Get Mystery Box with random crypto!

ጥንቃቄ Alert መከላከያ ሠሞንኛው ህዝባዊ እምቢተኝነትና ተቃውሞ በተደረገባቸው የመላው አማራ | ዘሪሁን ገሠሠ

ጥንቃቄ
Alert

መከላከያ ሠሞንኛው ህዝባዊ እምቢተኝነትና ተቃውሞ በተደረገባቸው የመላው አማራ ክልል ከተሞች "ተፅዕኖ ፈጣሪና አስተባባሪ ናቸው!" የተባሉ ወጣቶችን ስም ዝርዝር በመዋቅራዊ አመራሮች በኩል ተዘርዝሮ  እንዲሰጠው እየጠየቀ ይገኛል፡፡ ደብረብርሃንን የመሠሉ ከተሞች ላይ የነውሩ ተባባሪ የሆኑ አመራሮች መኖራቸውን መረጃዎች ደርሰውናል፡፡ እቅዱ ግን በመላው የአማራ ክልል ከተሞች ነው፡፡

ይህ ሌላኛው እልቂትና ትርምስ መፍጠሪያ አጀንዳ መሆኑ ነው! ይህ አሁንም ክልሉ እንዳይረጋጋና አማራጭ መፍትሄዎች ተግባራዊ እንዳይደረጉ የተወጠነ ሌላኛው የሴራ አጀንዳ ነው፡፡

መላው የአማራ ክልል የዞን ፤ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች በዚህን አይነቱ እጅግ አደገኛ መንገድ ውስጥ  ባለመግባት ከታሪካዊ ተጠያቂነት ራሳቸውን ማራቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

እስርና ግድያ ህዝባዊ ትግልን  ይበልጥ ያቀጣጥለዋል እንጂ አይቀለብሰውም፡፡ ነገርግን ይህ መንገድ ህዝቡ ከታችኛው አመራር ጋር እንዲጋጭና የእርስበርስ መተላለቅ እንዲፈጠር ለሚያደርግ የተጠነሰሰ አደገኛ የጥፋት መንገድ ነው፡፡

ይህ በደርግ ዘመን "ኢህአፓ ወዘተርፈ " እያሉ ወጣቶችን  ጠቁመው ሲያስረሽኑ ከነበሩት የዘመናችን የጥቁር ታሪክ አካላት ጋር የሚስተካከል ጉዳይ ነው፡፡

በመላው አማራ ክልል የሚፈፀም እስር ካለ ፥ በቀጥታ የአመራሩ እጅ እንዳለበትም መገንዘብ ያስፈልጋል!

ሠዎቹ ግን የሚረባረቡት  ይቺን ሀገር ከዚህ በላይ ወደምን አይነት አዘቅት ለመዝፈቅ ነው?

#ሼር አድርጉት!