Get Mystery Box with random crypto!

ግራም ነፈሰ ቀኝ ችግሮቻችን የሚፈቱት በንቁ ህዝባዊ ተሳትፎ በሚገነቡ ጠንካራ ተቋማት ብቻ ነው! | ዘሪሁን ገሠሠ

ግራም ነፈሰ ቀኝ ችግሮቻችን የሚፈቱት በንቁ ህዝባዊ ተሳትፎ በሚገነቡ ጠንካራ ተቋማት ብቻ ነው!

" ወጣቶቻችን ይህን ለትልቅ አላማ ለመሠለፍ የቀረበን ትልቅ እድል ተጠቀሙበት! "

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለሀገርና ለህዝብ ህልውና በሚደረገው ጦርነት ምን ያህል ዋጋ እየከፈለ እንደሚገኝ የዳር ተመልካች ሆኖ መረዳት ሊከብድ ስለሚችል በአውደ ውጊያው አካባቢ ጠጋ ብሎ ያለውን እውነትና የገዘፈውን መስዋዕትነት መመልከት ይቻላል፡፡

ይህ ተቋም የሁላችንም ይሆን ዘንድ የሁላችንም ተሳትፎና እገዛ እንደሚያሻው አስረጂና ነጋሪ አያሻውም፡፡

በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሰራዊት መስፈርቱን ለሚያሟሉና የዚህ ትልቅ አላማ የመሠለፍን እድል ለሚሹ ሁሉ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ተከታዩን የአባልነት ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል!



የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከነሐሴ 26/ 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ መስፈርቱን የሚያሟሉ ወጣቶችን መልምሎ በመደበኛ ሰራዊትና በእጩ መኮነንነት በማሰልጠን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል ማድርግ ይፈልጋል ፤

የመመልመያ መስፈርቶች ፦

1) ከአሁን በፊት የፖሊስ ወይም የመከላከያ አባል ያልነበረ/ች

2) ከወንጀል ነፃ የሆነ የፍርድ ቤት ቀጠሮና ክርክር የሌለበት/ባት

3) ከማንኛውም ሱስና አጉል ልማድ የፀዳ/ች እና ሙሉ ጤንነት ያለው/ያላት

4) በመከላከያ ለ7 ዓመት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች በማንኛውም ቦታ ተመድቦ መስራት የሚችል/የምትችል

5) ፆታ፡- አይለይም

6) ኢትዮጵያዊ የሆነ/ች በሚኖርበት ቀበሌ 2 ዓመት የኖረ/ች

7) ዕድሜ፡- ከ18-25 አመት ፤ ቁመት ለወንድ 1.60 እና ከዚያ በላይ ፣ ለሴት ደግሞ 1.55 እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች

8)ክብደት፡-ለወንድ ከ50-75 ኪ.ግ የሆነ ለሴት ደግሞ 45-66 ኪሎግራም የሆነች፣

9) የትምህርት ማስረጃ፦ ለወንድ 6ኛ ክፍል ያጠናቀቀ እና ለሴት እወቅና ካለው የትምህርት ተቋም ዲፕሎማ ወይም በሌቭል ያጠናቀቁ እና ከዚያ በላይ የሆኑ የ 8ኛ ክፍል የሚኒስቲሪ ካርድ ማቅርብ የሚችሉ ፣

10) ያላገባ/ችና ያልወለደ/ች

11) ደመወዝ በመከላከያ ስኬል መሰረት ሆኖ ጥቅማጥቅም የመኖሪያ ቤትና ህክምና አገልግሎት በነፃ የሚያገኙ ሲሆን በመከላከያ ዕቅድና ፍላጎት መሰረት በትምህርት ተቋም ገብተው የመማር ዕድል አላቸው፣

12) የምዝገባ ቦታ ፦ በሁሉም የክልል ከተሞች የፀጥታ ተቋማት ቢሮ( ሚሊሻ ፤ ፖሊስ ፤ ሰላምና ደህንነት ቢሮዎች )

13) የምዝገባ ቀን፡- ከነሐሴ 26/2014 ዓ/ም ጀምሮ አስከ መስከረም 10/2015 ዓ/ም ዘወትር በሥራ ስዓት እንዲሁም ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ

ማሳሰቢያ፡- በምዝገባ ወቅት መቅረብ የሚገባቸው ማስረጃዎች የቀበሌና የፖሊስ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የትምህርት ማስረጃ ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የቀበሌ መታወቂያ በዘመኑ የታደሰ ያስፈልጋል።

ወጣቶቻችን ይህን ለትልቅ አላማ ለመሠለፍ የቀረበን ትልቅ እድል ተጠቀሙበት!