Get Mystery Box with random crypto!

ሌላ ሌላውን እንተወውና...! የመከላከያ ሠራዊቱ መፈክር ' የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና ሉአላዊነት | ዘሪሁን ገሠሠ

ሌላ ሌላውን እንተወውና...!

የመከላከያ ሠራዊቱ መፈክር " የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና ሉአላዊነት እናስከብራለን! " ቢልም ቅሉ ፦

ከሰሞኑ እንኳ የሱዳን ጦር ቀድሞ ከያዘው ወደ70 ኪ.ሜ የሚጠጋ የኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት ፥ በመተማ ዮኋንስ ሰፈር - 4 የልማት ቦታን በመያዝ የወረራ ማስፋፋቱን ቀጥሏል!

የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ከድንበራቸው ወደ 200 ኪሎ ሜትር ዘልቀው በመግባት የአካባቢዎቹን ስያሜ በመቀየር ፥ በስፍራው ያሉ ነገዶችን በመጨፍጨፍ ፤ የወርቅ ማዕድን ማውጫዎችን ጨምሮ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ቱሩፋት የሚያስገኙ ግዛቶችን እንደተቆጣጠሩ ናቸው!

በዘመነ-ደርግ የሱዳን ሰራዊት አይደለም ወረራ መፈፀም ወደኢትዮጵያ ድንበር ተጠግቶ እንኳ መሽናት አይችልም ነበር!

ኧረ በዘመነ-ህወሓትም የሀገር ሉአላዊነትና ዳር ድንበር ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ አልገባም!