ በዚህ በሁሉም ስርአቶች የግፍ ዶፍ በሚያስተናግድና አመድ አፋሽ በሆነ ህዝብ ላይ ፥  ያውም አንድ ትውልድ በመቅረፅ ላይ ባለ ምሁር  ፥ በዚህ  ደረጃ እስከ አጥንት ድረስ የዘለቀ ጥላቻና የተጠቂነት አስተሳሰብ ያዳብራል ብዬ አላመንኩም ነበር!

ነገርግን አሁን በሁሉም መስክ በገሀድ የምናየው ፥ የታሪክ አጋጣሚ እየጠበቀ   ለዘመናት የጥላቻ መርዝ እንደኒኩሌር ሲያብላላ የኖረው ፥ በሀሰተኛ ትርክት የሰከረ ፅንፈኛ የፖለቲካ ቡድን ፥ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያውን በፍፁማዊ ጭካኔ እየተጠቀመው ይገኛል!

ከዚህ አኳያ የአማራ ህዝብ ሰለባ እየሆነ ያለበት ለአመታት የተረጨው ሀሰተኛ የጥላቻ ትርክት ሰንኮፉ እስካልተነቀለና "ህገ-መንግስት" በተሰኘው የሀገር ማፍረሻ ውል የተተከለበት ስርአታዊና መዋቅራዊ ግፍ  ስርአታዊ በሆነ ለውጥ ካልተተካ ካሳለፈውም በላይ የመጪው ጊዜ ከበድ ያለ እንደሚሆን ቅንጣት አልጠራጠርም!

ይህ የሚሆነው ደግሞ የአማራ ህዝብ ጠንካራ የፖለቲካ ማህበረሰብ ሆኖ ፥ አንድነትና ህብረቱን ጠብቆ ፥ በጠራ የፖለቲካ  ግብ ላይ በመመስረት  እንደህዝብ የሞት ሽረት ተጋድሎ ሲያደርግ ብቻ ነው!

አሁን ያለው የትግል አካሄድ "ከስቃይ ማስታገሻ መርፌነት" የዘለለ አንዳችም ጠብ የሚያደርገው ነገር የለም!