Get Mystery Box with random crypto!

ኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ …! ኮምቦልቻ ከተማ በዛሬው እለት መደበኛ የስራ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል፡፡ | ዘሪሁን ገሠሠ

ኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ …!

ኮምቦልቻ ከተማ በዛሬው እለት መደበኛ የስራ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል፡፡ ትናንት እንደህዝብ በአማራ ክልል ከተሞች ከፍተኛ ቁጣ የቀሰቀሰውን ህዝባዊ አጀንዳ አንግባ ለ2ተኛ ቀን በአደባባይ ተቃውሞዋን አሰምታለች ፥ ህዝባዊ ጥያቄዎቹም በሚገባ ተስተጋብተዋል፡፡

አደባባይ የወጣው ማህበረሰብም የመከላከያ ሠራዊት በአስነዋሪ መልኩ ወደሰላማዊ ሰልፈኛው ላይ እስከተኮሰበትና ድባቡን ወደአሳዛኝ ሁኔታ እስከቀየረበት ሰአት ድረስ ፥ ሀላፊነት በተሞላበት መልኩ ሰልፉ ሲከናወን ፥ ስሜቱንም ሲገልፅ ነበር፡፡ ሰልፈኛው ተቃውሞና ቁጣውን ከመግለፅ ባለፈ ፥ ህዝባዊና የግል ተቋማትንም ሆነ ሌሎች እኛኑ ዞረው የሚጎዱ ተግባራትን አልፈፀመም ፥ አይፈፅምም፡፡

በሂደቱ ግን በርካታ ነገሮችን የታዘብንበት ሆኖ አልፏል፡፡ በጋራ ኮዝ ላይ እንኳ ተመሳሳይ መረዳት ከሌላቸው ጀምሮ ይህን እንደህዝብ የጋራ ጥያቄና መሠረታዊ ነጥብ ሊሆን የሚገባውን አጀንዳ በፍላጎታቸውና በጠባብ አእምሯቸው ልክ ሊበይኑ ሲዳዱ እስካየናቸው ኃይሎች ድረስ ታይቶበታል ፥ በቂ ሌሰኖችንም የወሰድንበት ነው፡፡

አንዳንዶች አጀንዳዎችን አጣመው ለግለሰቦች ለመስጠት ፥ የራስ ፍላጎትን በማሽቃበጥ ለማሳካት ቁንፅል የሀሳብ ማራመጃ ለማድረግ አናሳ አስተሳሰባቸውን ሲያንፀባርቁበትም አይተናል፡፡ ራሳቸውን የሰላም ብቸኛ ዘብና ፈላጊ አድርገው በህዝብ መሠረታዊ ጥያቄ ላይ የተመፃደቁትንም ቤት ይቁጠራቸው፡፡

ያም አለ ይህ የመከላከያ ሰራዊቱ አረመኔያዊ ጥቃት ድባቡን እስከቀየረበት ሰአት ድረስ ግን ፥ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና የፀጥታ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት በመወጣት ህዝባዊ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡

እንደሀገር ህዝባችንን ኑሮውን አጣብቂኝና ሰቀቀን ካደረጉት ፥ እጅግ በርካታ የህልውና ፥ የማህበረ-ፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ማነቆዎች እስካልተላቀቀና ጥያቄዎቹ እስካልተመለሱ ድረስ ሁለንተናዊ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠሉ ተፈጥሯዊና የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡

በሠላማዊ አማራጭና ስርአታዊ በሆነ መልኩ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ያልቻለ ስርአትም አመፅና እምቢተኝነትን በራሱ ላይ መጋበዙ እሙን ነው! አሁን በሀገራችን እየሆነ ያለውም ይኸው ነው! "የሠላም በሮች ሲዘጉ የአመፅ በሮች ወለል ብለው ይከፈታሉና !

በትናንትናው እለት በመከላከያ ጥቃት በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን መስዋዕት ላደረጉ ወገኖቻችንን ወዳጅ ዘመዶች ብርታቱን ፥ ቆስለው በህክምና ላይ ለሚገኙት በቶሎ ማገገምን እመኛለሁ !

ሁለንተናዊ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!

#Amhara_Resistance