Get Mystery Box with random crypto!

ተቋማትን የሚያፈርሰው የሀሳብ ሳይሆን ርዕዮተ-አለማዊ ልዩነት ነው! ርዕዮተ ዓለም (ideol | ዘሪሁን ገሠሠ

ተቋማትን የሚያፈርሰው የሀሳብ ሳይሆን ርዕዮተ-አለማዊ ልዩነት ነው!

ርዕዮተ ዓለም (ideology) በአወንታዊም ሆነ በአሉታዊ መልኩ የአለምን የማህበራዊ እና የፖለቲካዊ ግንዛቤዎችን ወይም አመለካከቶችን ለማንፀባረቅ ፥ ለመቅረፅ ወይም ለመመልከት የሚያገለግል ፤ የሃሳቦች፣ የእምነቶች እና የአመለካከቶች ጥቅል ብያኔ ነው። የፖለቲካ አሠራሮችንና ተቋማትን ለመጠበቅ ወይም ለመለወጥ ፥ የጋራ እርምጃዎች ላይ ለመምከር፣ ለማጽደቅ ወይም ለመደገፍ የሚያገለግል ፅንሰ ሀሳባዊ የአመለካከትና የአስተሳሰብ መስመር ነው!


ርዕዮት አለም አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ አለምን የሚመለከትበት መነፅር ነው፡፡ ግለሰብ የየራሱ አስተሳሰብ ይኖረዋል፡፡ ግለሰቦች ሲሰባሰቡ ደግሞ አንድን የጋራ አላማና ግብ ለማሳካት የጋራ አስተሳሰብ ፥ አመለካከትና እምነቶችን ሊገነቡ ይችላሉ፡፡ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ (political community) ከገነባው የጋራ ርዕዮተ-አለማዊ አስተሳሰብ ተነስቶ ተቋም ይመሰረታል፡፡ በተመሳሳይ የአስተሳሰብ ፣ የአመለካከትና የአሰራር ስርአት ውስጥ ሆኖም ወደጋራ አላማና ግብ የህብረት ጉዞ ይጀመራል ፡፡


አስተሳሰብ ይገነባል የተገነባንም ያፈርሳል፡፡ የፖለቲካ ተቋማት ውስጥ በአጀንዳዎች ላይ የተለያዩ የሀሳብ ልዩነቶች ፣ ሙግቶች ፣ ፍጭቶች አደግ ሲልም እስከ ግጭት የደረሱ ፍትጊያዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ነገርግን በሁሉም ወገን ያለው ፍትጊያ ከጋራ ግብና አላማ አኳያ ከተገነባው ርዕዮት አለማዊ አቅጣጫ የወጣ ሊሆን አይችልም፡፡ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ልዩነቶችና ፍጭቶች ቢኖሩም በመጨረሻ በጋራ ርዕዮት አለማዊ ስርአት ውስጥ የሚታረቁ ይሆናሉ፡፡ ነገርግን የልዩነቱ ምንጭ ርዕዮተ-አለማዊ ከሆነ ተቋማትን በልዩነቱ ልክ የመሠንጠቅና የማፍረስ እድል ይኖረዋል፡፡

ተቋማቶቻችን ከግለሰቦች ክህደት ፣ ጥቅመኝነትና እልክ ባሻገር በሂደት ውስጥ ከነዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ርዕዮተ-አለማዊ ልዩነቶች እየተፈጠሩ ወደመፈረካከስ የሚሄዱበት አቅጣጫ እንደሚያመሩ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

ለምሳሌ - የአማራ ብሔርተኛ ሆኖ " የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል የሚሳካው ብሎም ጥቅምና ፍላጎቶቹ የሚከበሩት እንደአማራ አንድ አማራ ተደራጅቶ መታገልና ጠንካራ ተደራዳሪ መሆን ሲችል ነው! " ብሎ የተሰባሰበ ሀይል መካከል ፥ በሂደት " …የአማራ ህዝብ ጥያቄ የሚመለሰው በኢትዮጵያዊነት ማእቀፍና ከገዢ አንባገነኖች ጋር ተቀራርቦ በመስራት ነው፡፡ በመሆኑም የአማራ ብሔርተኝነት ሳይጠነክር ከወዲሁ መጨንገፍ አለበት!" የሚል ሀይል ከተፈጠረ ችግሩ የሀይል አሰላለፍና የጎራ መለያየት ይሆናል፡፡ ይህም ከጋራ መርህና ርዕዮተ-አለማዊ አቅጣጫ ማፈንገጥ ይሆናል!