Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-15 15:44:56
የዳግሎ ጦር የተቆጣጠረው ፕሬዚደንታዊ ቤተመንግሥት በጀት እየተደበደበ ይገኛል!

የጄኔራል ዳግሎ (ሒሚቲ) የፈጥኖ ደራሽ ጦር የተቆጣጠረው ካርቱም የሚገኘውን ፕሬዚደንታዊ ቤተመንግሥት በጀት እየተደበደበ ይገኛል!

የመንግሥት ጦር ቀደም ብሎ ከሰአታት በፊት አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያውን እንዳልነበር አድርጎ በጀት መደብደቡ የሚታወስ ነው!

ፈጥኖ ደራሽ ጦሩ ቤተ-መንግስቱን እንደተቆጣጠረ ይገኛል!

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አዛዥ የሆኑት ጄኔራል ዳግሎ " አል ቡርሃንን እጁን ሳልይዝ አላቆምም!" እያሉ ይገኛሉ!
3.2K viewsedited  12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 15:38:29
የዳግሎ ጦር ፕሬዚደንታዊ ቤተመንግሥቱን መቆጣጠሩን ገለፀ!

የጄኔራል ዳግሎ (ሒሚቲ) የፈጥኖ ደራሽ ጦር ካርቱም የሚገኘውን ፕሬዚደንታዊ ቤተመንግሥት መቆጣጠሩን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል!

መብረቃዊ ጥቃት ነው!

ያ ሱዳን ሱዳኒ
ያ ሱዳን ፈናኒ!
3.0K views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 15:20:52
የሱዳን ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ በጀት ተደበደበ!

ሱዳን ፖስት ቀደም ብሎ ባወጣው ዘገባ ፤ በጄኔራል መሐመድ ዳጋሎ (ሒሚቲ) የሚመራው የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ጦር (RSF) ካርቱም የሚገኘውን አየር ማረፊያና በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል የሚገኘውን የሜርዌን ጦር ሰፈር መቆጣጠሩን ዛሬ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ገልፆ ነበር፡፡

በአሁኑ ሠአት ደግሞ የሩስያ ስሪት የሆኑ ሁለት ሱኮይ ሱ-57 ፌሎን ተዋጊ ጀቶች የሱዳን ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያን እየደበደቡ መሆኑንና በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ብሎም ብዙ አውሮፕላኖች መጋየታቸውን የጁባ ሚዲያ ዘገባ ያስረዳል።

በመንግሥት ኃይሎችና በፈጥኖ ደራሽ ጦር (RSF) መካከል የሚደረገው ጦርነት በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል!
3.2K views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 22:30:58 በነገራችን ላይ በብዙ ጉዳዮች ዙሪያ "ተግ" ማለት ይጠበቅብናል!

በትክክልም "በምሬ ወዳጆ የሚመራው የፋኖ ጦር ይቅርታ ጠይቆ ትጥቅ ፈታ!" ብንባል ፥ ጠላት የፈለገውን ይበልና ያላግጥ እንጂ የእኛ አተያይና ምልከታ Still positive መሆን መቻል አለበት እንጂ ለዝርጠጣና ለፍረጃ መጣደፍ የሚጎዳው እኛኑ መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡ መደናገጥም ፍፁም ስህተት ነው፡፡

ሁለተኛው ነገር ከነባራዊ ሁኔታውና ከእውነታው ጋር መጋፈጥን እንልመድ! በጀግንነታቸውና በህዝብ ልጅነታቸው ብዙ ብዙ ያወደስናቸውን አመራሮቻችንን ሌላው ቀርቶ ተሳስተውም ቢሆን ቢያንስ ለአንድ ጊዜ ማመንን ልንካን ይገባል! ሰው ሲሰራ ይሳሳታልና ተፈጥሯዊውን የመሳሳት እድል እንኳ መስጠት ያስፈልጋል! የመላእክት አይነት የፍፁማዊነት አካሄድን መጠበቅ ፥ አስር አመት ያወደስናቸውን በአንድ ጊዜ ስህተት " አይናችሁን ለአፈር!" እያስባለን ብዙ ጠንካሮቻችንን እያሳጣን መሆኑንም ማወቅ ጠቃሚ ነው! ነገሮችን በእነሱ ጎን ሆኖ ማጤንም ብልህነት ነው!

ከዚህ አኳያ በነምሬ ጉዳይም ቢሆን መረጃዎች "ከበሬው አፍ ...!" እስኪደርሱን ቢያንስ ለውሳኔና ለትችት ከመጣደፋችን በፊት ፦

"ይህን ለመወሠን ምን አስገደዳቸው ?"
"ምንስ አማራጭ ነበራቸው?"
"ይህን ባይወስኑ ምን ይከተላቸው ነበር?"
"የሚከተለውን ነገርስ መቋቋም ይችላሉ ወይ ?"
" ይህን በመወሰናቸው ምን አተረፉ?"
"ይህን በመወሰናቸው ጉዳቱስ ምንድን ነው?"
" ከዚህ ውጭ ያላቸውን አማራጭ ለመከተልስ በቅድሚያ ምን ማድረግ መቻል አለባቸው?"
" የትኛውን ለመንከስ የት ጋር ማንከስስ አለባቸው ?
.
ወዘተረፈ ከሚሉት ተጠይቆች ተነስተን የሁኔታ ግምገማ ማድረግ መቻል ብልህነት ነው!

በመሆኑም ራሴን ጨምሮ አብዛሀኛዎቻችን ነገሮችን በስክነትና በብልሃት ማጤንን ብሎም ለድምዳሜ አለመቸኮልን መለማመድ ከቻልን ብዙ ፍሬአማ ጉዞዎችን ወደፊት እንጓዛለን!

መልካም ምሽት!
1.4K viewsedited  19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 16:38:13
ሌላ ሌላውን እንተወውና...!

የመከላከያ ሠራዊቱ መፈክር " የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና ሉአላዊነት እናስከብራለን! " ቢልም ቅሉ ፦

ከሰሞኑ እንኳ የሱዳን ጦር ቀድሞ ከያዘው ወደ70 ኪ.ሜ የሚጠጋ የኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት ፥ በመተማ ዮኋንስ ሰፈር - 4 የልማት ቦታን በመያዝ የወረራ ማስፋፋቱን ቀጥሏል!

የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ከድንበራቸው ወደ 200 ኪሎ ሜትር ዘልቀው በመግባት የአካባቢዎቹን ስያሜ በመቀየር ፥ በስፍራው ያሉ ነገዶችን በመጨፍጨፍ ፤ የወርቅ ማዕድን ማውጫዎችን ጨምሮ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ቱሩፋት የሚያስገኙ ግዛቶችን እንደተቆጣጠሩ ናቸው!

በዘመነ-ደርግ የሱዳን ሰራዊት አይደለም ወረራ መፈፀም ወደኢትዮጵያ ድንበር ተጠግቶ እንኳ መሽናት አይችልም ነበር!

ኧረ በዘመነ-ህወሓትም የሀገር ሉአላዊነትና ዳር ድንበር ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ አልገባም!
3.5K views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 15:35:00 በግሌ ስለፋኖም ሆነ ልዩ ሀይሉ የሚሠማኝ ይኸው ነው!

በትግል ላይ የሰነበተውና አሁንም በግንባር ላይ ታጥቆ የሚገኘው ፋኖ ፥ እንደህዝብ ያለንበትን አሳሳቢ የህልውና አደጋ ከተረዳና ለመታገል ቁርጠኝነቱ ካለው ፥ ግራም ነፈሰ ቀኝ ያለው አማራጭ አንድና አንድ ነው!



የታጠቁ ሀይሎቹን ይዞ በቋሚነት ወደሚንቀሳቀስበት የትግል  መሬት መጓዝና መስፈር!  ደጋፊና አባላቶቹም መስመሩ በተለየ ግልፅ መንገድ ይደግፉት ፥ ይቀላቀሉት!

ከተማና መሀል አገር ሆኖ ግን ሁልጊዜ "ተከበበ" እያልን መኖራችን ይቀጥላል እንጂ ፥ መክበባቸውም ሆነ ትጥቅ ለማስፈታት መንቀሳቀሳቸው ፈፅሞ አይቀሬ ነው!

ያ ካልሆነ ግን የሁልጊዜ   አጀንዳችን ፥ ህዝብን ከከበባ ይታደጋል ተብሎ የታመነበትን ፋኖ "  ...ተከበበ ፥ ታሰረ ፥ ትጥቅ ተቀማ ፥  ...! " የሚል ብቻ ሆኖ ራሳችንን እያደከምን  መጓዛችን ይቀጥላል!

ይህ ከሚሆን ደግሞ በየቤቱ ሆኖ እንደህዝብ  የሚደረገው ትግል አካል ሆኖ የሚጠበቅበትን ቢወጣ የተሻለ ይሆናል!

ልዩ ሀይሉም መወሰን ያለበት ፥ ከዚህ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ውሳኔ ነው ብዬ አምናለሁ!

ትጥቁን እንደያዘ ሚሊተሪውን አውልቆ ወደህዝቡና ቤተሰቡ ተቀላቅሎ ይታገል!  ዙሮ ዙሮ የተፈራውና የገመትነው ሁሉ እየተፈፀመ መሆኑ የተረጋገጠ ነውና በየአካባቢው ሆኖ ለቀጣይ የተቀናጀ ህዝባዊ ትግል ራሱን ያዘጋጅ!

ያ ካልሆነ ደግሞ የራሱን እዝና የአደረጃጀት ሰንሰለት ዘርግቶ ገዢ ቦታ ይዞ የሚታገልበትን አማራጭ ማበጀት አለበት!

አለበለዚያ ግን በሴራ የፖለቲካ አመራሮች ግራ እንደተጋባ ዩኒፎርም ለብሶ ከወዲያ ወዲህ   እንገፍ እንገፍ ማለቱን ከቀጠለ ፥  እጣፋንታው ተለቅሞ ማለቅና በጠላት እጅ መውደቅ ይሆናል!

አሁን ባለው መንገድና ነባራዊ ሁኔታ ፥ ሁለቱም ሀይሎች ለህዝቡ ተጨማሪ ጫና ከመፍጠር ውጪ ጫናውን ወደሚያቀል የትግል ስርአትም ሆነ ተደራዳሪ ኃይል ወደመፍጠር ሊገቡ አይችሉም!

ይኸው ነው!
3.7K viewsedited  12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 14:47:01 ከ80 የአለም ሀገራት ህዝብ ቁጥር የሚበልጥ ተፈናቃይ የተሸከመው የአማራ ክልል!

የአማራ ክልል መንግሥት ባመነው ስታስቲክስና አሚኮ በዘገበው መረጃ ብቻ ተመስርተን ፥ ከመላ ሀገሪቱ በተለይም ከኦሮሚያ ክልል በሚፈፀምባቸው ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ፥ ጭፍጨፋና ማፈናቀል ሳቢያ ህይወታቸውን ለማትረፍ ተሰደው ወደክልሉ የገቡና በተለያዩ የስደተኛ መጠለያዎች ብሎም በየጎዳናው የተበተኑ አማራዎች ቁጥር 2.4 ሚሊየን አልፏል፡፡

ይህ አሀዝ ላለፉት ወራት ከአዲስአበባና ከዙሪያዋ ካሉ ከተሞች ቤታቸው በላያቸው ላይ እየፈረሰ የተሰደዱትን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን አያካትትም!

ከ120 ሚሊየን በላይ ህዝብ የያዘችው ኢትዮጵያ ከ224 የአለም ሀገራት ተርታ ፥ በህዝብ ቁጥር 12ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ፥ አፍሪካዊቷ ቦትስዋና ደግሞ በ2,375,000 ህዝብ 145ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ታዲያ ይህ ባለፈው አሚኮ የዘገበውና መንግሥት ያመነው 2.4 ሚሊየን የተፈናቃዮች ቁጥር ብቻ ከአለም ሀገራት የ80ዎቹን ህዝብ ቁጥር የሚበልጥ ነው!

በሀገራችን ያሉ ክልሎችን እንኳ ብናነፃፅር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ሕዝብ ያህል ነው። የሌሎች በርከት ያሉ ክልሎችን ሕዝብ ይበልጣል። ሐረሪ ፣ ጋምቤላ ፣ አፋር ፥ ክልሎች ሕዝብ ድምር ይበልጣል፡፡

ወዳጄ! እንግዲህ ምንም ዝርዝር ሳያስፈልገው ፥ ይህ ምን ማለት እንደሆነ የማይገባው ለአፈናቃይ ብቻ ነው!

የአለም ሀገራቱን የህዝብ ቁጥር ደረጃ ለማረጋገጥ ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ!

https://www.nationsonline.org/oneworld/population-by-country.htm
3.8K views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 02:16:25
ለአማራ ልዩ ሀይል የተሻለ አማራጭ የሚሆነው ብዬ የማስበው!

ትጥቁን እንደያዘ ሚሊተሪውን አውልቆ ወደህዝቡና ቤተሰቡ ተቀላቅሎ ይታገል! ዙሮ ዙሮ የተፈራውና የገመትነው ሁሉ እየተፈፀመ መሆኑ የተረጋገጠ ነውና በየአካባቢው ሆኖ ለቀጣይ የተቀናጀ ህዝባዊ ትግል ራሱን ያዘጋጅ!

ያ ካልሆነ ደግሞ የራሱን እዝና የአደረጃጀት ሰንሰለት ዘርግቶ ገዢ ቦታ ይዞ የሚታገልበትን አማራጭ ማበጀት አለበት!

አለበለዚያ ግን በሴራ የፖለቲካ አመራሮች ግራ እንደተጋባ ዩኒፎርም ለብሶ ከወዲያ ወዲህ እንገፍ እንገፍ ማለቱን ከቀጠለ ፥ እጣፋንታው ተለቅሞ ማለቅና በጠላት እጅ መውደቅ ይሆናል!
4.8K viewsedited  23:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 01:57:50
አመሻሹን ከደሴ ወደ ደብረብርሃን በመጓዝ ላይ የነበሩት ልዩ ሀይሎች ፥ ሰንበቴ ላይ ከተሳፈሩበት መኪና አውርደው የጨፈጨፏቸው በዚህ መልኩ ነው!
4.5K views22:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 01:50:34
4.2K views22:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ