Get Mystery Box with random crypto!

ቀልደኛ ገበሬ ፤ ....! በትናንትናው እለት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከወለንጭቲ ወደ መተሃራ በመን | ዘሪሁን ገሠሠ

ቀልደኛ ገበሬ ፤ ....!

በትናንትናው እለት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከወለንጭቲ ወደ መተሃራ በመንቀሳቀስ ላይ በነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ "ኦነግ-ሸኔ" በሚል የዳቦ ስም በሚንቀሳቀሰው በመንግሥት የሚደገፍ ኃይል በተፈፀመ የተቀነባበረ ጥቃት 50 ያህል የፌደራል ፖሊስ አባላት ሲገደሉ ፣ ከ40 ያላነሱት ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል! ከተገደሉት መካከል አመራሮችም እንደሚገኙበት የተገለፀ ሲሆን ሙሉ ትጥቃቸው መወሰዱም ታውቋል፡፡

ይህ ቡድን እንደሚታወቀው ላለፉት አመታት በንፁሀን ዜጎች ላይ ያለእረፍት ከፈፀመው የዘር ፍጅት ፥ አሰቃቂ ግድያና ማፈናቀል ባሻገር ፥ በስፍራው የሚንቀሳቀሱ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላቶችን ጭምር ፥ ከመንግሥት መዋቅር በሚያገኘው መረጃ በመታገዝ በጉዞ ላይ እያሉ አሰቃቂ ጭፍጨፋና ዘረፋ በመፈፀም የሚታወቅ ነው፡፡ በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ሲፈፅምም ይህ የመጀመሪያው አለመሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ፥ የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ ገና ለስምሪት ሲወጡ ሙሉ ስማቸው ፥ ሀላፊነታቸው ፥ ብሄራቸው ብሎም የታጠቁት መሳሪያና የጉዞ መረጃዎቻቸውን አስቀድመው ለገዳይ ቡድኑ መረጃ የሚያደርሱት በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ የቡድኑ አካላት መሆናቸው በተደጋጋሚ ሲገለፅ ቆይቷል፡፡

ይህ ለይስሙላ "አሸባሪ" ብለን ፈረጅነው ያሉት ኃይል በክልሉ በርካታ አካበቢዎችን ተቆጣጥሮ ፥ በነፃነት እያሰለጠነና ትጥቅ በገፍ እየቀረበለት ፥ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ዜጎችን ፣ ኢንቨስተሮችና ጎብኚዎችን ሳይቀር እያገተ ገንዘብ የሚደራደር ፥ አሰቃቂ ግድያ የሚፈፅምና ክልሉን ወደ አስፈሪ ምድራዊ ሲኦልነት የቀየረ የሽብር ቡድን ነው፡፡

መንግሥት "የክልሎችን በተለይም የአማራ ልዩ ኃይልን ለማፍረስ እየተጣደፈ የሚገኘው" ባሰማራው የፀጥታ ሀይል አይደለም የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ይቅርና ያሰማራቸው የፀጥታ አካላት እንኳ በዚህ መልኩ በተቀናበረ መልኩ በሚጨፈጨፉበት ፥ ዜጎች ወጥቶ መግባት አስፈሪ በሆነባቸው ፥ ሌላው ቀርቶ "ኦነግ ሸኔ " ብሎ የሚያቆላምጠውን አሸባሪ ቡድን ትጥቅ ማስፈታት ባልቻለበት ሀገር ውስጥ እየኖርን ነው፡፡

"ቀልደኛ ገበሬ በሰኔ ይሞታል!" እንዲሉት ብሂል ...!