Get Mystery Box with random crypto!

በነገራችን ላይ በብዙ ጉዳዮች ዙሪያ 'ተግ' ማለት ይጠበቅብናል! በትክክልም 'በምሬ ወዳጆ የሚመራ | ዘሪሁን ገሠሠ

በነገራችን ላይ በብዙ ጉዳዮች ዙሪያ "ተግ" ማለት ይጠበቅብናል!

በትክክልም "በምሬ ወዳጆ የሚመራው የፋኖ ጦር ይቅርታ ጠይቆ ትጥቅ ፈታ!" ብንባል ፥ ጠላት የፈለገውን ይበልና ያላግጥ እንጂ የእኛ አተያይና ምልከታ Still positive መሆን መቻል አለበት እንጂ ለዝርጠጣና ለፍረጃ መጣደፍ የሚጎዳው እኛኑ መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡ መደናገጥም ፍፁም ስህተት ነው፡፡

ሁለተኛው ነገር ከነባራዊ ሁኔታውና ከእውነታው ጋር መጋፈጥን እንልመድ! በጀግንነታቸውና በህዝብ ልጅነታቸው ብዙ ብዙ ያወደስናቸውን አመራሮቻችንን ሌላው ቀርቶ ተሳስተውም ቢሆን ቢያንስ ለአንድ ጊዜ ማመንን ልንካን ይገባል! ሰው ሲሰራ ይሳሳታልና ተፈጥሯዊውን የመሳሳት እድል እንኳ መስጠት ያስፈልጋል! የመላእክት አይነት የፍፁማዊነት አካሄድን መጠበቅ ፥ አስር አመት ያወደስናቸውን በአንድ ጊዜ ስህተት " አይናችሁን ለአፈር!" እያስባለን ብዙ ጠንካሮቻችንን እያሳጣን መሆኑንም ማወቅ ጠቃሚ ነው! ነገሮችን በእነሱ ጎን ሆኖ ማጤንም ብልህነት ነው!

ከዚህ አኳያ በነምሬ ጉዳይም ቢሆን መረጃዎች "ከበሬው አፍ ...!" እስኪደርሱን ቢያንስ ለውሳኔና ለትችት ከመጣደፋችን በፊት ፦

"ይህን ለመወሠን ምን አስገደዳቸው ?"
"ምንስ አማራጭ ነበራቸው?"
"ይህን ባይወስኑ ምን ይከተላቸው ነበር?"
"የሚከተለውን ነገርስ መቋቋም ይችላሉ ወይ ?"
" ይህን በመወሰናቸው ምን አተረፉ?"
"ይህን በመወሰናቸው ጉዳቱስ ምንድን ነው?"
" ከዚህ ውጭ ያላቸውን አማራጭ ለመከተልስ በቅድሚያ ምን ማድረግ መቻል አለባቸው?"
" የትኛውን ለመንከስ የት ጋር ማንከስስ አለባቸው ?
.
ወዘተረፈ ከሚሉት ተጠይቆች ተነስተን የሁኔታ ግምገማ ማድረግ መቻል ብልህነት ነው!

በመሆኑም ራሴን ጨምሮ አብዛሀኛዎቻችን ነገሮችን በስክነትና በብልሃት ማጤንን ብሎም ለድምዳሜ አለመቸኮልን መለማመድ ከቻልን ብዙ ፍሬአማ ጉዞዎችን ወደፊት እንጓዛለን!

መልካም ምሽት!