Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-14 01:50:24 በቅርቡ የዶላር ዋጋ በመንግሥት ባንኮች ከመቶ ብር ሊያልፍ እንደሚችል ተገለፀ !

የአለም ባንክ ( WB) እና አለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ኢትዮጵያ የብርን የመግዛት አቅም አሁን ካለበት 50% እንድትቀንስ እንደሚፈልጉ መግለፃቸው ታውቋል! በዚህም መሠረት ተግባራዊ ከተደረገ አሁን በመንግሥት ባንኮች አንድ ዶላር ከሚሸጥበት 54 ብር በእጥፍ አድጎ ከመቶ ብር በላይ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው!

በአሁኑ ሠአት ዶላር ከመቶ ብር በላይ የሚመነዘረው በብላክ ማርኬት ብቻ መሆኑ የሚታወስ ነው!

ሀገሪቱ አቶ አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጣበት ማግስት ጀምሮ ፥ በዋናነት ያለአንዳች ጥናትና የኢኮኖሚስቶች ምክረ ሀሳብ ፥ የብርን የመግዛት አቅም በተደጋጋሚ እንዲቀንስ በማድረጉና በየጊዜው እያሳተመ ወደኢኮኖሚክ ስርአቱ በሚያስገባው የገንዘብ ኖት ሳቢያ ፥ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከጊዜ ወደጊዜ እየተዳቀቀና ይህን ተከትሎ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት በመፈጠሩ ፤ ለሀገሪቱ ህዝብ የኑሮ ውድነቱ እጅግ አሳሳቢና ለመቋቋም ከማይቻልበት ደረጃ እየደረሰ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

የመንግሥት ሠራተኛው ሆይ! ☞ ምናልባት ደመወዝህን በአዲሱ የዶላር ምንዛሬ ስትመታው በአለም ገበያው ላይ የምባይል ካርድ ሊገዛልህ ቢችል ነው !

ለማብራራት ☞ በአለም ገበያ ኢትዮጵያ ውስጥ የአንድ አማካኝ ደመወዝተኛ አመታዊ ክፍያ ከ1000 ዶላር በታች ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በወር በእጅህ ተጣርቶ የሚደርስህ 5 ሺ ብር በአለም ገበያ 50 ዶላር ሲሆን ፥ የ12 ወር አመታዊ ክፍያህ 600 ዶላር ይሆናል ማለት ነው፡፡

ስለገንዘብ የመግዛት አቅም መቀነስ ( devaluation ) ጥቅምና ጉዳት በተመለከተ ለማንበብ ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው ከወራት በፊት ለአንድ ካድሬ የሰጠሁትን መልስ ያንብቡ!

https://www.facebook.com/100077915236550/posts/168450745762099/?app=fbl

ኧረ አሁንስ ከፋ ጓዶች!
4.4K views22:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 20:16:09 አሳዛኝ ዜና!

አሁን ከመሸ ወደ ሸዋሮቢት በሀይሩፍ መኪና በመጓዝ ላይ የነበሩ 3 ልዩ ሀይሎችን ሰንበቴ ወረዳ ፥ ባልጭ ቀበሌ ሲደርሱ ከመኪና አውርደው ረሽነዋቸዋል!
5.4K views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 20:23:59 አንድ ወዳጄ ያጋራኝን የአዛውንቱን ዝንጀሮ ታሪክ ላካፍላችሁ!

እድሜ ጠገቡ ዝንጀሮ በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እያቃሰተ ነው፡፡ ልጆቹ ዙሪያውን ከብበውት የመጨረሻ የኑዛዜ ቃሉን መስማታቸውን ቀጥለዋል፡፡

በመሞቻው የመጨረሻ ሠአት ላይ የሚገኘው ዝንጀሮ እያቃሰተ ፦

<< እንግዲህ ልጆቼ አደራ ... መሞቴን እንዳረጋገጣችሁ በክብር የአቀባበር ስነ-ስርአት ቅበሩኝ ... ቀብሬን አክሱም ጽዮን አድርጉልኝ ... ፍትሐቴን ደግሞ ጎንደር ላይ ይሁንልኝ ... ተዝካሬን ደግሞ ላሊበላ እንዲወጣ አድርጉት ... ! >> በማለት ኑዛዜውን ቀጠለ ...

ኑዛዜውን የሚሠሙት ልጆች በአባታቸው ንግግር ተደናግጠው እርስበርስ ተያዩ፡፡

ነገር ግን አባታቸው በኑዛዜው መጨረሻ የተናገረው ዐረፍተ ነገር ሁሉንም ከድንጋጤአቸው አረጋጋቸው፡፡

<< ... ልጆቼ ይህንን የምናዘዘው ፥ ችላችሁ ታደርጉታላችሁ ብዬ ሳይሆን ... አያ ዝንጀሮ እንዲህ ብሎ ሞተ ተብሎ እንዲወራልኝ ፈልጌ ነው! >> ብሏቸው አረፈው!

ኧረ እነግርማ የሺጥላ ቢያንስ በ11ኛው ሰአታችሁ እንኳ ጥሩ ነገር ተናግራችሁ እለፉ!

ሻፓራካሻናታቂጦባራሲኮ!
3.7K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 18:24:08
#Breaking_News

መከላከያ ሰራዊት በሀገር አቀፍ ደረጃ በብሔራቸው አማራ የሆኑ ጋዜጠኞችን እና የፖለቲካ መሪዎችን ብቻ እየለየ ቤት ለቤት እየዞረ ማፈን ጀመረ።

ለአብነት ያህልም ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ዛሬ ከቀኑ 11:50 ላይ የመከላከያ ኮማንዶዎች አፍነው ወስደውታል። ዳዊት በጋሻው ባህርዳር ከሚገኘው ሆምላንድ ሆቴል ከጓደኞቹ ጋር ሻይ እየጠጣ በነበረበት ሰዓት እንደወሰዱት ታውቋል።

ጋዜጠኛው አሁን የት እንደተወሰደ ማወቅ ያልተቻለ ሲሆን፤ አሳሪዎቹ ኮማንዶ መሆናቸውን ተገልጿል።

ምንጭ፦ ኢትዮ 251 ሚዲያ
4.4K views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 17:59:23 ጥንቃቄ
Alert

መከላከያ ሠሞንኛው ህዝባዊ እምቢተኝነትና ተቃውሞ በተደረገባቸው የመላው አማራ ክልል ከተሞች "ተፅዕኖ ፈጣሪና አስተባባሪ ናቸው!" የተባሉ ወጣቶችን ስም ዝርዝር በመዋቅራዊ አመራሮች በኩል ተዘርዝሮ  እንዲሰጠው እየጠየቀ ይገኛል፡፡ ደብረብርሃንን የመሠሉ ከተሞች ላይ የነውሩ ተባባሪ የሆኑ አመራሮች መኖራቸውን መረጃዎች ደርሰውናል፡፡ እቅዱ ግን በመላው የአማራ ክልል ከተሞች ነው፡፡

ይህ ሌላኛው እልቂትና ትርምስ መፍጠሪያ አጀንዳ መሆኑ ነው! ይህ አሁንም ክልሉ እንዳይረጋጋና አማራጭ መፍትሄዎች ተግባራዊ እንዳይደረጉ የተወጠነ ሌላኛው የሴራ አጀንዳ ነው፡፡

መላው የአማራ ክልል የዞን ፤ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች በዚህን አይነቱ እጅግ አደገኛ መንገድ ውስጥ  ባለመግባት ከታሪካዊ ተጠያቂነት ራሳቸውን ማራቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

እስርና ግድያ ህዝባዊ ትግልን  ይበልጥ ያቀጣጥለዋል እንጂ አይቀለብሰውም፡፡ ነገርግን ይህ መንገድ ህዝቡ ከታችኛው አመራር ጋር እንዲጋጭና የእርስበርስ መተላለቅ እንዲፈጠር ለሚያደርግ የተጠነሰሰ አደገኛ የጥፋት መንገድ ነው፡፡

ይህ በደርግ ዘመን "ኢህአፓ ወዘተርፈ " እያሉ ወጣቶችን  ጠቁመው ሲያስረሽኑ ከነበሩት የዘመናችን የጥቁር ታሪክ አካላት ጋር የሚስተካከል ጉዳይ ነው፡፡

በመላው አማራ ክልል የሚፈፀም እስር ካለ ፥ በቀጥታ የአመራሩ እጅ እንዳለበትም መገንዘብ ያስፈልጋል!

ሠዎቹ ግን የሚረባረቡት  ይቺን ሀገር ከዚህ በላይ ወደምን አይነት አዘቅት ለመዝፈቅ ነው?

#ሼር አድርጉት!
5.0K views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 17:12:08 ያለፈው 1 ሳምንት ህዝባዊ ንቅናቄ ፤ ለጋራ ኮዙ በማንኛውም ጊዜ ፥ ዳር እስከዳር "ሆ!" ብሎ መነሳት የሚችል ጠንካራ ህዝባዊ ሀይል እንዳለ መረዳትም ማስረዳትም ተችሎበታል!

አላማና ግብን ለይቶ ከማሳካት ፤ ከአደረጃጀትና ስትራቴጂክ ሊደርሽፕ ከመስጠት አኳያ ግን ገና ብዙ ብዙ ርቀት መጓዝ ይጠበቅብናል!

በመሆኑም ፦ ይህ ህዝባዊ ንቅናቄና ቁጣ የፈጠረው ስሜት ሳይረግብ ፥ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም "ፍሬ" ያለው የትግል መቋጫ ላይ ለመድረስ እንድንችል ፦

የትግሉን መሪዎች ☞ መፍጠር
የጋራ አላማና ግብን ☞ መለየት
ጠንካራ አደረጃጀት ☞ መዘርጋት

ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ፥ ሰፊና አፋጣኝ ስራዎች መሠራት ይኖርባቸዋል!

ህዝባዊ ጥያቄዎች ምላሽ እስካላገኙ ፥ የተዛቡት እስካልተስተካከሉ ፥ የታመሙት እስካልተፈወሱ ድረስ ህዝባዊ ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

"የሠላም በሮች ሲዘጉ ፤ የአመፅ በሮች ወለል ብለው ይከፈታሉ!"

#Amhara_Resistance
4.3K viewsedited  14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 15:53:14
4.0K views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 15:52:23 ኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ …!

ኮምቦልቻ ከተማ በዛሬው እለት መደበኛ የስራ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል፡፡ ትናንት እንደህዝብ በአማራ ክልል ከተሞች ከፍተኛ ቁጣ የቀሰቀሰውን ህዝባዊ አጀንዳ አንግባ ለ2ተኛ ቀን በአደባባይ ተቃውሞዋን አሰምታለች ፥ ህዝባዊ ጥያቄዎቹም በሚገባ ተስተጋብተዋል፡፡

አደባባይ የወጣው ማህበረሰብም የመከላከያ ሠራዊት በአስነዋሪ መልኩ ወደሰላማዊ ሰልፈኛው ላይ እስከተኮሰበትና ድባቡን ወደአሳዛኝ ሁኔታ እስከቀየረበት ሰአት ድረስ ፥ ሀላፊነት በተሞላበት መልኩ ሰልፉ ሲከናወን ፥ ስሜቱንም ሲገልፅ ነበር፡፡ ሰልፈኛው ተቃውሞና ቁጣውን ከመግለፅ ባለፈ ፥ ህዝባዊና የግል ተቋማትንም ሆነ ሌሎች እኛኑ ዞረው የሚጎዱ ተግባራትን አልፈፀመም ፥ አይፈፅምም፡፡

በሂደቱ ግን በርካታ ነገሮችን የታዘብንበት ሆኖ አልፏል፡፡ በጋራ ኮዝ ላይ እንኳ ተመሳሳይ መረዳት ከሌላቸው ጀምሮ ይህን እንደህዝብ የጋራ ጥያቄና መሠረታዊ ነጥብ ሊሆን የሚገባውን አጀንዳ በፍላጎታቸውና በጠባብ አእምሯቸው ልክ ሊበይኑ ሲዳዱ እስካየናቸው ኃይሎች ድረስ ታይቶበታል ፥ በቂ ሌሰኖችንም የወሰድንበት ነው፡፡

አንዳንዶች አጀንዳዎችን አጣመው ለግለሰቦች ለመስጠት ፥ የራስ ፍላጎትን በማሽቃበጥ ለማሳካት ቁንፅል የሀሳብ ማራመጃ ለማድረግ አናሳ አስተሳሰባቸውን ሲያንፀባርቁበትም አይተናል፡፡ ራሳቸውን የሰላም ብቸኛ ዘብና ፈላጊ አድርገው በህዝብ መሠረታዊ ጥያቄ ላይ የተመፃደቁትንም ቤት ይቁጠራቸው፡፡

ያም አለ ይህ የመከላከያ ሰራዊቱ አረመኔያዊ ጥቃት ድባቡን እስከቀየረበት ሰአት ድረስ ግን ፥ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና የፀጥታ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት በመወጣት ህዝባዊ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡

እንደሀገር ህዝባችንን ኑሮውን አጣብቂኝና ሰቀቀን ካደረጉት ፥ እጅግ በርካታ የህልውና ፥ የማህበረ-ፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ማነቆዎች እስካልተላቀቀና ጥያቄዎቹ እስካልተመለሱ ድረስ ሁለንተናዊ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠሉ ተፈጥሯዊና የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡

በሠላማዊ አማራጭና ስርአታዊ በሆነ መልኩ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ያልቻለ ስርአትም አመፅና እምቢተኝነትን በራሱ ላይ መጋበዙ እሙን ነው! አሁን በሀገራችን እየሆነ ያለውም ይኸው ነው! "የሠላም በሮች ሲዘጉ የአመፅ በሮች ወለል ብለው ይከፈታሉና !

በትናንትናው እለት በመከላከያ ጥቃት በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን መስዋዕት ላደረጉ ወገኖቻችንን ወዳጅ ዘመዶች ብርታቱን ፥ ቆስለው በህክምና ላይ ለሚገኙት በቶሎ ማገገምን እመኛለሁ !

ሁለንተናዊ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!

#Amhara_Resistance
3.9K views12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 14:30:15 ቀልደኛ ገበሬ ፤ ....!

በትናንትናው እለት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከወለንጭቲ ወደ መተሃራ በመንቀሳቀስ ላይ በነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ "ኦነግ-ሸኔ" በሚል የዳቦ ስም በሚንቀሳቀሰው በመንግሥት የሚደገፍ ኃይል በተፈፀመ የተቀነባበረ ጥቃት 50 ያህል የፌደራል ፖሊስ አባላት ሲገደሉ ፣ ከ40 ያላነሱት ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል! ከተገደሉት መካከል አመራሮችም እንደሚገኙበት የተገለፀ ሲሆን ሙሉ ትጥቃቸው መወሰዱም ታውቋል፡፡

ይህ ቡድን እንደሚታወቀው ላለፉት አመታት በንፁሀን ዜጎች ላይ ያለእረፍት ከፈፀመው የዘር ፍጅት ፥ አሰቃቂ ግድያና ማፈናቀል ባሻገር ፥ በስፍራው የሚንቀሳቀሱ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላቶችን ጭምር ፥ ከመንግሥት መዋቅር በሚያገኘው መረጃ በመታገዝ በጉዞ ላይ እያሉ አሰቃቂ ጭፍጨፋና ዘረፋ በመፈፀም የሚታወቅ ነው፡፡ በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ሲፈፅምም ይህ የመጀመሪያው አለመሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ፥ የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ ገና ለስምሪት ሲወጡ ሙሉ ስማቸው ፥ ሀላፊነታቸው ፥ ብሄራቸው ብሎም የታጠቁት መሳሪያና የጉዞ መረጃዎቻቸውን አስቀድመው ለገዳይ ቡድኑ መረጃ የሚያደርሱት በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ የቡድኑ አካላት መሆናቸው በተደጋጋሚ ሲገለፅ ቆይቷል፡፡

ይህ ለይስሙላ "አሸባሪ" ብለን ፈረጅነው ያሉት ኃይል በክልሉ በርካታ አካበቢዎችን ተቆጣጥሮ ፥ በነፃነት እያሰለጠነና ትጥቅ በገፍ እየቀረበለት ፥ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ዜጎችን ፣ ኢንቨስተሮችና ጎብኚዎችን ሳይቀር እያገተ ገንዘብ የሚደራደር ፥ አሰቃቂ ግድያ የሚፈፅምና ክልሉን ወደ አስፈሪ ምድራዊ ሲኦልነት የቀየረ የሽብር ቡድን ነው፡፡

መንግሥት "የክልሎችን በተለይም የአማራ ልዩ ኃይልን ለማፍረስ እየተጣደፈ የሚገኘው" ባሰማራው የፀጥታ ሀይል አይደለም የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ይቅርና ያሰማራቸው የፀጥታ አካላት እንኳ በዚህ መልኩ በተቀናበረ መልኩ በሚጨፈጨፉበት ፥ ዜጎች ወጥቶ መግባት አስፈሪ በሆነባቸው ፥ ሌላው ቀርቶ "ኦነግ ሸኔ " ብሎ የሚያቆላምጠውን አሸባሪ ቡድን ትጥቅ ማስፈታት ባልቻለበት ሀገር ውስጥ እየኖርን ነው፡፡

"ቀልደኛ ገበሬ በሰኔ ይሞታል!" እንዲሉት ብሂል ...!
4.3K views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 14:03:34 ትጥቅ መፍታት ያለበት ማን ነው?

ኦሮሚያ ውስጥ ትናንት በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፅሟል። በተጠና መልኩ ከወለንጭቲ ወደ መተሃራ በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጥቃት ደርሶባቸዋል።  ጥቃቱ በተጠና መልኩ የተደረገ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን 50 ያህል የፌደራል ፖሊስ አባላት ተገድለው፣ ከ40 ያላነሱ ቆስለዋል። ከተገደሉት መካከል አመራሮችም እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን መሳርያዎቻቸው ተወስደዋል።

"ኦነግ ሸኔ" ተብሎ የሚነገርለት የክልሉ መዋቅር የሚደግፈው ኃይል ትጥቅ ሳይፈታ ነው የሌሎቹ ክልሎች በተለይም የአማራ ልዩ ኃይል ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅሮች ይጠቃለል የሚሉን።

@Getachew Shiferaw
4.2K views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ