Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንድ ነገሮችን ለማስታወስ ያህል! #በደም_ነጋዴነትን_እንታገለዋለን ሁሉ ነገር ገደብ | ዘሪሁን ገሠሠ

አንዳንድ ነገሮችን ለማስታወስ ያህል!

#በደም_ነጋዴነትን_እንታገለዋለን

ሁሉ ነገር ገደብ አለው፡፡ ገደብ ያለፉና ለተለያዩ ችግሮች የሚዳርጉንን አካላት ግን ከእንግዲህ መታገስ አያሻም!

ማንም ሰው የሚታገለው በቅድሚያ ለራሱ ሲል ነው፡፡ ሲቀጥል እንደማህበረሰብ የተጋረጠብንን አደጋ ለመቀልበስ ፣ የምንጠይቀውን የፍትህና የእኩልነት ጥያቄ ለማስመለስ ነው፡፡ ለራሱ ዛሬ ፣ ለትውልዱ ነገ አስቦ ዛሬ ላይ የሚታገል በጊዜ የነቃ ሙሉ ሠው ነው!

በዚህም መሠረት ሁሉም በየመክሊቱና በተሰማራበት መስክ ሁሉ የህዝብን ትግል ማገዝና መደገፍ ይችላል ፤ አለበትም፡፡ ፡፡ ለዚህ ተግባሩ ክፍያው ነፃነት ፣ ሰላም ፣ ፍትህና እኩልነት እንጂ የተለየ ነገር ሊሆን አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ ሁላችንም በቻልነውና የመጨረሻ አቅማችን እስከሚችለው ድረስ የሚጠበቅብንን አበርክተናል እናበረክታለንም፡፡

ነገርግን የህዝብን ትግል መነገጃና ግላዊ ፍላጎትን ማሟያ ማድረግ ከእንግዲህ ሊገታ ይገባዋል፡፡ በሜካፕ አርቲስት ታጅበው የመሸቀያ ፎቶ ለመነሳትና በተግባር ያልተገለፀ ርካሽ ውዳሴ ለማጋበስ ግንባር ድረስ በመዝለቅ የሚተጉ "ፎር ስታር ፋኖዎችን" ከእንግዲህ በቃችሁ ማለት መልመድ አለብን! በብዙ ጉድ ችለን ፀጥ ያልነው "መጓተቱ አይበጅም” ብለን መሆኑንም ሊታወቅ ይገባል!

በተለያዩ ሀገራት ያላችሁ ወገኖቻችንም ፥ በቅንነትና ትግሉን የደገፋችሁ እየመሠላችሁ ፥ አደረጃጀትን ከመደገፍ ይልቅ ሬንጀርና ጦርሲ ለብሶ ከንፈሩ ላይ ኮቾሮ ጣል አርጎ ሰልፊ የለቀቀውን ሁሉ "ለመሳሪያ መግዣ ፥ ለስንቅና ትጥቅ ፣ ….ወዘተ" በሚል ማታለያቸው ረብጣ ገንዘብ እየላካችሁ ወንድሞቻችን እርስበርስ ሲጠራጠሩ ፣ ግጭቶች ሲፈጠሩ ፥ አደረጃጀቶች ለመከፋፈል ሲዳረጉ ብሎም በተግባር ውድ ዋጋን የከፈሉት አስበውት የማያውቁትን እንዲያስቡና ሞራላዊ ተፅዕኖ እንዲያርፍባቸው ሲሆኑ አይተናል!

በመሆኑም በዚህ ረገድ የሚስተዋሉ ትግሉን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚጎዱና ነጋዴዎችን ከሚያበዙ ተግባራት መታቀብ ያስፈልጋል!

ፋኖን መደገፍ ከፈለክ በአደረጃጀቱ ይፋዊ የድጋፍ ማእቀፍ በቀጥታ ደግፍ! ሌላውንም ሀይል በተመሳሳይ እንዲሁ በህጋዊና በይፋዊ የድጋፍ ማዕከላት ደግፍ! አደራ/አማና ሰጥተህ ከሆነም ፥ ድጋፍህ ለታለመለት አላማ መድረሱን አረጋግጥ! ከዚያ ውጭ በተዋኒያን እውናዊውን ትግል እንደምትጎዳው መረዳት ያስፈልጋል!

ይታሰብበት!