Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳን ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ በጀት ተደበደበ! ሱዳን ፖስት ቀደም ብሎ ባወጣው ዘገባ ፤ በ | ዘሪሁን ገሠሠ

የሱዳን ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ በጀት ተደበደበ!

ሱዳን ፖስት ቀደም ብሎ ባወጣው ዘገባ ፤ በጄኔራል መሐመድ ዳጋሎ (ሒሚቲ) የሚመራው የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ጦር (RSF) ካርቱም የሚገኘውን አየር ማረፊያና በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል የሚገኘውን የሜርዌን ጦር ሰፈር መቆጣጠሩን ዛሬ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ገልፆ ነበር፡፡

በአሁኑ ሠአት ደግሞ የሩስያ ስሪት የሆኑ ሁለት ሱኮይ ሱ-57 ፌሎን ተዋጊ ጀቶች የሱዳን ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያን እየደበደቡ መሆኑንና በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ብሎም ብዙ አውሮፕላኖች መጋየታቸውን የጁባ ሚዲያ ዘገባ ያስረዳል።

በመንግሥት ኃይሎችና በፈጥኖ ደራሽ ጦር (RSF) መካከል የሚደረገው ጦርነት በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል!