Get Mystery Box with random crypto!

ፋኖ የራሱን ወታደራዊ መረጃ ፥ በአደረጃጀቱ የመረጃና የፕሮፓጋንዳ ክፍል ብቻ እንዲተላለፍ የሚያደር | ዘሪሁን ገሠሠ

ፋኖ የራሱን ወታደራዊ መረጃ ፥ በአደረጃጀቱ የመረጃና የፕሮፓጋንዳ ክፍል ብቻ እንዲተላለፍ የሚያደርግ ጥብቅ አሰራርን መከተል አለበት!

በተደጋጋሚ የፋኖ አመራሮችን ሳገኝ የማቀርበው ምክረ-ሀሳብ ይህንን መሠል ተቋማዊ አሰራር ማጎልበትን ቅድሚያ ሰጥተው እንዲሰሩበት ነው! ዛሬም ጥቂት ወንድሞችን በነበረን ቆይታ ሳሳስብ የነበረው ይህንኑ ነው!

በተግባር እሳት ላይ ተጥደው ከሰራዊቱ ጋር የሚፋለሙ ፋኖዎች ፥ ስለአውደ-ውጊያ ውሎዎቻቸውም ሆነ አጠቃላይ እንቅስቃሴአቸው ሳንሱር የተደረገ ብሎም ጥቅምና ጉዳቱ ተመጥኖ ይፋ የሚደረግ ተቋማዊ የመረጃና የፕሮፓጋንዳ ስርአት ማበጀት አለባቸው!

ጦርነት 80% የሚሆነው የመረጃና የፕሮፓጋንዳ ስራ ነው፡፡ በጥቂት የተሳሳተ መረጃ ትልቅ ዋጋ ይከፈላል፡፡ በትንሽ ወሬ ጦር ይፈርሳል፡፡ በተሳሳተ መረጃ ለጠላት ምቹ አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ አንድምታው ያልተገመገመ የመረጃ ፍሰት ጦርን ከጦር ፥ ጓድን ከጓድ ሁሉ እስከማጋጨት ሊጓዝ ይችላል፡፡

በመሆኑም የምስራቅ አማራም በሉት የወሎ ፋኖ ሁሉም የአንድ አላማ ዘማቾች ፥ የአንድ ህዝብ ልጆችና የአንድ አፈር አፈሮች ናቸውና በመረጃና በፕሮፓጋንዳ ረገድ የሚስተዋሉባቸውን ችግሮች ከላይ በገለፅኩት መሠረት በሀላፊነትና በጥንቃቄ ሊመሩት ይገባል፡፡

ከአደረጃጀቱ እውቅና ውጭ ፥ በድጋፍ ስምም ሆነ በተለያዩ መንገዶች ወደግንባር ዘልቀው ያዩትን የፎቶግራፍ ፣ የድምፅ ፣ የቪዲዮና መሠል መረጃዎችን ፥ ያለይሁንታ በማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በተለያዩ መንገዶች የሚያስተላልፉና የሚያሰራጩ አካላትን መከታተልና ቁጥጥር ማድረግ ይገባል! የድርጊቱ ፈፃሚዎችም አላማችን ከህዝብና ከትግሉ ጎን ሆነን በጎ አስተዋጽኦ ማድረግ ከሆነ ሀላፊነት ሊሰማን ይገባል!

የተለያዩ የዩቱብና መሠል ሚዲያዎችም ከፋኖ አደረጃጀት የዘርፉ ክፍል ወይም አመራር ውጪ ባገኛችሁት አጋጣሚ ማንኛውንም የፋኖ አባል ወይም አመራር ፥ ለፖለቲከኛ የሚቀርብን ጥያቄ ጭምር እየጠየቃችሁ በሚዲያ ሲሰራጩ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያስከትሉ ብሎም ለትርጉም የተጋለጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንድትቆጠቡና ሀላፊነት እንዲሰማችሁ ለማሳሰብ እወዳለሁ!

ድል ለሀገርና ለህዝብ ክብር በጀግንነት እየተፋለሙ ላሉት ህዝባዊ ሠራዊቶቻችን ይሁን!